ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም። ስለዚህ ነገሬን አጠር አድርጌ ላቅርብ። እነሆ!
የኢትዮጵያ ማንነት መገለጫው በዋነኛነት ምንድነው?
- ሕዝቡ ነው።
ታዲያ በሕዝቡ ስም (ኢትዮጵያ) ጥላ ስር መሪዎቻችን ሁሉ የማይሰባሰቡት ለምንድነው?
- የታሪክ እስረኛ ሆነን በር በሌለው ጨለማ እስር ቤት ውስጥ በመታለል ቁጭ ስላልን።
- ኢትዮጵያን መነሻ ሳናደርግ ኢትዮጵያ መድረሻ እንድትሆንልን ተመኝተን ጉም ስንጨብጥ።
- ክልላችንን (አጥሩን) አፍርሰን እንዳንያያዝ አጥሩ ጎልያድ ሆኖብን ፍርሀት ስለሞላብን።
ሁሉም የሚስማማበት ጉዳይ ምንድነው?
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ የጭቆና ሰለባ ሆኗል።
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ደግና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ነው።
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ የተደባለቀና አብሮ ለዘመናት የኖረ ነው።
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ተባብሮ ታግሎ መንግስታትን ጥሏል።
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ተባብሮ ለጥቁር ሕዝብ ኩራት ሆኗል።
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ አንድነታቸውን ዛሬም እያንፀባረቁ ነው።
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉም ብሔረሰብ ሰብሳቢ ያጣ ቤተሰብ ሆኖ ተቸግሯል።
ሁሉም የሚገርመው የመሪዎች አባዜ ምንድነው?
- መንግስት ከፋፍሎ ይገዛል። ስልጣኑ ጥሞታል።
- ተቃዋሚ ተከፋፍሎ ይታገላል። ለስልጣን ቋምጧል።
የሚገርመው እውነታ ምንድነው?
- እግዚአብሔር በተአምራቱ እስካሁን ብቻውን አንድነቷን እየጠበቀ ነው።
- የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን በራሱ እያስተዳደረ ነው።
እግዚአብሔር አዲስን ነገር የሚያደርግበት ዘመን ሲመጣ የሚሆነው ምንድነው?
- ልጆቿ አጥርን እያፈረሱ ይያያዛሉ።
- ምህረትና ፍትህ ይሳሳማሉ።
- ቁርሾ በፍቅር ይሟሟል።
- እውነት በእውን ይሰምራል።
- አሮጌውን ክፉ ታሪክ የሚያስረሳ አዲስ ታሪክ ይሰራል።
- ልትሞት ነው የተባለችው ኢትዮጵያ በትንሳኤ ትነሳለች።
- የኢትዮጵያ እናትነት እንደ ንጋት ጮራ ብርሃኗ ይወጣል።
I am not Ethiopian first.
I am not Ethiopian second.
I am Ethiopian.
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
የኢሜል አድራሻ፦ ethioFamily@outlook.com
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply