ገጣሚና ደራሲ…
ከግዑዙ መሬት፣ ከመንደሩ ይልቅ ከዘር ማንዘሩ፣
ሰብዓዊነትን ያልማል ብዕሩ
“የሰው ልጅ ልብ…” ነው አገሩና ድንበሩ!
ሰብዓዊነት ነው ክብሩ፤
ገጣሚ አገር የለውም፣
“ዩኒቨርሱ”ም አይበቃውም፤
ሰዋዊ ህመም ያመዋል፣
ፈውሱም ይፈውሰዋል፣
ገጣሚ ያ ይበቃዋል!
ወርዶ ወርዶ “ቀየ መንደር ውስጥ አይወድቅም”
አዎ! ገጣሚ፣ ደራሲ እንዲያውም አገር የለውም፣
የበዓሉ አገሩ ሰው ነው፣
“…ህንጻው ምን ቢረዝም፣ ምን ቢጸዳ ቤቱ፣
መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ፣
ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ፣
የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር፣
የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ድንበር…” (ኦሮማይ)
ጸጋዬም ጊንጪ ኢምንት ቢሆንበት
ጉደር፣ አምቦ፣ ቡራዩ … ጠ’ቦበት፣
አዲሳ’ባ ኢትዮጵያም ብታንስበት፣
ብዕሩ ፈርዖኦንን ተመኘ፣
ነፈርቲቲ እና አፍሮዳይትን ቃኘ፣
ገጣሚ አገር የለውም፤
“ዩኒቨርስ”ም አይበቃውም!
ደራሲ እና ገጣሚ እንዲህ ጠ‘ቦ አይጠብም፣
ከቶ አገር የለውም…..
ወለላዬ ግሩም ብሏል ይመስለኛል፣
“አለ ሙያቸው ሙያ እየጫንባቸው…”
መዝገቡ ሊበን – ከሚነሶታ (segeldigest@gmail.com)
Ezira says
እዉነት ነው እዉነት ብለኃል – መዝገቡ ሊበን እንዳለው ፣
ሁላችንም ባለን መረዳት – ሁላችንም እንደምናውቀው፣
የገጣሚና ሠዓሊ ሁሉ – ማደጊያውና መኖሪያው
ጎሽ! እደግ ተመንደግ ተብሎ – መደነቂያና መወደሻው፣
መኖሪያውና መቀበሪያው – ትልቁና ሰፊው አገሩ
በእያንዳንዱ ሰው ልብ እንጅ አልነበረም በመንደሩ።