• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለማንነታችን መከታ ያልሆነን፣ ለመጠቃታችን ምክንያት እየሆነ ነው!

January 1, 2017 04:17 am by Editor 1 Comment

ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በሕዝባችን ላይ፣ በተለይም በዐማራው ነገድ ላይ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በ«አርበኞች ግንቦት 7» እያመካኘ ነው። ለዚህም ምክንያት የሆነው አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ በሚቆጣጠረው የብዙኃን መገናኛ ያላደረገውን አደረኩ፣ ያላዘመተውን ወታደር አዘመትኩ፣ «የክተት አዋጁ ፊሽካ ተነፋ»፣ በሁሉም ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴዎች እኔ አለሁበት፣ የምመራው እኔ ነኝ፣ የሚለው ወሬ ቀድሞ መነዛቱ ነው። ወሬው በትንሽ ተግባር ቢደገፍ ኖሮ ባልከፋ። ክፋቱ ምንም ዓይነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሳይጀምር፣ ኤርትራ በረሃ ከትሟል የሚባለው ፋኖ፣ የተከዜን ወንዝ ሳይሻገር፣ የወያኔ አገዛዝ አንገሽግሾት ባመቸውና በመሰለው መንገድ ጥይት የተኮሰውን ሁሉ የእኔ ነው ማለቱ፣ «ለወያኔ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ፣ ጂግራ ናት ይሏታል» እንዲል ሠፊ በር ከፍቶለታል። በመሆኑም በርካታ ዐማሮች  በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ለሞት፣ ለእስር፣ ለእንግልትና ለስደት እንዲጋለጡ ምክንያት እየሆነ መምጣቱና ይህም  ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ በመሄዱ፣ የዐማራው ነገድ ‘አርበኞች ግንቦት 7 ለማንነታችን መከታ ያልሆነ ድርጅት፣ ለጥቃታችን ምክንያት  ባይሆን ምናለበት?’ የሚል ጥያቄ እንዲያነሳ ግድ ብሎታል።

የኢትዮጵያን ፖለቲካና የወያኔን እንቅስቃሴ አዘውትረው የሚከታተሉ ሰዎች ሊያስታውሱት እንደሚችሉት፣ በነጄኔራል ተፈራ ማሞ ተጠነሰሰ ለተባለው መፈንቅለ መንግሥት ሙከራና ተፈራ ማሞን ጨምሮ ወይዘሮ እማዋይሽ ዓለሙ፣ ጀኔራል አሳምነው ጽጌ እና በርካታ ዐማራዎችን ለከፍተኛ ድብደባ፣ሥቃይና የዕድሜ ልክ እስራት መነሻ ምክንያቱ ግንቦት 7 መሆኑ ይታወቃል።  ሰሞኑን ደግሞ፣ ጉዳዩ «ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ» መሆኑ ቢታወቅም፣ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን፣ ያነሱ ወገኖች፣ ጥያቄአቸው ሕገመንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት፣ ልክ ለስልጢዎች፤ አገዎችና ቅማንቶቹ እንደተደረገው ሁሉ የእኛም የዐማራ ማንነታችን ይከበርልን ብለው በሕጋዊ መንገድ ጥያቄ ባቀረቡት የሕዝብ ተወካዮች ላይ፣ ወያኔ በአሸባሪነት ክስ የመሠረተባቸው አርበኞች ግንቦት 7  ወያኔን ለማስወገድ የትጥቅ ትግል ጀምሬአለሁ በማለት የሚያራምደው በተግባር ያልታየ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው።

ወያኔ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ላቀረቡት ሕጋዊ የማንነት ጥያቄ ተገቢ መልስ ከመስጠት ፋንታ፣ የማንነት ጥያቄ አቅራቢዎቹን የዐማራውን ክልል መስተዳድር እንደምንም ባለመቁጠር፣ «ጌታዋና የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች» እንደሚሉት፣  ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት በተላኩ የትግሬ አፋኝ ቡድኖች የአስተባባሪ ኮሚቴውን ለማፈን ባደረጉት ሙከራ፣ የኮሚቴው ሰብሳቢ የሆነው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ሕጋዊ ባልሆነ መገንገድ ሊያፍኑት ለመጡት አፋኞች እጄን አልሰጥም በማለቱ በተነሳው የአፍናለሁ አልታፈንም ግብግብ በተተኮሰ ጥይት የጎንደር ከተማን ሕዝብ የዘመናት የታመቀ ችግር መክደኛውን ገልብጦ እንዲወጣ ሰበብ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ሰበብ በመላ ጎንደር፣ ጎጃምና መሰል አካባቢዎች መዛመት ብርክ የሰደደበት ወያኔ፣ «ለብሔር/ብሔረሰቦችና ሕዝቦች  ዕኩልነትና አንድነት ዋስተና የሆነ፣ በሕዝቡ ፍላጎት የጸደቀ» እያለ ጧት ማታ የሚፎገላበትን ሕገመንግሥት አግዶ፣ የዐማራውን ነገድ በጠራራ ፀሐይ የትግሬ ሚሊሻ እንደፈለገው የሚገድልበት፣ የሚደበድብበት፣ የሚያስርበት  ወታደራዊ አገዛዝ ሙሉ መብት የሚሰጥ አዋጅ አውጆ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የሸዋና የወሎ የዐማራ ልጆችን በገፍ እየገደለና እያሰረ ይገኛል።  በመሆኑም አዋጁ ከታወጀ እስከዛሬ ድረስ ከአንድ ሺ በላይ ዐማሮች ሲገደሉ፣ ከ30,000 (ሰላሳ ሺ) በላይ ወጣቶችና አዛውንቶች ታስረው የመከራን ጥዋ በመጎንጨት ላይ ይገኛሉ። ለዚህ ሁሉ ምክንያት ሆኖ የሚጠቀሰው አርበኞች ግንቦት 7 ነው።

ለዚህ ድርጅት አመራሮችና በድርጅቱ ውስጥ አለን ለምትሉ ዐማሮች የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ግልጽ መልዕክት ሊያስተላልፍ ይወዳል። የድርጅቱን እንቅስቃሴ ከጅምሩ እስካሁን ድረስ በሚገባ ተከታትለናል። በክትትላችን ያገኘነው ውጤት አርበኞች ግንቦት ሰባት በራሱ ማንነት ላይ ያልቆመ፣ ማንነቱን ከሌሎች ጋር በሚፈጥረው «ጥምረት፣ ውሕደት፣ ቅንጅት» ወዘተ ለማሳደግ የሚጥር፣ ተፈጠረ የሚባለው ጥምረት የት እንደደረሰ ሳያታወቅና የመጀመሪያው ጥምረት ፊርማ ሳይደርቅ፣ ሌሎች ጥምረቶች የሚፈሉበት መሆኑን ታዝበናል። ከሁሉም በላይ የሚገርመው ጥምረት የሚመሠርተው ዐማራውን በዐውራ ጠላትነት ከፈረጁ ብሔርተኛ ድርጅቶች ጋር መሆኑ እርሱም በተዘዋዋሪ መንገድ የዐማራው ጠላት መሆኑን እያሳየ መጥቷል። ለምሳሌ በከማል ገልጁ ከሚመራው ኦነግ ጋር፣ ዐማራውን በጠላትነት ከመፈረጅ አልፎ፣ የሽግግር መንግሥት ተብየውን ያረቀቀውንና ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ሁኔታ ካመቻቹት፣ በአሰቦት ገዳም፣ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ ፤ በአርባጉጉ፣ ወተር፣ በወለጋ ወዘተ በገፍ ለተገደሉት ዐማሮች  አመራር የሰጡትን የነሌንጮ ለታ ቡድንና ከተገንጣዮቹ የሲዳማ ንቅናቄዎች ጋር የፈጠረው ሽርክና ፀረ-ዐማራ ብቻ ሳይሆን፣ ፀረ-ነባሯ ኢትዮጵያ መሆኑን በተግባሩ እያሳየ ነው። ከዚሁሉ አልፎ በአመራሩ አንድም የዐማራ ተወካይ በሌለበት ሁኔታ በወሳኝነት ዐማራው በሚኖርባቸው አካባቢዎች ከኤርትራ ተስፈንጥሬ አዲስ አበባ እገባለሁ የሚለው ሕልሙ ዐማራውን በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ለእልቂት እየዳረገ ነው።  በመሆኑም ሁኔታውን  ቆም ብሎ በማሰብ ያለበትን ሁኔታ መርምሮ  ዐማራው በእርሱ ስበብ ተጠቂ ሳይሆን፣ መከታው የሚሆንበትን መንገድ ይከተል። ወይም አለኝ የሚለውን ኃይሉን አሰልፎ ወያኔን ይፋለም። ለዚህም የዐማራው ልጆች በአመራሩ ወሳኝ ቦታዎችን ይስጥ። ይህ ሲሆን እኛም  ወያኔን ለማስወገድ የምንችለውን ለማድረግ እንጥራለን። ይህ ካልሆነ፣ አርበኞች ግንቦት 7 መከታችን ካልሆነ መጠቂያችን እንዲሆን የማንፈቅድ መሆኑ እንዲታወቅ እንሻለን።

ጽሁፉን በPDF ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት – ሞወዐድ
ማስታወቂያና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ 
mwaoipr@gmail.com
ቅዳሜ ታሕሳስ ፳፪ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም.

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. አሰፋ ምን ተስኖት says

    January 4, 2017 05:28 pm at 5:28 pm

    እኔ አማራ ሆኜ አማራ በወያኔ የሚፈጻምበትን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመታደግና ራሱንም ሆነ ኢትዮጵያን ከወያኔ ነጻ ለማወጣት መደራጀቱን አጥብቄ እየደገፍኩ፤ የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅትን ደጋፊም ሆኜ በዚህ መግለጫ በጣም አዝኜአለሁ በጣምም አፍሬአለሁ።
    የሞረሽ ወገኔን የሚመሩት ሰዎች የ1960ዎቹን የእርስ በእርስ መጠፋፋትና ሃገራዊና ሕዝባዊ ዓላማን ለጠላት አሳልፎ የመስጠት አባዜ የፖለቲካ ስግብግብነትና አረመኔነት ዛሬ ኢትዮጵያ ለደረሰችበት ደረጃ እንዳላደረሰን ያንኑ አሳፋሪና አፀያፊ ስህተት ዛሬም ለመድገም ሲሞክሩ ሲታይ በጣም ያሳፍራል።
    1. በአርበኞች ግንቦት 7 ሰበብ ወያኔ ሕዝብ ሊጨርስ የቻለው ብሎ መግለጫ ማውጣት ወያኔ አማራን ለመግደልና ለማጥፋት የሚሰጠው ምክንያት ትክክል ነው ወያኔ የዘር ማጥፋት ለማካሄድ ምክንያቱ ተቀባይነት አለው ብሎ የወያኔን ፋሺስታዊ እርምጃ ሕጋዊ ማድረግ ምን ይሉታል?
    2. ስለ እነ ጄ/ል ተፈራ ማሞስ ግንቦት 7ን ተጠያቂ ማድረግ አማራን እወክላለሁ ከሚልና የአማራን ትግል ይረዳል ተብሎ የሚታመንበትን ድርጅ በወያኔ ቋንቋና ወያኔያዊ በሆነ ቅጥፈትና ዓይን ያወጣ ውሸት የሚዋሽ አድርጎ ማቅረብ ምን ይሉታል?
    3. ትላንት ጦር መዘው ሲጋደሉ የነበሩ ሳይቀሩ በፖለቲካና በዲፕሎማሲ ጥበብ መቀራረብን እየፈጠሩ ለጋራ ጉዳይ የጋራ መግባባት እየፈጠሩ ነው የሃገራቸውን አንድነትም ሆነ እድገትና ብልጽግና ያመጡት እንጂ በትላንቱ በመኖር አይደለም። በኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ከአማራና ከኦሮሞ በላይ በዘር የተደባለቀ ህዝብ የለም። ስለዚህ ኦነግም ሆነ ወያኔ የዘራውን የጥላቻ መርዝ ለማርከስ ከኦሮሞ ድርጅቶች ጋር መቀራረብና በጋራ መሥራት ብልህነት የተሞላበት የፖለቲካ ጥበብ እንጂ ጉዳቱ ምን ላይ ነው?
    4. አርበኞች ግንቦት 7 ሕብረ ብሔር ድርጅት ሲሆን የትጥቅ ትግልን ጭምር የሚያራምድ ድርጅት ነው፤ ሞረሽ ለወገኔ ግን የሲቪክ ድርጅትና አማራውን ለመታደግ ጥሪ ያነሳ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ካልጠፋ ሞረሽ ለወገኔ ህልውናው ይጠፋል ያለው ማነው እና ነው ይህንን በመሰለ ሁኔታ ሞረሽ ወገኔ በገዛ ወገኑ ላይ ጦር ሰብቆ የተነሳ አስመስሎ መግለጫ ማውጣት ያስፈለገው?
    5. በጽሑፉ መጨረሻ ላይ ደግሞ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ለአማሮች ቦታ ይስጥ ይላል፤ ይህንን ጽሑፍ ያወጣው ግለሰብም ሆነ ቡድን ራሱን በሌላ ድርጅት ሥልጣን አደላዳይ ልሁን ማለቱ ምን ይሉታል?
    ብቻ የዛ ግፍና መከራ በመክፈል ላይ የሚገኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላክ ፍርዱን ይስጣችሁ። እናንተ ጠላት ፊት ለፊት ወገናችንን እየገደለና ደም እያፈሰሰ ወደ ፊት የሚያየው ዓይናችሁን አሳውራችሁ በጎናችሁ ያለውን ወገናችሁን ለመግደልና ለማጥፋት የምትጥሩ በሰማይም ሆነ በምድር ፍርዱን አትጡት።
    አሁንም ቢሆን ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ይዞት የተነሳውን ዓላማ እደግፋለሁ፤ ድርጅቱንም ወገንን ጠላት፤ ጠላትን ደግሞ ወገን በማስመሰል አማራውን በመግደልህ አይፈረድብህም በሚል ወያኔን የሚያሞካሽ መግለጫም ድርጅቱን ሳይሆን በድርጅቱ ስም መግለጫውን ያወጣው ግለሰብም ሆነ ቡድን ሊጠየቅበት ይገባል።
    እግዚአብሔር አስተዋይ ልቦና ይስጠን!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule