አርነት ! _ የጥቁር ምድር አርማ ፤
ልዕልና ! _ የጥቁር ክብር ማማ፤
የጥቁር ደም – የጥቁር ዘር፤
የጥቁር ብቃይ – ከጥቁር አፈር፤
አንደበት !_ የፍሰሃ ቃል፤
ፋና ወጊ !_ የጥቁር ቀንዲል፤
አብሳሪ !_ የጥቁርን ልዕልና – የጥቁርን ድል ፤
ምንጭ ! _ የሰው ልጅ ዘር ግኝት፤
ማህተም ! _ የጥቁር ሕዝብ ዕሴት፤
ማተብ ! _ የሰው ልጆች ዕምነት፤
የክርስቲያን፤ የእስላሙ፤ _ የይሁዲው ቤት፤
ኢትዮጵያዊ ነኝ ! _ ነፃነተ ዖሪት ::
ቀሪውን የአሥራደው ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
Leave a Reply