እስካሁን አልበገር ባለውና ከሁሉም በላይ ደግሞ ለህልውናው የተማመነበት የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካው በህዝቦች ወንድማማችነት መንፈስ ከሽፎበት ብርክ በብርክ የሆነው የወያኔ አገዛዝ ከአንድ አመት በላይ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ሲያወርድ የቆየውን አመጽ ቀጥሏል፡፡ በያዝነው ሳምንት በሰላም የኢሬቻ ባህላዊ በአላቸውን በሚያከብሩ ኦሮሞዎችና ሌሎች በአሉን ለማክበር በስፍራው በተገኙ ሌሎች ዜጎች ላይ እስካሁን ከታዩት ግፎች ይበልጥ ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ አካሂዷል፡፡ በዚህ አሰቃቂ ግፍ በመቶ የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት አልፏል፡፡ በሽ የሚቆጠሩ እናት አባቶች ልጆቻቸውን፣ ጨቅላ ህጻናትና ታዳጊዎች እናት አባቶቻቸውን፣ ወንድም እህቱን እህት ወንድሟን አጥተው ለአስከፊ ሰቆቃ ተዳርገዋል፡፡ ድርጅታችን ይህንን አሰቃቂ ድርጊት በጥብቅ እያወገዘ ለተሰውት ወገኖች ዘመዶችና ወዳጆች መጽናናትን ይመኛል፡፡
ይህ ስርአት እስከቀጠለ ድረስ ይህ አይነቱ ግፍም አብሮ ይቀጥላል፡፡ ግን ደግሞ ከአንድ አመት ወዲህ እንደምናየው ህዝባችን የተያያዘው ትግል እየሰፋና እየተጠናከረ ይሄዳል እንጂ የወያኔ መሪዎች እንደሚመኙት ከእንግዲህ በምንም አይነት አፈና የሚበርድ አይሆንም፡፡ የወያኔ መሪዎች ልብ አላሉትም እንጂ ዛሬ የሃገራችን ህዝብ ባለበት የምሬት ደረጃ በጭፍን አመጽ ምክንያት ትጥቁን እንደማይፈታና እንዲያውም ከሚፈጸምበት ግፍ ጋር ቁጣውና አልበገር ባይነቱ እየጨመረ እንደሚሄድ ያለፈው አመት የትግል ሂደት በግልጽ አሳይቷቸው ነበር፡፡ ዛሬም በኢሬቻው ጭፍጨፋ ማግስት የሚታየውም ይኸው ነው፡፡ ድርጊቱ ከዚህ ስርአት ከእንግዲህ ምንም አይጠበቅ በሚል ስሜት እልህ የተጨመረበት ህዝባዊ ትግል አነሳስቷል፡፡ እንግዲህ ጥያቄው ይህ ተጋድሎ እንዴት ቀጥሎና ይህ የግፍ አገዛዝ ተወግዶ ዴሞክራሲያዊና ተጠያቂነት የሰፈነባት አገር እንመስርት የሚለው ነው፡፡ (ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply