• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሀዋሳ የጦርነት አውድማ አልሆነችም

July 19, 2019 10:09 am by Editor 2 Comments

በተነሳው ተቃውሞና ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው አሉ

የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ለዛሬ ለማወጅ መቀጠሩን ተከትሎ በሐዋሳ እና አካባቢዋ ግጭት ተቃውሞ መከሰቱ ተገለፀ ። ከዚህ ጋር ተያይዞ ከተማዋ የጦርነት አውድማ እንደሆነች ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚወራው ሐሰት መሆኑ ተነገረ ።

የጥያቄ አራማጆች ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደገለፁት የሲዳማ ሽማግሌዎች እና ወጣት የጉዳዩ አቀንቃኞች ዛሬ ጠዋት ሊያካሂዱት ያቀዱት ስብሰባ አካባቢውን በዘጉት በፀጥታ ኃይሎች ተደናቅፏል። ባለሥልጣናት ወደዚያ ባለመምጣታቸው፤ እና ወደ መሰብሰቢያው ስፍራም እንዳያልፉ ያገዷቸው የፀጥታ ኃይሎች ላይ ወጣቶቹ ድንጋይ መወርወራቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

ሐዋሳ ከተማ ላይ በቁጣ ወደ ጎዳና የወጡት ዜጎች ጎማ በማቃጠል ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭትም ቢያንስ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱን ሌሎች ደግሞ መጎዳታቸውን የሆስፒታል ምንጮች ለዶይቼ ቬለ «DW» ገልጸዋል።

የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ሳርሚሶ ጭንቅላቱን በጥይት መመታቱ የተገለፀው ተጎጂ ወደ ሐኪም ቤት ከሄደ በኋላ ሕይወቱን ማጣቱን ለሐዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ገልጸዋል።

«መጀመሪያ ላይ ትንሽ ጭንቅላቱ ላይ የቆሰለ ሰው ገብቷል። እሱ የመጀመሪያ ርዳታ ሰጥተን ወደ ቤቱ ሄዷል። ከዚያ ቀጥሎም ደግሞ አንድ ሴት ነበረች የመጣችው። ባጠቃላይ አራት ወንድ እና አንድ ሴት ነበር የመጡት። አንደኛው ከአዳሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመጣ ከዚያ ሪፈር የተደረገ ሰው ነበረ ጭንቅላቱ ላይ ነበር ቆስሎ የነበረው፤ ቁስሉ አሁን ሀኪሞች እንዳረጋገጡት በጥይት የተመታ ይመስላል። ከፍተኛ የሆነ ቁስል ነው። እሱ አዳሬም ወደ እኛ እንደላከ እኛ ጋርም ብዙ ሳይቆይ ሊያርፍ ችሏል።»

ሌሎቹ ተጎጂዎችን በተመለከተ የሚታየው እስካሁን ለከፋ አደጋ የሚያደርስ እንዳልሆነም አክለው ገልጸዋል። ግጭት ተቃውሞው በሐዋሳ ከተማ የተወሰነ እንዳልሆነ ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ተገቢውን ምላሽ ካላገኙ ዛሬ ማለትም ሐምሌ 11 ቀን 2011ዓ,ም የሲዳማን ክልልነት ለማወጅ መዘጋጀታቸውን የጉዳዩ ጠያቂዎች ሲያሳስቡ መሰንበታቸው ይታወቃል።

ሐዋሳ ከተማ ሐሙስ ዕለት

ሐሙስ ከቀትር በፊት የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ሲአን የሲዳማ ተወላጆች እንዲረጋጉ አሳስቦ ነበር። የሲአን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደስላኝ ሜሳ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄውን ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ ለማድረግ እንዲቻል ቅድመ ዝግጅት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ለዶቼ ቨለ «DW» አረጋግጠዋል። እንዲያም ሆኖ እስካሁን አካባቢው ስለመረጋጋቱ የተሰማ ነገር የለም።

በሌላ በኩል ሀዋሳ ከተማ የጦርነት_አውድማ እንደሆነች ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሠራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው። በዚህ ፈታኝ ወቅት ሀገሪቱን ወደማያባራ ግጭት ውስጥ እድትገባ ፅኑ ፍላጎት ያላቸው የፌስቡክ አርበኞች በመኖራቸው የምንሰማቸውን መረጃዎች በደንብ ልናጣራ እና ልንመረምራቸው ይገባል በማለት ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያና ተናግረዋል። ግጭቱ ከተነሳ ጀምሮ እስካሁን በሲዳማ ዞን እና ዙሪያው በሚገኙ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ነው።

©DW

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    July 19, 2019 10:37 pm at 10:37 pm

    ህወሓት 24 ሰኣት በጀሌዎቹ አገር ውስጥና ከአገር ውጭ የጥፋት ወሬ እያሠራጨ ነው። እነርሱ በፈጸሙት ደባና ሌብነት ዶ/ር ዐቢይን እየወነጀሉት ነው። በአዋሳ፣ በአሦሳ፣ በአማራ በሚካሄደው ሁሉ እጃቸው አለበት፡፡ የሌባ ዐይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ ነው! በምን ተኣምር ነው ዶ/ር ዐቢይ በ1ኣመት ተኩል እነርሱ 27 ኣመት ሲመዘብሩ ዜጋ ላይ ግፍ ሲፈጽሙ የኖሩትን ማቃናት የሚችለው? ይገርማል እኮ! አገር ሁሉ ህወሓትን አይቀበልም አይፈልግም። የሚነዙትን ውሸት ማጋለጥ የያንዳንዳችን ሓላፊነት ነው። ለነገሩ ውዥንብር ይንዙ እንጂ አይሳካላቸውም!! ይህን እነርሱም አውቀውታል! ትልቁ የህወሓት ችግር የትግራይን ሕዝብ እንዴት አፍኖ እንደሚይዝ ነው። አንደኛው ብልሃት በዜና ማሠራጫቸው 24 ሰኣት ወሬ መንዛት ነው። ሌላኛው የጋራ ጠላት መጠፍጠፍ ነው። ሳያስቡ ያደረጉት አንድ መውደቂያቸው ጄኔራል ሰዐረን ትግራይ ወስዶ መቅበር ነው። የሰዐረ ቀብር ፈንጂ ሆኖ ይበትናቸዋል!

    Reply
  2. Segel gazeta says

    July 20, 2019 10:51 am at 10:51 am

    ህወሃት ራሱ ገድሎ፡ «ገደሉት…» ብሎ አስወርቶ፡ አብሮህ ሃዘን የሚቀመጥ ቡድን ነው፡፡ እንዲያም ቢሂን ግን አብይም ቢሆን በርካታና አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ድጋፍ የሚያስገኝለትን እርምጃ መውሰድ አልቻለም፡፡ አንድ አመት ቀላል አይደለም፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule