አስራ ስድስት የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የተፈራረሙበት የተላዘበ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ልከዋል። ደብዳቤው ጋዜጠኛ፣ አሳታሚና ጸሃፊ እስክንድር ነጋ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ባስቸኳይ እንዲፈታ የሚጠይቅም የሚያሳስብም ነው።
ደብዳቤውን አስመልክቶ በዓለም ዙሪያ ላሉ የህሊና እስረኞች ጥብቅና የሚቆመው “የፍሪደም ናው” ነገረ ፈጅ ፓትሪክ ግሪፍተዝ ለቪኦኤ እንደተናገሩት እስክንድር ነጋ እንዲፈታ በመጠየቅ የተጀመረው ስራ እስክንድርን በማስፈታት እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል፡፡ እስክንድር ነጋ በየትኛውም መስፈርት ከሽብር ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ እንደሌለ ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል። ህጉ የጋዜጠኞችን አፍ ለማዘጋት የተፈበረከ መሆኑንም አስታውቀዋል።
አስራ ስድስቱ ፈራሚዎች በላኩት ደብዳቤ የእስክንድር ነጋን ቤት ለመውረስ ስለተጀመረው ሩጫ መረጃ እንዳላቸው አስታውሰው በለሰለሰ ቋንቋ አቶ ሃይለማርያም ያላቸውን ሃላፊነትና መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው እስክንድር እንዲፈታ አሳስበዋል። ከዚህ በፊት የእንግሊዝኛውን ዜና ባወጣን ጊዜ የአማርኛውን እንደምናስከትል በገለጽነው መሠረት የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ለሰነድነት ያገልግል ዘንድ የጎልጉል ሙሉ ትርጉም ይዘን ቀርበናል። ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
Leave a Reply