• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በውኑ መንፈስ ይታሰራልን?

August 10, 2013 11:47 pm by Editor 2 Comments

እንደ ህወሃት አይነት አምባገነን መንግስታት ከተጠናወታቸው በርካታ ችግሮች መካከል ትግል እና ታጋይን ነጣጥሎ ያለማየት ችግር ሲሆን የትግል መሰረቱ ፍትህ እስከሆነ ድረስ፣የትግል መዳረሻው በተፈጥሮ የተገኘን መብት በችሮታ ካልሰጠናችሁ ከሚሉ አምባገነኖች መዳፍ ፈልቅቆ ለማውጣት እስከሆነ ድረስ በእርግጥም ይህ ትግል ከስጋና ከደም በላይ የተሻገረ በብዙሃን ላይ የሚሰርፅ መንፈስ ነው።ስለሆነም እንደመንፈስ የረቀቀው ትግል በታጋዩ ላይ ገዝፎ ይገለጥ ይሆናል እንጂ ታጋዩ ቢሰዋ አልያም በአምባገነኖች የግዞት እስር ቢወረወር ትግሉ አይታሰርም ደግሞም አይሞትም።

ለምሳሌ ፀረ-አፓርታይድ ትግል ማጠንጠኛው ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን መሻት እንዲሁም የዘረኝነትን ክፉ ቀንበር መሰባበር ነበር።

ነገር ግን በወቅቱ የነበሩ የዘረኛው አፓርታይዳዊ አገዛዝ አመራሮች የትግሉን ረቂቅ ወጣቶችንና አዛውንቶችን ለእስርና ለሞት ከመዳረጋቸው ባሻገር የትግሉን መሪ ኔልሰን ማንዴላን በሮበን ደሴት ላይ ለ27 ዓመታት ሊያስሩ ችለዋል።ይሁን እንጂ የትግሉ መንፈስ ፍትህና ነፃነትን የሚፈልጉትን ሁሉ ኮርኩሮ የመቀስቀስ አቅም ስለነበረው ፀረ-አፓርታይድ ፍልሚያው እንደ ሰደድ እሳት ከያቅጣጫው ይንቀለቀል ነበር።ይልቁንም ታጋዮችን በመስበር ትግሉን እናከስማለን የሚሉትን አምባገነኖች የትግሉ ወላፈን እየበላቸው ዛሬ ከመጥፎ ተሞክሯቸው ጋር ታሪክ ሆነው ቀርተዋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተከሰተ ያለው ሁኔታ ከዚህ ብዙም የሚርቅ አይደለም።ታጋዮችን ላነሳሳቸው የህዝብ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ በግለሰቦች ላይ የሚደረገው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ቢመጣም የትግሉ እቶን ይበልጥ ከመንደድ ወደኋላ አላለም።ሠርካለም ፋሲል በግፍ በወህኒ እንድትወልድ መደረጉ እነ ርዕዮት አለሙን ከጋዜጠኝነት አላሸሻቸውም፥ይልቁን ስለእውነት እና ፍትህ በመቆም ለብዙ ወጣቶች አርአያ በመሆን የወያኔን የግፍ ፅዋ በወኔ ተጎነጨችው እንጂ።እስክንድር ነጋን በግፍ በህፃን ልጁ ፊት በካቴና በማሰር ወደ ወህኒ ሲጋዝ፣በውርስ ያገኘውን የእናቱን ቤት መንግስት ሲወርሰው በርግጥም በወያኔ ሹማምንት ስሌት ”እስክንድርን ያየ ይቀጣ” በሚል የህዝብ የነፃነት ጥያቄ በፍርሃት ካባ ተሸፍኖ ይቀራል ከሚል የመነጨ ነበር።

በቀለ ገርባን በማሠር፣ባለቤቱን በግፍ ከሥራ በማፈናቀል የተተኪው ትውልድ አካል የሆኑ ህፃናት ልጆቹን ለችግር  በማጋለጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የነፃነት ጥያቄ ማፈን አይቻልም።ይልቁን ዛሬ የትግሉ መንፈስ አድማስን ተሻግሮ የነፃነት ጩኸታችንን በአውሮፓ እና በአሜሪካ መንግስታት ተወካዮች ሳይቀር እየተስተጋባ ይገኛል።በቅርቡ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ  የሰብዓዊ መብት ኮሚቴ አባላት በጀርመናዊቷ ባርባራ ሎክቢለር በመመራት ወደ አዲስ አበባ ያቀና ሲሆን በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት አያያዝ አሳሳቢ መሆኑን የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ሁኔታ ለማየት ወደ ቃሊቲ እንዲሄዱ ከተደረገ በኋላ በተለመደው የወያኔ ድራማ ከስፍራው ያለ ውጤት እንዲመለሱ ተደርጓል።

በአንድ ነገር ይበልጥ እርግጠኞች ነን፦እልፎች በወያኔ ግዞት በግፍ ሊጣሉ ይችላሉ፣ አዕላፍት ሊሰው ይችላሉ። ነገር ግን የትግላችን መሠረት የሆነው የነፃነት፣የእኩልነት፣የፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል፣የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና የፖለቲካዊ ፍትህ ጥያቄያችን ግን ፈፅሞ በግዞት በቃሊቲና መሰል ወኅኒዎች ሊታሠር አይችልም። (ፎቶ: በጸሃፊው የተላከ)

ጸሃፊው በዚህ አድራሻ ይገኛሉ: beyenemesfin77@yahoo.com

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    August 12, 2013 12:22 am at 12:22 am

    የኢትዮፕያን ሪቪው አታሚ ኤልያስ ክፍሌ እንዴት እዚህ ውስጥ ተገኘ?

    Reply
    • abiti says

      August 12, 2013 11:33 am at 11:33 am

      (ፎቶ: በጸሃፊው የተላከ)

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule