• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በማወቅና በማድረግ እውነትን መኖር?

January 3, 2017 01:54 am by Editor 3 Comments

የሕይወትን እውነትና ትክክለኛ ትርጉም ተረድተን በሰላምና በፍቅር ለመኖር የሚያስችል የአእምሮ መታደስ ለማድረግ የሚከተለውን ላካፍላችሁ፡

ከሁሉ አስቀድሜ ልረሳው የማልችለውን መልካም ባህላችንን ተጠቅሜ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን እላለሁ፤ እኔም ከሃገር፣ ከቤተሰብ፣ ከዘመድና ከጓደኛ ተለይቼ ባህሉንና ወጉን ጠንቅቄ ከማላውቀው ሕዝብ ጋር በእኛ አቆጣጠር ባለፈው ታሕሳስ 16 ቀን 2009 ዓ/ም የፈረንጆችን የገና በአል አክብሬ አሁን ደግሞ የእኛን ታሕሳስ 29 ቀን 2009 ላይ ከኢትዮጵያውያንና ከኤርትራውያን ወገኖቼ ጋር ለማክበር በዝግጅት ላይ ነኝ፤ እዚህ ላይ የቀን ልዩነት ቢኖርም የመከበሩ ዋና ዓላማና የቀኑ ባለቤት የሆነው ግን አንድ ነው፤ እሱም ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው በመሆን በሰው ልጆች መካከል በመመላለስ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ለማለት ድፍረት እንዲሆነን “አማኑኤል” የተባለው ጌታ ኢየሱስ ነው።

ዛሬ ይችን አጭር መልእክት ጽፌ እንድልክ ያነሳሳኝ ዋና ጉዳይ በተለያየ ሚዲያ ሁላችንም እንዳየነው በዚህ የፈረንጆች ክሪስመስ አከባበር ላይ ሰፊ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ስጦታን እርስበርስ መቀባበል እንጂ የበአሉ ዋና ባለቤት በሆነው ላይ አለመሆኑ አስገርሞኝ ነው፤ በእኛ አገርም ሁሉም እንደ አቅሙ ድፎ ዳቦው፣ ቆሎው፣ ዶሮው፣ በጉ፣ ቅርጫው፣ ጠላው፣ ጠጁ፥ አረቄው ከገና ጨዋታውና ከዘፈኑ ጋር አይቀርበትም፤ ይህን ሳስብ ታዲያ ምንም እንኳን ይህን በመሰለና መጠኑን በጠበቀ መልኩ በአግባቡ ደስ መሰኘቱ ባይከፋም እንደ ባለ አእምሮ ሰው ቆም በማለት የሚከተሉትን ሦስት የሕይወት ጥያቄዎች በማስተዋልና ትኩረት በመስጠት አብረን እንድናያቸው ወደድኩ፡-

1) ይህ በታላቅ ፌስታ የምናከብረው የልደት በዓል በእውነት ባምሳሉ ለክብሩ ለፈጠረው የአዳም ዘር በሙሉ ፋይዳው ምንድር ነው??? የሚለው ወሳኝ የህይወት ጥያቄ ዋናውና የመጀመሪያው ይሆናል ማለት ነው።

መልሱን የሚነግረን በዘላለም ፍቅሩና ምህረቱ ይህንኑ ሥራ የሠራልን ፈጣሪ አምላክ በህያው ቃሉ እንጂ ሰው በራሱ ሊመልስ ይቅርና የሚናገረውንና የሚጠቅመውን እንኳ የሚያውቅ አይመስለኝም፤ ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔርም (በሉቃስ 2፡10-11) ላይ “እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና’’ ይለናል።

ይህን ቃል ለትምህርታችን ዘርዘር በማድረግ አብረን በትእግስት እስቲ እንየው፡- ለሕዝቡ ሁሉ ስላለ ሁላችንንም ይመለከተናል፤ ታላቅ ደስታ በመባሉ ደግሞ ጊዜያዊ የሆነው ሰው ሠራሽ ምድራዊ ደስታ ከሰማይ በመላእክት በኩል የመጣውን ደስታ ፈጽሞ አይተካውም ፤ በአጠቃላይ ከሰማናቸውና ከምንሰማቸው በላይ የሆነና የምሥራች ተብሎ የተነገረ፣ በሚያስፈራ በሽታም ሆነ በሌላ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ብንሆን ፍርሃታችንን አስወግዶ ደፋር የሚያደርገንና ፍጹም ፈዋሽ የሆነ የማያዳግም መድሐኒት ከሴቶች መካከል የተባረከች ከተባለች ከድንግል ማርያም ክርስቶስ ብቻ ሳይሆን ጌታና አማኑኤል የሆነ ለእኛ እንደተወለደልን ማስተዋልና የመለኮትን የመድሃኒትነት ስጦታ በቃሉ እንደተነገረን ትእዛዝ/Prescription/ ተቀብለን ሰዎች ከሚሰጡን ጊዜያዊ ስጦታ ባለፈ መልኩ መጠቀም መቻል ብልህነትና አስተዋይነት ይመስለኛል፤ ሕይወት ጅማሬ ብቻ ሳይሆን መጨረሻም አለውና።

እስቲ እዚህ ላይ ስጦታን በተመለከተ ይህን ልበልና ላጠቃል፣ አንድ የሚወደን ሰው ፍቅሩን ለመግለጽ በውድ ዋጋ ገዝቶ በሰርጋችን እለት በብዙ ሕዝብ ፊት ሲሰጠን አልቀበል ብንለው ምን ይሰማው ይሆን? ታዲያ በዮሐንስ ወንጌል 3፡16 ላይ እንደተጠቀሰው በሃጢአት ምክንያት ለሞተው የሰው ዘር በሙሉ ውድ አንድ ልጁን በመድኒትነት የሰጠውን የምህረት አምላክን ስጦታ አልቀበል ብንል ማነው የሚጎዳው? ሰጪው ደስ ብሎት ሲሰጥ ተቀባዩ ገብቶት በመቀበል ካልተጠቀመበት ሰጪውን እስከነስጦታው መናቅ አይሆንብንምን?ደግሞስ ለዚህ ሰሞኑን ለምናከብረው በዓል ምክንያት ስለሆነው ሰማያዊ ስጦታ ሰጪው እንድንመራበት በሰጠን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ፡ አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ሰውን ሁሉ ስለመውደዱ /ዮሐ 3፡16/ ለገዛ ልጁ ሳይራራ ስለ ሁላችን በደል አሳልፎ የሰጠው /ሮሜ 8፡32/ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገለጠ….ወዘተ ለሚለው ህያው ቃል እያንዳንዳችን በግል ምን ዓይነት መልስ ይኖረን ይሆን???

2) ሌላው የሕይወት ትክክለኛ ትርጉም በእውነት ምንድር ነው? የሚለው ይሆናል፤ ምናልባት መልሱ፡- መብላት መጠጣት፣ ንብረት ማካበት፣ ማግባትና ልጅ መውለድ፣ እድሜ ጠግቦ ጉዞን መጨረስ ይሆን ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ መልካም ናቸው፤ ነገር ግን ሁሉም ጊዜያዊና ጠፊ በመሆናቸው ብል ሳይበላው ከሞት ባሻገር አብሮ የሚሻገር የዘላለም ርስታችንን በዚች በተበላሸች ምድር እያለን ካላረጋገጥን እጅግ የሚያሳዝን መንፈሳዊ የሕይወት ክስረት ነው የሚሆነውና አሁንም እናስተውል::

3) ጌታ ኢየሱስ በምድር አስተምሮው ላይ ስም ሰጥቶ የሃይማኖት ድርጅት በመመስረት የዚህ ሃይማኖት ተከታይ ካልሆናችሁ መንግሥተ ሰማይ አትገቡብ አላለም፤ ነገር ግን በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ይድናል/ዮሐ 10፡9/፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም /ዮሐ 14፡6/፤ ልጅም ትወልዳለች እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል /ማቴ 1።21/፤ ልጁ ያለው ሕይወት አለው የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም /1ኛ ዮሐ 5፡12/፤ በአጠቃላይ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ድረስ ያሉት መጽሐፍት የሚናገሩት የምህረት አምላክ የሆነው ቸሩ እግዚአብሔር በኃጢአት ምክንያት ከኤደን ገነት የወጣውን የአዳም ዘር በልጁ ሞትና ትንሳኤ መልሶ ማስገባቱን ነው፤ ወንድም ወንድሙን አያድንምና /መዝ 49፡7/ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድሃኒት አመጣለት /ኢሳ 59፡16/ ስለሚል ባለንበት ሃይማኖት ውስጥ በመሆን መጽሐፍ ቅዱስን ትኩረት ሰጥተን ለማጥናት ቀኑ ሳይመሽ አሁኑኑ እንድንጀምር በእግዚአብሔር ፍቅር ከልቤ አሳስባለሁ፤

ትናንት ላናገኘው አልፏል፤ ነገም የእኛ መሆኑን አናውቅም፤ ዛሬ ግን እንድንጠቀምበት የተሰጠን የእድሜያችን እንቁ ሃብት ነውና ብልህና አስተዋይ እንሁን።

ቸሩ በቸርነቱ ይርዳን!!!

አሜን።
እውነቱ ይነገር ነኝ (eunethiwot@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. ጎይቶም says

    January 12, 2017 12:43 am at 12:43 am

    እውነት ነው፤ እኛ ሁላችን ልናስብበት የሚገባና ቆም ብለን በማሰብ ድካማችንን በማስወገድ እውነተኛ ማንነታችንን በፍቅርና በሰላም አብረን ለመኖር ብልህ ሰዎች እንሁን!

    Reply
  2. Tadesse says

    January 30, 2017 07:14 pm at 7:14 pm

    Agree and liked it very much.

    Reply
  3. Mulugeta Andargie says

    February 3, 2017 07:46 am at 7:46 am

    Guys!!! Politics has no truth as mathematics has. It is human philosophy. Otherwise, our theory would be metaphysics. It will not be materialistic. Don’t expect from any politician truth.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule