ከቅኝ አገዛዝና ከሰብዓዊ መብት ረገጣ በሰላማዊ ትግል ‘ሰላም’ አግኝተዋል የሚባሉት አገሮች ሕንድ፤ አሜሪካና ደቡብ አፍሪካ ይመስሉኛል። የነዚሃን አገሮች ተመክሮ ወስደን፤ እነሱ በሄዱበት መንገድ ሄደን እንሱ ያገኙትን ሰላምና ነፃነት እናገኛለን ማለት ዘበት ይመስላል።
ከላይ በተጠቀሱት አገሮች የተደረገው ትግል ‘ከሰለጠነ’ ጠላት ጋር ነው። በጥቂቱም ቢሆን የሕግ የበላይነት ነበር። ለነፃነቱ የታገለው ሕዝብ በዘር፤ በቋንቋ፤ በቀለም፤ በሐይማኖት.. ወዘተ ቢለያይም አንድ-ወጥ የሆነ ራዕይ ነበረው። ያም ሆኖ የደቡብ አፍሪካው ANC አስፈላጊ የመሰለውን መንገድ ሁሉ የተጠቀመ ይመስለኛል። ሰላማዊ የሚባለው የትግል ዓይነት ሁልጊዜ ሰላማዊ መቋጫ ላይኖረውም ይችላል። ሕንድን ከእርስ በርስ ጦርነትና ከመገነጣጠል አላዳናትም።
ለነገሩ አገራችን የገጠማት ችግር ከማንም ጋር የሚመሳሰል አይደለም። መፍትሄውም እንደዚያው አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤ ግን ከጥቃት ራስን መከላከል የተፈጥሮ ሕግ ነው።
ወያኔ ትናንት የሞተለት ዓላማ ነበረው፤ ዛሬ ደግሞ የሚሞትለት ሐብትና ንብረት አለው። በነ ስብሐት ነጋ ጭንቅላት ፈርሳ የተሠራች ኢትዮጵያን አያሳየን። አሜን!!
ተው ስማኝ አገሬ (ቁጥር አንድ)
ይሄ ‘ነፃ ትግል’ የምትሉት ነገር
ለማንም አልበጀ ከወያኔ በቀር
ሰው እየተገፋ
አገር እየጠፋ
አርባ ዓመት አምሣ ዓመት ‘በነፃ’ ታግላችሁ
ምንድን ለመሆን ነው አገር ከሌላችሁ?
በለው ! says
*****************************
ወያኔ ትናንት የሞተለት ዓላማ ነበረው፤
ዛሬ ደግሞ የሚሞትለት ሐብትና ንብረት አለው!!
ይቺ ናት ጨዋታ በለው! አዎን..
ትናንትማ ሲያታልለው
ወንድምህ ሊበላህ ነው አለው
እኔ ባልኖር ምንም አልነበረክም ብሎ ሰበከው
እኔ ከሌለሁ ትበታተናለህ ብሎ አተራመሰው
እራሱ እየገደለው ገዳይህን አወጣለሁ ሲለው
አፉን ከፍቶ እንባውን አዥጎደጎደው
ደረቱን ሲደቃ ገዳዩ አርጂው ሆነው
አሳዘነው ቁጭ ብሎ ጠጣ በልቶ አባላው
ሃይማኖት ቋንቋ ዘር ባሕሉን በረዘው
ስኳር እያላሠ በራዕይ ሆዱን ቆዘረው
የተማረ ይግደለኝ ብሎ ነበርና ሰማው
መሬቱን ሸጦ ጎበዝ ብሎ ወረቀት ሸለመው
የሁለት ትውልድን አኮላሽ ወኔውን ሰለበው ።
—–
እነኛማ እውነተኛ ታጋዮች ደከማቸው
ያልበረቱም አጥንታቸው ለአውሬ ለአሞራ ቀረ ሥጋቸው
ለእራሳቸውም አልሆኑ ለሀገርም ለቤተሰባቸው
እነርሱ ሞተው ጥቂቶችን ማበልጸጋቸው
ኣረ ለመሆኑ ምንኛ የዋሆች ናቸው ? ?
እንኳን ሀገር የቀብር ቦታ ላይተርፋቸው
ለምን ነበር የገዛ ወገናቸውን መግደላቸው ?
የሞተ ተጎዳ ሆዳም ሀብት አፈራ በደማቸው
አርባ ዓመት አምሣ ዓመት ‘በነፃ’ ሞታችሁ!!።
*******************
ተው ስማ በለው!! ከሀገረ ካናዳ