• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መለሰ ዜናዊ ናፈቁኝ – የለቅሶ አየር ሰዓት አማረኝ

March 30, 2015 06:18 am by Editor Leave a Comment

ሰላም ወገኖቼ!! ተጠፋፋን። ግን አንለያይም። ድሮ የዘፈን ምርጫ ክፍለ ጊዜ ነበር። እሁድ እሁድ ወታደሮች ከደጀን፣ እናትና አባት፣ ቤተሰብ ከቤት ሆነው ይኮሞክሙት ነበር። አሁን ግን ለምን ተከለከለ? ባድመ፣ ሽራሮ፣ ዛላምበሳ፣ ገመሃሎ፣ ላከ ኤርትራም አሉ፤ ዘላበድኩ መሰለኝ … ብቻ የዘፈን ምርጫ ክፍለ ጊዜው ትዝ ብሎኝ ነው። ቀጭኑ ዘ-ቄራ ነኝ!!

“የለቅሶ ማስተላለፊያ የአየር ሰዓት/ክፍለ ጊዜ ቢጀመር ጥሩ ነው። ምርጫውን ያደምቀዋል” የሚል አስተያየት ሟርተኞች ያቀርባሉ። ግን ምን አለበት የከፋቸው ቢያለቅሱ። በየጓዳው እያለቀሱ ነው። አደባባይ ወጥተው ቢያለቅሱ ምን ነውር አለው? ለመለስ ደረት እየተመታ ሲለቀስ የአየር ሰዓት ተፈቅዶ የለ? ለሞተ ሰው ከተፈቀደ በህይወት ላለው፣ ግብር ለማያጓድለው ለምን ይከለካል? ወይስ ነዋሪው በሟች ተበልጧል?

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲባል የመለስ ለቅሶ በጊነስ ቡክ አለመመዝገቡ አያስገርምም። አማራ ደረት ሲደቃ፣ ደቡብ በዜማ ሲናባ፣ ትግሬ በለቅሶ ሲያዜም፣ ኦሮሞ እንባውን “ያ አባ ኮ” እያለ ሲያንዘቀዥቅ፣ ማን ቀረ? ሃይሌ ገ/ስላሴ ሲቃ ይዞት የእንባ “ቫት” ሲገብር … ድፍን አገር ሃዘን ሰብሮት፣ መሪው በድንገት እንደ ቡሽ ተስፈንጥረው ሲሄዱበት፣ ራዕያቸው ሲተንበት፣ ህልማቸው እንደ ጉም በድንገት ሲበተነበት፣ ጉሮሮው በድንገት ሲዘጋበት፣ ኑሮ ወደ ጎዳና ተዳዳሪነት ሲለወጥ፣ “የመጪው ጊዜ ብሩህነት” ሲደበዝዝ፣ እንዴት አያነባ? ጎበዝ ለመለሰ ዜናዊ ማን ያላነባ አለ?

መለስ አማረረን ብለው የተሰደዱ፣ በስደት ካምፕ የመለስን ፎቶ ሰቅለው ለቅሶ ተቀምጠዋል። ጠጅ ቤት፣ ጫት ቤት፣ … ምርጫ ሲመጣ ቀጭኑን ያመዋል። ምርጫ የግል ነው። የምርጫ ሰሞን ወሬ ለቃሚዎች ሲሳይ ይሆንላቸዋል። እገሌ ይህን አለ እያሉ በጀት ያስጨምራሉ። ወሬ ለመልቀም ይከንፋሉ። በየጫት ቤቱ ይራወጣሉ። ተናግሮ ማናገርና መልቀም። ጓደኞቻቸውን ማስበላት። አሳልፎ መስጠት። በህወሃት የባህር መዝገብ ማስመዝገብ።

OLYMPUS DIGITAL CAMERAአቶ መለስ አፈር አይክበዳቸውና (ለነገሩ አፈር ውስጥ አልገቡም) 99.6 በመቶ ምርጫን በማሸነፍ “ታሪክ መሰራቱን” ሲያበስሩ 96 በመቶ እንዲያሸንፉ ያደረጓቸው ወዳጆቻቸው ፊት ሰክረው ነበር። አራዳው መለስ በደስታ ቢሰክሩም መስታወት ቤት ውስጥ ሆነው መናገርን ግን አይረሱትም። ደስታ እየደቃቸው መስታዋት ቤት ውስጥ ሆነው “ኮራሁባችሁ” ሲሉ ከሲኤምሲ በ200 አውቶቡሶች ተጭነው መስቀል አደባባይ የደረሱ የኮብል ድንጋይ አንጣፊዎች አጨበጨቡ። በፉጨት አስተጋቡ። መለስ ደስታቸውን ሳያጣጥሙ ሾለኩ … ከመስታወት ቤት ወደ ግራውንድ ሲቀነስ ወረዱ። እዛ ወከባ የለም። ጭብጨባና ፉጨት የለም። ራዕይ፣ ቅዠት፣ “ሌጋሲ”፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ ህዳሴ፣ ኪራይ ሰብሳቢ፣ ኒዎሊበራል፣ ምናምን የለም። የዘላለም እረፍት … ቀጭኑ እንባ ባይረጭም ሃዘን ገባው።

የዜናዊ ልጅ ምነው ሞትን ሞተው በነበር? ቀጭኑ ጠየቀ። ሞት ያለ ሳይመስላቸው እንዲሁ በትዕቢት ማማ ላይ እንዳሉ ኮበለሉ። ቢያንስ ህዝብ የመምረጥና የመሻር ወሳኝ ሃይል እንዳለው አይተውና አሳይተው ቢነጉዱ ኖሮ እስከዛሬ ባነባን ነበር – ለነገሩ አይተዋል ማሳየት አቃታቸው እንጂ። ቀጭኑ መለስን የሚወቅሰው በዚህ ነው። ነጻ ትውልድ እንዲፈጠር አድርገው ቢያልፉስ ምን ነበር? የሚገርመው አሁንም ትምህርት የሚወስድ የለም። አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ኦቦ ሃይለማርያም ማለቴ ነው። ከ96 ወደ 100 በመቶ ለማሳደግና ሲሞቱ ደቡብ ሱዳን፣ ፑንትላንድ፣ ሩዋንዳና ኡጋንዳ የዘለቀ ሃዘን እንዲታወጅላቸው የሚተጉ ይመስላሉ። ሃይሌ ዕዳቸው ብዙ ነው፤ ለነገሩ የአገር መሪዎች ባለብዙ ዕዳ ናቸው፤ የሃይሌ ግን የበዛ ይመስለኛል፤ የራዕዩ፣ የሕዳሴው፣ የውዳሴው፣ የሌጋሲው፣ … ኧረ ስንቱ?! ራዕያቸውን፣ ሌጋሲያቸውን፣ … ተግባራዊ እናደርጋለን፤ እያሉ ስለ መለስ እንደሚናገሩት አንድ ቀን “ሞታቸውንም ተግባራዊ እናደርገዋለን” ብለው ንግግር ቢያደርጉስ? ለነገሩ ምን ይተገበራል? ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን ህያዋን የሆንን? ወደ ጉዳዬ ልመለስ …meles in box1

“እኒህ ፖለቲከኞች ነፍስ የላቸውም እንዴ” ስትል ማይሟ እናቴ ሁሌም ትጠይቃለች። ደግ ስራ ሰርቶና ተወድዶ መሞት ለምን እንደማይወዱ አይገባትም። ለመለስ ለቅሶ አልሄደችም። ለዚህ ነው መሰል የቀበሌው ሊቀመንበር አሁን ድረስ ይገላምጣታል። በነገራችን ላይ ያንዱ ቀበሌ ሊቀመንበር ባልደረባዬ ነበር። የመለስን ለቅሶ ቀበሌ ድንኳን አስተክሎ ሲያከናውን ወደ ጓሮ እየጠራሁ ጫት አጎርሰው ነበር። ድንገት ስናወራ “ለመለስ ለቅሶ ከልብህ አላዘንክም፣ መልፈስፈስ አሳይተሃል፣ ቁርጠኝነት አይታይብህም፤ …” ተብሎ መገምገሙንና 40 ሳይደግስ መሰናበቱን ነግሮኛል። አይ ግም-ገማ!!

አሁን ማን ይሙት እነዚያ ጎንደር ላይ አበል ከፍለው ደሃውን ሲያላቅሱትና በግምገማ ደረት ሲያስመቷቸው የነበሩት ሴቶች መለስን ያውቋቸዋል? ጋምቤላ አኙዋክ ምድር ለመለስ የሚያነባ ሰው ይገኛል? ፊልም የሚሰራ ደፋር ጠፋ እንጂ ከዚህ በላይ ምን ፊልም አለ? ኤርትራ ቤተ መንግስት ውስጥ አንድ ክፍል በድብቅ ሃዘን ተካሂዶ ነበር ብሎ የፈተለ ሰው አጋጥሞኛል። የኤርትራ ባንዲራ ዝቅ ስለማለቱ ግን መረጃ የለውም። የስምዖን ልጅ ሲሽቀነጠር እናያዋለን።

ባገራችን ምርጫ ያለ ፈቃድ ማልቀስና ደረት መምታት ነው። ባገራችን ምርጫ የራስ ሳይሆን የሌሎችን ምርጫ ማጽደቅ ነው። ባገራችን ምርጫ የራስን መብት ለሌሎች በህጋዊ ሰነድ ስም ማስረከብ ነው። ምርጫ!! በወሳኝ ጉዳዮች ላይ ምርጫ ብሎ ነገር የለም። አለመስማማት ተፈጥሯዊ ነው። አለመቀበልና አለመስማማት ግላዊ ነው። ልዩነት ያለ፣ የነበረ፣ የሚኖር እውነት ነው። ምርጫ በነዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ይገኛል። ከዚህ ውጪ ያለ የጫና ምርጫ የሰውን ልጅ አሻንጉሊት አድርጎ የማሳነስ ያህል ነው። የሰው ልጅ ክቡር ነው። ምርጫውን ያውቃል። ግን የእኛን አገር አይመለከትም።

ምርጫ በመጣ ቁጥር አየሩ ሁሉ ይከረፋል። ምርጫ በመጣ ቁጥር የህወሃትና ኢህአዴግ እብደት ይገንናል። እነሱ ሰማይና ምድሩን አፍነው የፈጣሪ ያህል የሆኑ ይመስላቸዋል። ቅጠሉና ዛፉ እንኳ አይታመንም። ወይ አንደኛውኑ ምርጫውን ቢዘጉት አይሻልም? ቀጭኑ ይህንን ሃሳብ ያቀርባል። ምርጫ የሚኖረው ምርጫና የመምርጥ መብት ሲከበር ነው። አስመራጩ ባንዳ፣ አስፈጻሚው ባንዳ፣ የበላዩ ባንዳ፣ የበታቹ ተላላኪ፣ መቃወም፣ መተንፈስ፣ ማስተማር፣ መናገር፣ መዝለፍ፣ ማጋለጥ፣ ነጻ ሚዲያ፣ ነጻ የመጫወቻ ሜዳ ሳይኖር ምርጫ? ይቀፍፋል። መቼ እንደምንሰለጥን አይታወቅም። ሁሉም ጋር ችግር አለ። የዜናዊ ልጅ ግን ናፍቀውኛል። መልካም ነገር አስተምረውን አለፉ፣ ተፈተለኩ፣ ተነቀሉ፣ ተደለቱ፣ አሁንም ለሳቸው ማልቀስ የሚፈልጉ አሉ። የማልቀሻ የአየር ሰዓት ይፈቀድ ብለው የሚጠይቁ አሉ። ለመለስ የለቅሶ ምርጫ ክፍለ ጊዜ ይመደብልን። ከየብሔሩ እያፈራረቅን መስማት የምንፈልግ ቧልተኞችም አለን። ቀጭኑ የምርጫ እድል ቢሰጠው “ያ አባ ኮ” በሚል የኦሮሞ አርሶ አደሮች ያነቡበትን ለቅሶ ቀዳሚ ክሊፕ አድርጎ ይመርጠዋል። ከዚያም “ሰለሜ ሰለሜ” የሚለውን በለቅሶኛ ያስከትላል። ቸር እንሰንብት!! ቀጭኑ ዘ-ቄራ!!


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule