ይህ መጽሐፍ ባለ 657 ገፆች ነው። በዘጠኝ ምዕራፎች ተከፋፍሏል። እነርሱም፦
- የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መከፋፈል፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖት ተከታዩና ዐማራው የከፈሉት ዋጋ
- የኢትዮጵያ አንድነት ትንሣኤ፣ የዐማራው የአንድነትና የፀረ-አንድነት ትግል ውጤት
- ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ የፍፁማዊ ዘውዳዊ አገዛዝ የአንድነት ግንባታ ሂደት ድምድም እና የኢትዮጵያ ዳግም ብተና ጽንስ
- የለውጥ ፈላጊው ትውልድ የኃይል አሰላለፍ
- ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ከ1972 እስከ 2007 ዓም ድረስ በዐማራው ነገድ ላይ ያደረሰው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል
- ስለ ዐማራና ስለ ኢትዮጵያዊነት ምሑራን ምን ይላሉ?
- የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)፦ ዐማራው ላይ የደረሰው ሰቆቃ የወለደው ነፍስ አድን ድርጅት
- ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፦ የአሥራት ዘር ፍሬ
- ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መግለጫዎች በከፊል የሚሉ ናቸው።
የመጽሐፉ አቀራረብ ከዚህ በፊት በተለምዶ በገበያ ላይ ከሚውሉት ለየት ያለ ነው። በውስጥ ይዘቱም ከዚህ በፊት ለአንባቢዎች ቀርበው የማያውቁ ጥሬ መረጃዎች፣ ታሪካዊ ትንታኔ፣ እና ዋቢ መጻሕፍት ተካትተዋል። የቀረቡት መረጃዎች በሠንጠረዦች፣ በፎቶግራፎች እና በልዩ ልዩ ካርታዎች አባሪነት የተብራሩ ናቸው።
ይህንን መጽሐፍ በመግዛት እና በማንበብ ስለአገርዎ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ተጨማሪ ዕውቀት ያገኙበታል። በተለይም ዐማራው የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያዊነትን ኅልውና ለማስቀጠል ስለከፈለው እና አሁንም ስለሚከፍለው መስዋዕትነት ለመረዳት ያስችልዎታል።
መጽሐፉን እንዴት እና ከዬት መግዛት እንደሚቻል፦
መጽሐፉ ከማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ በገበያ ላይ ውሏል።
- በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ለሚኖሩ፦ በእናት ኢትዮጵያ ገበያ (ዲሲ)፣ በአስኒ ገበያ (ቨርጂኒያ)፣ በናዝሬት ባልትና (ቨርጂኒያ)፣ በእንጦጦ ገበያ (ዲሲ) እና በሌሎችም የኢትዮጵያውያን መደብሮች ያገኙታል።
- በመላው ዓለም ላሉት የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ኮሚቴዎች በቅርብ ቀናት ስለሚሠራጭ በየአካባቢው ካሉት የድርጅታችን አካሎች ተጠሪዎች መግዛት ይቻላል።
- በፖስታ ቤት እና በሌሎችም መንገዶች የሚሠራጭበትን መንገዶች በቅርቡ እናሳውቃለን።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
Leave a Reply