አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ አገዛዝ (የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ሕ.ወ.ሃ.ት.) ከ25 ዓመታት በፊት የመንግሥት በትረ ሥልጣንን እንደ ፈረኦን ከጨበጠ ማግሥት አንስቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቀዳሚ ዒላማው በማድረግ የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ተጥሶ መንበሩ ላይ የተቀመጠ ፓትሪያርክ በህይወት እያለ ያለውን ከመንበሩ በማባረርና በማሳደድ በምትኩ ከራሱ ጎሳ መርጦ ፖትሪያርክ አድርጎ ሾመ።
ይህ የፖትሪያርክ ሹመት ቀኖናን ቤተ ክርስቲያንን ከመጣስ ባለፈ ፖለቲካዊና ከፖለቲካም የከፋው የዘረኝነት ፖለቲካን (ethnocratic politics) የተከተለ ስለነበር በተቀረው የአገዛዝዙ የዘረኛ መንግሥታዊ መዋቅሮች እንደረደረገው ሁሉ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥም የዘረኝነት መዋቅር እያደገ ሄዶ ለወደፊት ቤተ ክርስቲያኗንም ሆነ አጠቃላይ ሃገሪቱን ለከፋ አደጋ ያጋልጣል በሚል አብያተ ክርስትያናትም ሆኑ በርካታ መንፈሳዊ አባቶችና ምእመናን እርምጃውን በጽኑ ተቃውመውት ነበር። (ሙሉውን ጽሁግ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply