ምን ማለት ነው እሱ ወዳጀ፤ ይሄ ሕገ ወጥ ስደተኛ
ወዶ የሚሰደድ ከሌለ፤ ከሀገሩ የሚርቅ መከረኛ
ነፍሱን ለማትረፍ የሻ ሰው፤ ይሸሻል እንጅ ባመራው
እንግዳ አይደለ ወይ ጎብኚ፤ ፈቃድ ጠይቆ የሚገባው
እስኪ ንገረኝ እባክህ፤ ለእናንተው መሐመድ ሰዎች
ተቸግረው ለተሰደዱት፤ ከሀገራቸው ላለመሆን ሟች
ቪዛ ተመቶላቸው ነበረ? ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ?
አሳልፋቹህ ስጡን ብለው፤ በጠላት ለሰይፍ ሲታሰቡ
ውሰዷቸው ተብለው ነበር? ወይስ ቤዛ ሆነ እርግቡ?
ውጡልን ተብለውስ ነበር? ፊቱን ነስቷቸው ሕዝቡ?
አንተ ግን ውለታ ቢሱ፤ አምላክ የማታውቅ የማትፈራ
የነፍስ ብለው የተጠጉትን፤ ለማምለጥ ከአጋንንት ጭፍራ
እያረድክ ፈነገልካቸው፤ ደፍረህ አርክሰህ በጠራራ
ይሄ ነው ላንተ ጽድቅ ማለት፤ ደም ጠጥቶ መስከር ግፍ ሥራ
ከሰይፍህ የተረፉትን፤ ደክሞህ ሰልችቶህ መተራ
እያነክ አስረከብካቸው፤ ለግዞት ሞት ለመከራ
አምላክን የፈራ ማለት፤ ለሰብአዊነትም ያደረ
ምርጫ ያጣን መርዳት እንጅ፤ ድጋፍን መስጠት ለተቸገረ
ያለውን መቀበል አይደለም፤ ለሥጋዊ ጥቅም እየመከረ
በሥጋ ገበያው ገብቶ፤ ካዝና የሚሞላን እየጨመረ
በለው! says
*********************
ለነገሩማ በደጁ የሚጮህ ውሻ ደም የጠማው
ጀግናው ሲያሸልብ እኪሱ የሚገባው
ድንቄም ሀብታም አረብ ጅብ በለው!
ቀን የጣለውን መንግስት ያበረረውን አገኘው
መሸሻ ሲያጣ ሲያውቅ ኢትዮጵያዊውን ውሻ አለው።
የጥንቱን ታሪክ የቁራኑን ምስክርነት የካደው
የነብዩን መሀመድ አደራ የበላው ውሻስ እርሱ ነው
በውሻ ልብ ቅቤ በአረብ ልብ ስብዕና አላደረም
ምን ቢቀላ ቀለማቸው ለካስ ቆሳሻ ነው ውስጣቸው
ቢያቅራሩም በሃይማኖት ላካስ ባዶ ኖረዋል በእምነት!
ማንነቱን ያልተናገረ በሀገሩ ሰንደቅ ተማምኖባት
አልጣላትም ጨርቅ ብሎ ተንጋለለ እራሱ ላይ አጊጦባት
የማያቋት የናቋት ይማሩ እነኛ ባንዳ ከሀዲዎች
የሀገሩ ሰንደቅ የቋሚም ምስክር መለያም ናት ለሟች
እባካችሁ እናንት አስመሳይ ሆድአደር አድርባዮች
ብሔርተኞች ጎጠኞች አሸባሪ ከፋፋዮች ዘረኞች
ሰንደቅ በአንድንት የሁሉም ናት ስደተኛ የሞተባት!!
የጀግኖቻችን ደም ፈሶ አጥንት ተከስክሶ መልሰው ያነሷት
አታርክሷት ለክፉ ሰው አጉል ቦታ አትቅበሯት ::
***************በለው!