• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፕሮፌሠር ፍቅሬን ለቀቅ ቧልትህን ጠበቅ

February 23, 2017 04:17 am by Editor 7 Comments

ሰሞኑን በፕሮፌሠር ፍቅሬ ስራዎች ለማሾፍ እና የእርሳቸውን ክብር ለማውረድ በጅምላ እየተካሄደ የሚገኝ የስም ማጥፋት ስራ እየተመለከትኩኝ ነው አንዳንዶቹ ባለማወቅ እና ከብስለት ማነስ የሚያደርጉት መሆኑን ባውቅም የተወሰኑት ግን ሆን ብለው የሚፈፅሙት ተግባር መሆኑን ለማወቅ ችያለው፡፡ በፕሮፌሰሩ ላይ እየተካሄደ የሚገኘው የማንቋሸሽ ተግባር ከየት እንደመነጨ ለምን እንደሚካሄድና እነማን እንደሚፈፅሙት መመልከቱ መልካም ይመስለኛል፡፡

ፕሮፌሠር ፍቅሬ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2008 ዓ.ም ለንባብ ያበቁት የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ትክክለኛ የዘር ምንጭ የተሰኘው መፅሐፍ ለገበያ ከዋለ በኋላ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እጅግ ተፈላጊ መፅሐፍ በመሆን መነበብ የቻለ ትልቅ መፅሐፍ ነው በዚህም በኢትዮጵያ የመፅሀፍ ታሪክ ውስጥ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ በተደጋጋሚ በመታተም ታሪክ የሰራ መፅሀፍ ነው፡፡ ይህ መፅሀፍ የኦሮሞውና የአማራው ህዝብ ሌሎች ፀሐፊያን እንደሚሉት የተለያየ ዘር ያላቸው ከተለያዩ ሀገራት ፈልሰው ወደኢትዮጵያ መጡ የሚለውን የታሪክ ፀሀፊዎቹን የዘመናት አስተሳሰብ የሠበረ ለዚህም ማስረጃ ያቀረበ መፅሐፍ በመሆኑ እኔ ብቻ ነኝ የማውቅልህ የሚሉ የታሪክ ፀሀፊያንን ስራዎች አፈር በመክተቱ ምክንያት የታሪክ ፀሀፊዎች ስህተታቸውን ከመቀበል ይልቅ ፕሮፌሠር ፍቅሬን በተለያዩ መንገዶች ማጥቃት እንዲጀምሩ ምክነያት ሆኗል፡፡

በአንድ ወቅት ይህ መፅሀፍ ከመታተሙ በፊት ፕሮፌሰር መስፍን ስለፕሮፌሠር ፍቅሬ ሲገልፁ የኢትዮጵያን ታሪክ መፃፍ ያለበት ፍቅሬ ቶሎሳ ነው ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ፕሮፌሠር መስፍን ትክክል ነበሩ ምክንያቱም ፕሮፌሠር ፍቅሬ ከጎሳ አስተሳሰብ ነፃ የወጣ ሙሉ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ የኢትዮጵያን ታሪክ ካለምንም ወገንተኝነት እንደሚፅፈው እሙን ነበር፡፡ ይህ ግን እራሳቸውን ከጎሳ አስተሳሰብ ነፃ ማውጣት ላልቻሉ የሀገራችን ምሁራን ተቀባይነት አልነበረውም ምክንያቱም ለበርካታ አመታት ህዝቡን ለመነጣጠል የፃፉት ፀረ አንድነት የታሪክ ፅሁፎች አፈር እንደሚገቡ ያውቁታልና በዚህም የተነሳ እነዚህ ከፕሮፌሰር ፍቅሬ የኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ጋር በተቃራኒ የቆሙ ወገኖች አንድ ንብረትነቱ የኤፈርት የሆነ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የሚገኝ የቴሌቪዥን መድረክ መሪ በመጠቀም ፕሮፌሠሩን ለማሸማቀቅ ሞከሩ ለተወሰነ ጊዜ የተሳካ ቢመስልም ፕሮፌሠር ፍቅሬ ከቆይታ በኋላ በለቀቋቸው ፅሁፎች ማንበብና ማገናዘብ የሚችለውን በመረጃ ማሳመን ሲጀምሩ የተወሰኑ ምሁራን አሁንም የጥላቻ የመሰለ ትችታቸውን መፃፋቸውን ቀጠሉ፡፡ ሆኖም ፕሮፌሠር ፍቅሬ በቀና ልቦና የመጨረሻ መልሴ ያሉትን ምሁራዊ መልስ ሠጡበት፡፡ ከዚህ በላይ ምንም ማድረግ ያልቻሉት የፕሮፌሰር ፍቅሬ ሀሳብ ያሸማቀቃቸው ፀሀፊያን ከመፅሀፉ ትችት ወደፕሮፌሠር ፍቅሬ ግጥሞች ዞሩ፡፡

ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት የፕሮፌሠር ፍቅሬ መፅሀፍ ያልናደው የታሪክ ውሸት ያልሰባበረው የታሪክ ስንክሳር የለም፡፡ ይህ ደግሞ በባዶ ሜዳ ላስቀራቸው የታሪክ አዋቂ ነን ባዮች ትልቅ ኪሳራ ነበረ፤ ይህንን የእውቀት ኪሳራ መቀበል ያቃታቸው ፀሀፊያን ሌሎች መረጃዎችን በማሰባሰብ ሌላ ተጨማሪ ነገር ይዞ ከመቅረብ ይልቅ በቀጥታ የፕሮፌሰሩን መፅሐፍ በዛ የቴሌቪዥን መድረክ መሪ አማካኝነት ተረት ተረት ነው ለማለት ደፈሩ፡፡ በዚህ የፕሮፌሰር ፍቅሬ መፅሐፍ ተቃዋሚ ጎራ ውስጥ ከእድሜ ጠገብ ምሁራን እና ፀሀፊያን ጀምሮ እስከተራ የፌስቡክ ፀሀፊያን ድረስ የሚገኙበት ነው፡፡ በመሠረቱ የፕሮፌሠር ፍቅሬ መፅሀፍ መተቸት የለበትም የምል አይነት ግለሰብ አይደለሁም፡፡ በጣም የወደድኳቸው ትችቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ ወዳጄ እያስፔድ ተስፋዬ የግሪክ ፀሐፊያንን ፅሁፎች በመጥቀስ ጥሩ ሊባል የሚችል የበሠለ ትችት አቅርቦ ነበረ በዚህም ከፕሮፌሠር ፍቅሬ ጋር ተገናኝተው ለሰዓታት የቆየ ውይይት አድርገው መስማማት ችለዋል፡፡ የሌሎቹ ግን ከጥራዝ ነጠቅነትና ከጥላቻ እንዲሁም ከአልሸነፍም ባይነት የመነጨ ነበረ ነውም፡፡

ታሪክ የተሻለ ማስረጃ በተገኘ ቁጥር የሚሻሻል ምሁራዊ እርምት የሚሠጥበት የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት አንድ አካል በመሆኑ ሌሎች የተሻለ ማስረጃ ይዘው በሚቀርቡ ጊዜ የፕሮፌሰር ፍቅሬ መፅሐፍ ሊሻሻል የሚችል ነው፡፡ እስከዚያው ድረስ አሁን ባለን የታሪክ ፅሁፍ ደረጃ የፕሮፌሰር ፍቅሬን መፅሐፍ ከመቀበል ውጭ ሌሎች አማራጮች አልቀረቡልንም፡፡ ከዚህ ቀደም ግሩም ዘለቀ እንዳለው የፕሮፌሠር ፍቅሬ መፅሐፍ ትልቅ ስህተት በኢትዮጵያዊ ምሁር መፃፉ ነው፡፡ ለዘመናት ፈረንጆች የፃፉልንን የተንሸዋረረ የታሪክ መፅሀፍ ስናነብ ለኖርን እና ፈረንጅን እንደመለአክ ለምንመለከት ሰዎች የፕሮፌሰር ፍቅሬን መፅሐፍ አዕምሯችን ሊቀበልልን አልቻለም፡፡

ይህ በጊዜ ሁኔታ ሊቀየር እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ጋሽ ፍቅሬ ኢትዮጵያውያንን በአንድ ማዕዘን አሰባስቦ ሊያኖር የሚችል ትልቅ መሰረት በአንድ መፅሐፍ አሰቅምጦልን ታሪክ ሰርቷል ይህንንም በአካል ተገናኝተን አጫውቼዋለሁ ሌሎቻችንም ክብር ልንሠጠው ይገባል፡፡ ይህንን የአንድነት ማዕዘን የሆነ መፅሀፍ የመጠበቅ የሁላችንም የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የምንል ወገኖች ሃላፊነት ነው በተረፈ የፕሮፌሰርን ግጥሞች ስለተቸን ገጣሚ ነን ብለን የምናስብ የታሪክ መፅሀፉን ተረት ተረት ነው ስላልን ታሪክ ፀሀፊ ነን የምንል ካለን አእምሯችንን መፃፍ ብቻ ሳይሆን ማንበብም ልናስተምረው ይገባል፡፡

እንደዚህ አይነቱን ለኢትዮጵያ መልካም አስተሳሰብ ያለውን ቅን ምሁር ለማዋረድ መሞከሩ መልካም አይመስለኝም፤ ልብ ወለድ ፀሀፊዎቹም ፕሮፌሰሩን ለቀቅ በማድረግ የቧልት ፅሁፋችሁን ጠበቅ ብታደርጉት አእምሯችሁ በማታውቁት ነገር ከመወጠር የሚያርፍ ይመሰልኛል፡፡

(ኤርሚያስ ቶኩማ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. ክፍሌ says

    February 25, 2017 05:32 pm at 5:32 pm

    ውድ ጎልጉል፣
    ይሁነው አሰፋ የተሰኘ “የፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን መፀሐፍ የምትተቹና የምትቃወሙ ኢትዮጵያን ባለማወቅ፣ ከቅናትና ምቀኝነት በተነሳ ሃሰት ነው” ብሎ ዝቶ ነበር [ኢትዮሊንክ፣ 1/4/17]። የታሪክ ምሑሩን ፕሮፌሰር ጳውሎስ ሚልክያስንና ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን “…የሰነዘራችሁት አስተያየት እጅግ በጣም ዝቅ ያለ ትምህርታዊ ተመክሮን፣ክብርና ማዕረግን ያልተከተለ ሥነ-ምግባርና ፕሮፌሽናሊዝምን ያጓደለ … አሉባልታና ተራ ነቀፌታ፣ ቅናትና ተንኰልን የሚያንጸባርቅ …” ብሎአል። የይሁነው ችግር፣ ስለ ምርምርና “ፕሮፌሽናሊዝም” ብዙ አለማወቁ ነው። መረጃ ሳያቀርብ መሳደብ “ፕሮፌሽናሊዝም” ነው? “ከ45-63 ቢብሊወግራፎች” ስለ ቀረበ ብቻ መረጃውን ትክክል ያደርገዋል? ዶ/ር ምትኩን “ከተገንጣዎች ወገን የሆነ የሚናገረውና ሊያስተላልፈው የሚፈልገው የወያኔን ፀረ- ኢትዮጵያ አቋም የያዘ” ሲል ከሷል። መረጃ ግን የለውም። ሦስቱን ግለሰቦችና ያካሄዱትን ጥናቶች አያውቅም። አይገርምም? ኤርምያስ ቶኩማ ደግሞ “ፕሮፌሠር ፍቅሬን ለቀቅ ቧልትህን ጠበቅ” ብሎናል። ከይሁነው ጋር ተመሳሳይ አሳብ ያዘለ ነው። መረጃ አያስፈልገንም፣ ዝም ብላችሁ ተቀበሉ ነው።

    ይሁነውና ኤርምያስ ወደፊት እንዳንገሰግስ ያገዱንን መሠረታዊ ችግሮቻችንን ያንጸባርቃሉ። ዓላማቸው ያልደገፋቸውን ሁሉ በስድብ ናዳ ማስወገድ ነው። ያልተጠየቀ ስህተት ሲቀባበል እውነት ተብሎ ይወሰዳል። እዚያው መዳከር ነው። ይባስ ወደ ኋላ መሄድ ነው። የድረ ገጽ አዘጋጆች ከስድብና ስም ከማጥፋት ውጭ መረጃ የሌላቸው ጽሑፎች የድረገጻቸውን አቋም እንደማያንጸባርቁ ለአንባቢው መግለጽ አለባቸው።

    አንባቢው፣ የይሁነውንና የኤርምያስን ጽሑፍ ካነበበ በኋላ የጠቀስኩትን የሦስቱን ምሑራን ጽሑፍ እያስተያየ ያንብብ።

    Reply
    • Editor says

      February 26, 2017 09:27 am at 9:27 am

      ቢችሉ የጽሁፎቹን link እዚሁ ላይ ቢያሰፍሯቸው መልካም ነው

      አርታኢው

      Reply
      • kifle says

        February 26, 2017 09:41 pm at 9:41 pm

        http://www.satenaw.com/amharic/archives/28947
        http://www.ethiomedia.com/1000codes/7955.html
        http://www.ethiomedia.com/1000codes/ewnetegnaw-yezer-minch.pdf
        በነገራችን ላይ፣ ስም ማጥፋት በአሜሪካ [libel] ያስከስሳል።

        Reply
        • Editor says

          February 26, 2017 11:40 pm at 11:40 pm

          kifle

          ምስጋናችን ይድረስዎ

          ከጎልጉል

          Reply
  2. Getachew says

    March 3, 2017 02:54 am at 2:54 am

    I read the links.
    I think Golgul and wherever Yehun’s and Ermias’s
    articles are published should be taken down.
    Yehun surely has language problem.
    Pls correct me if I am wrong.

    Reply
  3. Mulugeta Andargie says

    March 6, 2017 01:50 am at 1:50 am

    Guys!!! The Oromo people will write his own history whenever they get time. Fikre Tolossa is not an Oromo, he is from Guragie tribe; I don’t think he knows more about their history; I really have a doubt!!!

    Reply
    • Kebede says

      March 6, 2017 05:16 pm at 5:16 pm

      Dr. Fikre says he is Oromo. You say he is Guragie? This must be the joke of the year. You must be Tigre. The Tplf type. You “don’t think he know about their history?” By “their” you mean the Oromo? What is your history? You admitted you are not Oromo; so what right do you have to comment on someone’s knowledge? Mulugeta, Are you still at Foreign Affairs? I thought you had moved to Peace and Security.

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule