
ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከ1920ዎቹ ትውልዶች የቀለም ቀንድ፣ የአገርና የሃይማኖት ፍቅር፣ የአንድነትና የነፃነት ቀናዒ ከነበሩት አንዱ እንደሆኑ ይታወቃል። አሥራት ሞትን ታግለው፣ ድል እየነሱ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ሕይዎት ሲታደጉ የኖሩ፣ ምርጥ የቀዶ ጥገና ሐኪም እንደነበሩ ሕያው ታሪካቸው ያስረዳል።
በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በተገዙት ሽዕቢያና ወያኔ ትብብር፣ የአገራችን ዳር ድንበር ሲቆራረስ፣ ሰንደቅ ዓላማችን ሲራከስ፣ ቀይባሕር የባዕድ እንዲሆን ሲደረግ፣ ሕዝቡ በነገድ ተከፋፍሎ ዓይንና ናጫ እንዲሆን ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና ሲሰጥ፣ አሥራት ይህ ሊሆን አይገባውም በማለት ከተሰበሰቡት የነገድ ድርጅቶች መካከል ድምፃቸውን ያሰሙት እርሳቸው ነበሩ። ቀጥሎም ዐማራን ለማጥፋት ዓላማው አድርጎ የተሰለፈው ወያኔና ጓደኞቹ በሐረርጌ፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ራያና ቆቦ ወዘተ ዐማራ በዘሩ ተመርጦ ሲታረድ፣ ሲሰቃይና ከነሕይዎቱ ገደል ሲጣል፣ ለዚህ ሕዝብ ድምፅ ለመሆን የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅትን (መዐሕድ) አቋቁመው የሕዝቡን በደል ለዓለም ማኅበረሰብ ከማሰማት አልፈው፣ ዐማራው ተደራጅቶ ለኅልውናውና ለማንነቱ እንዲታገል ፋና ወጊ ሆነው የቆሙ እንደነበሩ በክብር ይታወሳሉ።
ይህ ጥረታቸው ከዐማራው አልፎ የመላውን አገርና አንድነት ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ኅሊና በመሳቡ ባጭር ጊዜ ውስጥ ሠፊ ዕውቅና ለማግኘት በመቻላቸው፣ ለወያኔ እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሰናልክ ሆነው ታዩ። ይህም ወያኔን እንቅልፍ ስለነሳው፣ በሀሰት ከሶ፣ ከሳሽም፣ ዳኛም፣ መስካሪም ወያኔ ሆኖ፣ በእስር አሰቃይቶና ሕክምና ከልክሎ ለሕልፈተ ሕይዎት እንደዳረጋቸው ዓለም ያውቃል።
አሥራት በሕይዎት ኖረው ባያዩትም፣ የእርሳቸውን ፈለግ የተከተለው ትውልድ «ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!» በሚል ቋሚ መፈክር ዓርማቸውን አንግቦ፣ የዐማራው ድምፅ ከአጥናፍ አጥናፍ መስተጋባት ብርክ የለቀቀበት ወያኔ፣ አጽማቸው በሰላም እንዲያርፍ አልፈለገም። ሞተው ተቀብረውም የቆመውን ወያኔ አስፈሩት። ትናንት ሕይዎታቸውን ቀጠፈ። ዛሬ ደግሞ አጽማቸው ያረፈበትን የመቃብር ቦታ፣ ግፍ የማይፈሩት የትግሬ ልጆች ማፍረሱን የወንድና የጀግና ተግባር አድርገውታል።
ኢትዮጵያውያን ስንባል ለአስከሬን ክቡር እንሰጣለን። ይህን ግን የዐማራ ጠላቶች ለሆኑት የትግራይ ትውልዶች ባዕድ በመሆኑ፣ ጠላትነታቸውን ሕይዎት በመቅጠፍ ብቻ ሳይሆን፣ አጽምንም በማድቀቅ እያሳዩን ነው። ይህ ለዐማራው ልጆች የማይረሳ የበደል በደል ነው። አሥራት የሚችሉትን ሠርተው መልካም የጽናት ምልክት ሆነው አልፈዋል። የእርሳቸውን ዓርማ አንስተን ፍቅር ለማይገባቸው ፍቅርን፣ ትዕግሥት ፍርሃት ለመሰላቸው ጀግንነትን፣ ማስተዋል አለማወቅ ለመሰላቸው፣ ማወቃችን ለማሳየት መዘጋጀት ለነገ የሚባል እንዳልሆነ ሊገባቸው በሚችለው ቋንቋ ልናናግራቸው ይገባል።
የአሥራትም ሆነ የሌሎች ኢትዮጵያውያን አጽም በክብር ካረፈበት ቦታ ሊጠበቅ ይገባዋል። አሁን በተያዘው መልኩ የአሥራትን አጽም አውጥቶ ለመጣል ከታሰበ መዘዙ ብዙ ሊሆን እንደሚችል ለትግሬ ትውልድ ሊያውቅ ይገባል። ይህ አረመኔ አገዛዝ ያልፋል። የማያልፈው ትውልድ ነው። በመሆኑም መጭው የትግሬ ትውልድ በሰላም እንዲኖር ፍላጎት ያላችሁ ትግሬዎች ይህን ግፍ በዝምታ ልትመለከቱት አይገባም። ሲጀመር የአሥራት አስከሬን በክብር ማረፍ የነበረበት ለኢትዮጵያ አርበኞች በተዘጋጀው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካነ መቃብር ቦታ ነበር። ያን ሆን ተብሎና የእርሳቸውን ክብር ያዋረድን መስሎት መለስ ከለከለ። የባንዳው የአስረሱና የዜናዊ ልጅን ጊዜ ሆነና ፣አርበኛው ተገፍተው ዘረ ባንዳው መለስ ተቀበረበት። ይህ በራሱ የፈጠረው ቂም ሳይሽር ሌላ ቂም መግባት ለምን አስፈለገ? ይህ አረመኔያዊ ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ሕሊናን የሚዘገንን ስለሆነ፤ የትግሬ ትውልድ ለመጭ ሕይዎቱ ሲል አብሮን ሊጮህ ይገባል።
የዐማራው ልጆችና ድርጅቶች ይህን ጉድ፣ ከማውገዝ ባሻገር ፣ወያኔና አጋሮቹን ሊቆጠቁጥ የሚችል ተግባር ለመፈጸም እንዘጋጅ!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ ፤ ሁሉም ዐማራ ለአንድ ዐማራ!
ቅዳሜ ግንቦት ፲፱ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም.
ቅፅ፭፣ ቁጥር ፲፮
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply