• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መርዓዊና መንታ መንገዳቸው!

September 10, 2013 07:15 am by Editor Leave a Comment

“መልካም መሥራትን ተማሩ፤ ፍርድን ፈልጉ፤ የተገፋውን አድኑ፤ ለድሃ አደጉ ፍረዱለት፤ ስለመበለቲቱም ተሟገቱ። ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር ፤ ኃጢያታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነፃዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ። እሽ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችሁዋለች፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሯልና።“ ትንቢተ ኢሳይያስ 1፣17-20

ውድ አንባብያን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። 2006 ዓ.ም በአገራችን ሰላም ፍቅርና አንድነት የሚሰፍንበት እንዲሆን ስመኝ ባለፉት ዓመታት የነበሩ ግድፈቶች በዓለማዊውም ይሁን በመንፈሳዊው ቤት ተነቅሰው የሚወገዱበትን መንገድ ማመቻቸትን ግን ግድ እንደሚለን በመጠቆም ነው። የእምነቱ ተከታዮች ስለሆንን ያየነውን እኛም ከመናገር ዝም ስለማንል ይህን ለማለት ተነሳሁ።

የዛሬው የጽሑፌ ቅኝት በቀድሞው የጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን “ ኃላፊ“ እና የኮሎኝ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በጀርመን የኮሎኝ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ብቻ ስለሆኑት ቀሲስ ዶክተር መርዓዊ ተበጀ አመራር ላይ ያጠነጥናል።

በእርግጥ ግለሰቡ በጀርመን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መሥራች መሆናቸውን ማንም አይክድም። ስለእሳቸው ውዳሴ ለማብዛት በእኔ ግምት እጅግ ከሚገባቸው በላይ “ውዳሴ መርዓዊና ቤተሰቡ” ወይም  ሰላማ በተባለው መጽሔታቸው “የ30 ኛ ዓመት ዝክረ ነገር” ላይ ተዘርዝሯል። ዝክረ ነገሩ መርዓዊን ከቅዱሱ ሙሴ ጋር ያመሳሰለበት በየዓረፍተ ነገሩም አቦ አቦ  እያሉ በሚያሞጓጉሳቸው ግለሰቦች ተዘጋጅተው በራሳቸው ታርመው ለንባብ መብቃታቸውን ለታዘበ እሳቸው መርዓዊን ሃይ የሚላቸው የለም እንዴ? ያስብላል። ጽሑፎቹ ለውዳሴ የተዘጋጁ ስለመሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም።

በመጽሔቱ ውስጥ ባለፉት 30 ዓመታት የነበሩ ችግሮችን ለማሳየት እንኳን አለመሞከሩና ጥሩ ጥሩውን ብቻ መርጦ መለጠፍ ተገቢ አይደለም።ችግሮቹ ሁሉ ፀሓይ የሞቃቸው የአደባባይ ሚስጥሮች ናቸውና።በእኔ እምነት ከአንድ ቄስ ይህ አይጠበቅም።ለሌሎች ሊቃውንትም እድሉን በመስጠት የሚያስተምር ፍሬ ነገር እንኳን እንዲካተት አልተደረገም። ቢያንስ በዚህ የ30 ዓመት ጉዞ አብረዋቸው የነበሩ አባቶችና ወንድሞችን እንኳን በመጽሔቱ ዝግጅት አላሳተፉም። ራስን ከፍ ከፍ ከማድረግ ውጭ። በአዘጋጅነት የተሳተፉት የጀርመን ድምፆቹ ሁለት ሴት ጋዜጠኞችም ያሉትን ችግሮች መርማሪያዊ በሆነው የጋዜጠኝነት ስርዓት ለሌሎች የሚሰነዝሯቸውን ምላሶቻቸውን በመርዓዊ ላይ ማጠፋቸው አስተዛዝቦናል። የሙያዊ ስነምግባርም አይደለም።ግድ የለም በሰዎች ፊት ከፍ ከፍ ማለት በፈጣሪ ፊት ዝቅ ዝቅ ማለትን እንደሚያስከትል የሚያስተምሩ ካህን ራሳቸውን ለመካብ ምነው ተጣደፉ ታዲያ? ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይላል የአገሬ ሰው።

የእሳቸው የመርዓዊ ዋነኛ ችግር አምባገነንነታቸው ነው።ከእኔ በላይ ማንም አያገባውም እናንተ ምንም አታውቁም ትናንት ነው የመጣችሁት ወዘተረፈ የተለመዱ ፉከራዎቻቸው ናቸው።ይህንን ደግሞ የሚያስተጋባላቸውና የሚተካቸው ሌላ አምባገነን ቄስም ከኑረንበርግ አካባቢ ብቅ ማለት ጀምረዋል።በካህናቱ ኔት ወርክ ዙሪያ ወደፊት የምመለስበት ይሆናል።

ነገር ግን በጀርመን -በቅርቡ ከጽዋ ማህበርነት ወደ ቤተክርስቲያንነት ያደገውን የካርልስሩኸ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያንን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት አገር ቤት ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር ከሚተዳደሩት አስራ አንድ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በቀድሞው የሙኒክ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ በፍራንክፈርት ቅድስት ማርያም በኮለኝ ሚካኤልና በስቱትጋርት አቡነ አረጋዊ አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ብክነት ዝርፊያ ሙስናና የአስተዳደር ችግሮች፤ በቪዝባደን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ከገንዘብ ብክነቱ በተጨማሪ ስር የሰደደ የኑፋቄ ትምህርትና የመሳሰሉት ነግሰው የሚገኙባቸው ናቸው።

እነዚህ ሁሉ ችግሮች ላለፉት 30 ዓመታት ሳስተዳድረው  ቆይቻለሁ ለሚሉት ለቀሲስ መርዓዊ ግድም አይላቸው። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው አለበትና። የአንዳቸውንም አብያተክርስቲያናት አስተዳደር ችግር ተሳስተው እንኳን የማያነሱት መርዓዊ  ከአንድ ወዳጃቸው ቄስ በይፋ እንደሰማሁት ምን ያለበት ዝላይ አይችልም አይነት አስተያየት ነው የሰጡት።

በውዳሴ ዝክረ ነገራቸው ቻሌንጅ የሚያደርጓቸው ሰዎች ላይ ጣት ከመሰንዘር ያለፈ ውስጣቸውን እንኳን ለማየት አልደፈሩም። አይሆንላቸውማ! ቀላል ምሳሌ መውሰድ ይቻላል ከዚህ ቀደም በወጣው ሰላማ ዝክረ ነገራቸው ላይ የኮሎኝ ቤተክርስቲያን በስጦታ የተገኘ እንደሆነ ገልፀው ነበር። አሁን ደግሞ ባለቤታቸው በጻፉት ጽሑፍ የወንጌላዊት ቤተክርሰቲያኑ ቄስ ቤታችን ድረስ መጥቶ ነው ቁልፉን ያስረከበን ይሉና ወረድ ብለው ደግሞ አሁን ቤተክርስቲያኑን ስለገዛነው ይላል። ቤተክርስቲያኑ በእውነት በግዢ ከሆነ የተገኘው ስንት ተገዛ? የተገዛበት ሰነድስ ለምን ለህዝብ አይገለፅም መደበቁ ለምን አስፈለገ? ለቤተክርስቲያን ተሟገትኩ ያሉባቸውን ደብዳቤዎች በዝክረ ነገራቸው ሲለጥፉ ምነው የሕንፃ ቤተክርስቲያኑ ግዢ ውል ስካን አልደረግም ብሎ አሻፈረኝ አለ እንዴ? ካለ ማለቴ ነው።

በተጨማሪም ላለፉት 30 ዓመታት በርካታ ገንዘብ በዶች ማርክና በኦይሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። አንድም ጊዜ ግን ኦዲት ተደርጎ አያውቅም ይሄስ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው። አቤት ደፋር መሪ መጥቶ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ኦዲት ይደረጉ ያለ ጊዜ የቀድሞው የሙኒክ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ የነበሩት የቀሲስ መስፍንን ጽዋ ችግር ያለባቸው ሁሉ ይጎነጩታል።

የሙኒኩ ችግርም ቢሆን እሳቸውን መርዓዊን ይመለከታል። ቀድሞ በሥራቸው የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት በአግባቡ መምራት አልቻሉምና። የቤተክርስቲያናችን ቃለ አዋዲ አንቀጽ 60 ቁጥር 2 ረ  “እያንዳንዱ ካህን በሕገ ቤተክርስቲያን መሰረት የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ጠብቆ የማስጠበቅ ቤተክርስቲያንን ከሚያስነቅፉ የነውር ሥራ ሁሉ መራቅ ግዴታው ነው።“ ይላል። ከአንቀጹ የምንረዳው እያንዳንዱ ካህን ሕገ ቤተክርስቲያንን የመጠበቅ ግዴታ ብቻ ሳይሆን ሌላው ሲያጠፋም የመከላከል ግዴታ እንዳለበት ነው።

ሳስተዳድረው ቆይቻለሁ በሚሉት ቤተክርስቲያን ይህን የመሰለ አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸም እንኳን ምእመናን ታግለው ጳጳስ ተጠርተው ውሳኔ እስኪሰጡ ድረስ ምንም አልተነፈሱም። ለምን? ፈረንጆቹ “if you scratch my back, I will scratch yours” የሚሉት ብሂል ስላለ ነው በግርድፍ ትርጉሙ “እከክልኝ ልከክልህ” አይነት መሆኑ ነው። ከማንም በፊት ችግሩን የሚያውቁት ቀሲስ መርዓዊ ምንም እርምጃ ያለመውሰዳቸው ከቤተክርስቲያኗ ሕግ በላይ ጓደኝነታቸው በልጦባቸው ይሆን?

በፍራንክፈርት፣ በሽቱትጋርትና፣ በቪዝባደን አብያተ ክርስቲያናት ላሉት አይን ያወጡ ችግሮችም እሳቸው ራሳቸውን ተጠያቂ ማድረግ አለባቸው። ናቸውም። ሙገሳ ሲሆን ቀድሞ መገኘት ወቀሳ ሲሆን ግን አይመለከተኝም ማለት ብልጣ ብልጥነት ነው። ይቅርታ ለመጠየቅ ሞት ሆኖ ለሚታያቸው አምባገነኑ ቄስ በተደጋጋሚ መድረኮች ሌሎች አባቶች ይቅርታ ሲሉ እንኳን ለምን አላችሁ ይቅርታ አያስፈልገውም በማለት የሚሞግቱ “ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ“ በሚለው ያረጀ ያፈጀ ባህል ለመጓዝ የሚሽቱ ሆነዋል።

በአጠቃላይ የእሳቸው አመራር በዘፈቀደ ወይም ሞክረህ ተሳሳት “Trial and error” የሚባለው ስልት ነው ትርጉሙ ደግሞ  “Trial and error- is a fundamental method of solving problems. It is characterised by repeated, varied attempts which are continued until success, or until the agent stops trying. It is an unsystematic method which does not employ insight, theory or organised methodology.” http://en.wikipedia.org/wiki/Trial_and_error

እሳቸው እኮ መርዓዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የማያውቀው በጀርመን ማግደቡርግ በ2007 እ.ፈ.አ የፕሮቴስታንትና የካቶሊክን ጨምሮ  ከ10 የክርስቲያን የእምነት ተቋማት ጋር በጥምቀትአንድ ነን ብለው ታሪክ የማይረሳው ስምምነት የፈረሙ እኮ ናቸው።ለዚህ እንኳን በይፋ ይቅርታ ጠይቀው ካደረጉት ስምምነት እስካሁን የቤተክርስቲያናችንን ስም አላስወጡም።

ቀሲስ መርዓዊ ጥብቅ ግንኙነት ማድረግ የማይሻቸውን በእምነት የሚመስሉንን እንደ ግብጽ ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያናትን ድጋፍ ሲያጣጥሉ እሳቸውን ጨምሮ ከአራት የማያንሱ አባቶች ደሞዝና ጥቅማጥቅም የሚያገኙት ግን ከጀርመን የወንጌላውያንና የካቶሊክ የእምነት ተቋማት ነው።ይሄ ለምን አያቅራቸውም?ራሳችንን እስክንችል ቤተክርስቲያናችን ድጋፍ ካስፈለጋት ምነው የግብጾቹስ ምን አደረገ?

ይሄ ደግሞ የሚያሳየው ሰርቻለሁ ብለው 109 ገጽ ውዳሴ ላዘጋጁት ቀሲስ “መርዓዊና የ30 ዓመታት የአመራር ችግሮቻቸው“ በሚል ሌላ ተጨማሪ የ3ኛ ዲግሪ ማሟያ ጽሑፍ ማዘጋጀት ያስችላሉ።

ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ቱባ ቱባ ችግሮች መልስ እንዳያገኙ መርዓዊን እጅ ተወርች ያሰራቸው ምንድን ነው ብትሉ? መልሱ የቆሙበት መንታ መንገድ ነው። ችግር ካለባቸው ካህናት ጋር ግጭት መፍጠር አይፈልጉም አዲሰ አበባ ከሚገኘው ሲኖዶስም ጋር የጠበቀ ግንኙነት ማድረግ አይሹም። በስደት ያሉትን አባቶችም ያሞጋግሳሉ ግን ልባቸው ወደነሱም ለመሄድ ግራ ተጋብታለች።

አንድ ቀላል ምሳሌ ለማየት እንችላለን።ዝክረ ነገር በሚል በወዳጆቻቸው ወንጌላውያን ተቋማት ድጋፍ በነፃ የሚያሳትሟት ባለቀለሟና የታተመችበትን ዋጋ የማያወጡ ውዳሴዎቿ ላይ እንኳን በስደት ወይም በአገር ቤት ያሉትን ፓትሪያርክ ፎቶ ከፊት ይዘው መውጣት ሲገባቸው የሁለቱንም አላወጡም። የራሳቸውን መልዕክት መክፈቻ አድርገው ውስጡም መዝጊያውም  የራሳቸው ውዳሴ ሆኖ እያንዳንዷን በ5 ዩሮ በመሸጥ ላይ ናቸው።

ከሁሉም ጋር (ከሁለቱም ሲኖዶሶች) ጋር አንድነት ወይም ልዩነት ሳይኖራቸው በመንታ መንገዱ ላይ መጓዛቸው በአንዱ በኩል በተለይ በአገር ቤት ከሚገኘው ሲኖዶስ የሆነ ችግር ቢመጣ ወደ ውጮቹ ለመጠጋት የዘየዱ ይመስላሉ።ይሄ ደግሞ በዘመኑ ቋንቋ መንታ አቋም ወይም Double standard ነው። በእኔ እምነት በስደት የሚገኙት አባቶችም ቢሆኑ በዚህኛው ሲኖዶስ በአስተዳደር በሙስናና በመሳሰሉት አስነዋሪ ተግባራት እርምጃ የተወሰደባቸው ካህናት ቋት አይሆኑም። በዛኛውም ችግር ያለባቸው በዚህኛው መሸሸግ አይችሉም።ስለዚህ ሁላችንም ከግል ስብዕናችን ይልቅ ለቤተክርስቲያን ሕግ እንገዛ።በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ያለውን ችግርም ወደፊት በስፋት የምመለስበት ይሆናል። ውድ አንባብያን ይህ ጽሑፍ የግል አስተያየቴ መሆኑን እንድትገነዘቡልኝ እሻለሁ።እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ!  ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule