
“ዋሸሁ እንዴ?” (ነን ሶቤ) ሲል ይጠይቃል፣ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ። ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው ለታዳሚው ሕዝብ አይደለም። በአስር ሺዎች የታደሙበት የኮንሰርት አዳራሽ ውስጥ ከታዳሚው ፊት-ለፊት ለተቀመጡት ለእነ አባዱላ ገመዳ፣ ወይንም ደግሞ ለእነ ለማ መገርሳ ይመስላል። ከፍ ሲል ደግሞ ኮንሰርቱን በቀጥታ ስርጭት እየተከታተሉ ላሉት የአድዋ ባለ ግዜዎች የቀረበ ጥያቄ ነው።
ይህ ድምጸ-መረዋ ወጣት በምርጥ ቅላፄው ያንጎራጎረው ፉከራ እና ዜማ እጅግ ያስደምማል። ማስደመሙ እውነትን በመድረክ ላይ መዘርገፉ አይደለም። ከራሱ ደህንነት ይልቅ የወገኑን ስቃይ እና ሰቆቃ በማስቀደሙ ነው። እንዲህ አይነቱ እውነትን አደባባይ ወጥቶ በድፍረት የመናገር “ገት” የነበረው ቴዲ አፍሮ ነበር። ይህንን በማድረጉም በአንባገነኖቹ ጥርስ ውስጥ ገብቶ ብዙ ቢያስከፍለውም፣ ከህዝብ ልብ ውስጥ ሊወጣ አልቻለም።
በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ፣ ትላንት ምሽት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የኦሮሞ ሙዚቀኞች ማህበር ባተዘጋጀው “ወገን ለወገን” ኮንሰርት ላይ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ መድረኩን ጠቆጣጥሮት ነበር። የሕዝቡን ስሜት እየኮረኮረ፣ ብሶቱን በአደባባይ ዘርግፎታል። ጠንከር ባሉ ቃላት የተቃኘው ስንኝ ከውብ ድምጽና ቀስቃሽ ዜማ ጋር ታጅቦ ሲቀርብ ልዩ ስሜትን ፈጥሮ ነበር። ይህ ዜማ በቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ በአዳራሹ የነበረው ድባብ እጅግ ይደንቃል። ሃጫሉ ይጠይቃል፣ ታዳሚው ስሜቱን በጩኸት ይገልጻል። ኦሮምኛ ባልችልና የሚለውን ነገር ባልረዳ ኖሮ ይጸጽተኝ ነበር። ይህ ወጣት ድምጻዊ መድረኩን ተቆጣጥሮ ይዞ እንዲህ ይል ነበር፤
Geerar geerar naan jettuu
Dhiirri geeraree hin quufne
Hidhaa qaallitti jiraa
Dhiirri geeraree hin quufne
Hidhaa qilinxoo jiraa
Dhiirri geeraree hin quufne
Hidhaa karchallee jiraa
Karchallee Amboo jiraa…
ይህ ስንኝ በካፊል ወደ አማርኛ ሲመለስ፤
“ሸልል ሸልልይሉኛል
ምኑን ልሸልል እኔ
ቂሊንጦ አይደለም ወይ
ቃሊቲ አይደለም ወይ
ከርቸሌ አይደለም ወይ
አምቦ ከርቻሌ አይደለም ወይ…
መኖርያው የወገኔ
የፈረሶቻችንን ዝና፣
የጀግኖቻችንን ዝና
አድዋ ላይ ይነግረና!
መቀሌ ላይ ይነገር!
አብሮ መኖር ይሻላል ብለን…
መከባበር ይሻላል ብለን…
እስከዛሬ ታግሰናል…
ከእንግዲህ ግን ይበቃናል!” ይላል ሃጫሉ።
እስር ቤቱ ሁሉ አፋን አኦሮሞ ይናገራል ሲሉ እነ ስዬ አብርሃ እንኳን የመሰከሩለት ጉዳይ በመሆኑ ይመስላል ሃጫሉ በመሃል እንደ አዝማች፣ “አይደለም እንዴ? ዋሸሁ እንዴ? (ነን ሶቤ?)” የሚለው የአለምዬ ጌታቸውን ስንኝ የሚያክልበት። በቃሊቲ፣ በቂሊንጦ፣ በከርቸሌ፣ … እየማቀቁ ያሉ የሕሊና እስረኞች ጉዳይ ከራሱ ደህንነት በላይ ስላስጨነቀው ይህችን አጋጣሚ መጠቀም ነበረበት።
ይህ የጥበብ ሰው ከርቸሌን በወሬ ሳይሆን በተግባር ያውቃታል። የአድዋ፣ የመቀሌ የሚላቸው ጥጋበኞች አምቦ ላይ አስረውት ለሁለት አመት አሳቃይተውታል። ለእስር እና ለዱላ ያበቃው ወንጀሉ መብቱን ማቀቁ ነበር። በወሩ መጨረሻ ላይ በጊዮን ሆቴል ያዘጋጀው ኮንሰርትም በወያኔ ካድሬዎች ተሰርዞበታል።
ተከባብረን አብረን እንኑር ያሉ የኦሮሞ መሪዎች፤ እነ ፕ/ር መረራ ጉዲና፣ እነ በቀለ ገርባ በአድዋ ልጆች የግፍ ብትር እየተመቱ ነው። አድዋዎቹ ይህንን መከባበር እንደፍርሃት ከወሰዱት፣ መከባበሩ ካሁን በኋላ ያበቃል የሚል መልዕክት ነው ሃጫሉ ያስተላለፈው።
ይህ የሃጫሉ ስራ፣ አትሌት ለሊሳ ፈይሳ በአሎምፒክ በድረክ ከፈጸመው ጀብዱ አይተናንስም። እርግጥ ነው። አትሌት ለሊሳ አለምአቀፍ ትኩረትን ስቦ ነበር። ሃጫሉ ግን መልዕክቱን ሲያስተላልፍ በአንባገነኖቹ ጉያ ሆኖ፣ ሊመጣበት የሚችለውን ነገር ሁሉ ተጋፍጦ ራሱን ለመስዋእትነት ያዘጋጀ ጀግና ነው።
ይህንን አድርጎ ቢታሰርም፣ ታሪክ ሰርቷልና ምን ግዜም አይቆጨውም። የግዜ ጉዳይ እንጂ አምባገነኑ ስርዓት ይሄዳል የሃጫሉ ስራ ግን ምንግዜም ይዘከራል።
ሙዚቃውን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ።
ክንፉ አሰፋ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
“በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ፣ ትላንት ምሽት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት የኦሮሞ ሙዚቀኞች ማህበር ባተዘጋጀው “ወገን ለወገን” ኮንሰርት ላይ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ መድረኩን ተቆጣጥሮት ነበር።”
“የኦሮሞኛ ቋንቋ ባልችልና የሚለውን ነገር ባልረዳ ኖሮ ይጸጽተኝ ነበር።” (ክንፉ አሰፋ)
__ ወገን ለወገን ማለት ምን ማለት ነው!? የኦሮሞ ወገን አማራ፡ ትግሬ፡ ደቡቤ፡ አፋር፡ ሱማሌ መሆኑ ቀረ?
“የአዲስ አበባ፡ የሐረሩ፡ የአፋሩ፡የኦሮሞው የጉራጌው የትግሬው የአማራው የለውም አባይ አንቺ ወላዋይ እያለ ያቀነቀነው ማን ነበር?..
መቼ እንኳን ቋንቋውን ለሚችል ለማይችልም ሙዚቃ ቀስቃሽ፡አሳባሪና አስጨፋሪም ነው። እንዲያው ስሙ ያልተሞገሰና በግብዣም ያልተጠራ ወገን እንደተገለለ ተቆጥሮ ማኩረፉና መቀየሙ አይቀርም ለነገሩ ጠሪ አክባሪ ነበር ቃሉ… ነን ሶቤ?
፣ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ።“ዋሸሁ እንዴ?” (ነን ሶቤ) ሲል ይጠይቃል ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው ለታዳሚው ሕዝብ አይደለም።” ከታዳሚው ፊት-ለፊት ለተቀመጡት ለእነ አባዱላ ገመዳ፣ ወይንም ደግሞ ለእነ ለማ መገርሳ፡ ዶ/ር አብይ ለእነ አዲሱ አረጋ ይመስላል።”(ለሚመለከቱና ለሚገመግሙም) ይህ አግባብነት አለው። የ፻ ዓመት ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ ሚሊኒየም አዳራሽ? ” በአዲስ አበባ ላይ የመጨፈሪያና መሰብሰቢያ ቅድሚያ የማግኘት’ልዩ ሕገመንግስታዊ’ ጥቅማጥቅምን መብት ተጠቅሞ ጨፍሮ ወገኑን በቃሊቲ፡ በቅሊንጦ፡ በከርቸሌ አስረው በክልላቸው (እራስን በራስ በሚያስተዳድሩበት) ሰፈር የሌላው ብሔር፡ በሜንጫ ሲታረድ፡ ከነነፍሱ ገደል ሲጨመር፡ በተኛበት ቤቱ ላይ የሰደድ እሳት ተለቆ ሲቃጠል፡ ሴት ከሕጻናት በሜንጫ ሲተለተል፡ነግ በእኔ አለማለታቸው ያመጣው “የምንይልክ ሰፋሪ መጤ” የሚሉ ትምኪት የወለደው ግፍ ጠባብነት እንደሆነ ከነገራቸው ጥሩ ነው። ለመሆኑ ሌላው ብሔር ለኦሮሞ ተፈናቃይ ወገኑ ዕርዳታ እንዴት አልተገኘም? ለታሰሩ ወገኖቹስ ሲዘፈነላቸው ሲሞገሱ እንዴት አብሮ ድምፁን አላሰማም!?
__በእርግጥ ኦሮሞ የራሱን ቤት በራሱ ላይ ቆልፎ ቁልፉን ጥሎ አፋልጉኝ የወጣው ወይንም ‘ተከልሎና ተከልክሎ’ የበላተኛ ተመካች እንዲሆን የተፈረደበት በእራሱ ቦልጥቀኞች (ዲያስፐርስ) መሆኑን ማመንና መቀበል አለበት።
* አጫሉ ሁንዴሳ አድዋና መቀሌን ሊያነሳ የታጋይ ጦረኛ(ነፍጠኛ) ኦሮሞዎችን ከእነፈረሳቸው፡ ለሀገር ሉዓላዊነት ታሪክ፡ አልደፈር አልገዛ ባይነት፡ ሀገር እንዳስከበሩ በደምና አጥንታቸው ለአንዲት ኢትዮጵያ እንደተሰው አስታወሰ፡ እንጂ እንደዛሬው ሀገር ጥለው እንደከብት ጋጣ (ክልል) መታጎራቸውን ሊመሰክር አልነበረም!።
*** ስሕተቱ የመጣው ግን..ጂርቱ…ኢጆሌ ኦሮሞ ቦረና፡ አንቦ፡ወለጋ፡አርሲ፡ባሬንቱ፡ ቱለማ፡ ሜጫ ቦሌ ፡.. ኤሰ ጅርቱ? አብሮ መኖር ይሻላል ብለን… መከባበር ይሻላል ብለን…
እስከዛሬ ታግሰናል… ከእንግዲህ ግን ይበቃናል!” ይላል ሃጫሉ። ” አጫሉ ይህን የሚለው ማን እማን ላይ? እምን ላይ? ከማን ላይ? ከማን ጋር ቆሞ እንደሚነሳ አልታወቀም!?
ሌላው ሕዝብ ሁለት ግዜ አልተጠራም በግብዣውም በሽለላውም!ጉድ በል ሰላሌ! ዘንድሮ አለ ነገር! አለ …ጉዲ ሰዲ ቂም በቀል፡ ቁርሾ፡እልህ፡ እግዚኦ መሓረነ…”ያዢ ያጣች ሀገር” አሉ አባቴ ዘይገርም!
በአድ ነው ብአዴን ሁልጊዜም ለአማራ፣
ህሊናውን ክዶ ለከርሱ የሠራ፣
አማራ ለሀጫም ብሎ የሚሳደብ፣
የዓሳ ማጥመጃ የህወሀት መረብ፡፡
ጎልጉሎች!! አጫሉ እኮ ያገሳው የናንተን ሃሳብ ተመርኩዞ አይደለም!! እኔም ተከታትየዋለሁ ኮንሰርቱን!!ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ሆነብን የናንተ ነገር!!መቼም ጉዳይን ጉዳይ ያነሳውና ዘበቱ ወደ ቁምነገር አልያም ፌዝ ሆኖ ያልፋል! ስለዘበት ስናወራ ማጋነን መዋሸት:ማሳቅ:ማስለቀስ:መዘላበድ:ማቃቃር:ማወዳጀት: ማፋቀር:እና ሌላም ሌላም ይዘከዘካል!!ዘበት ነዋ!!ዘበት ራሷ ቄንጥ አውጪ ናት!! ለባብሳ የወጣች ኮረዳ ይመስል ትሽሞነሞናለች! ቀበጥ ናት እኮ! ወዲያው እኩያዋ ያዝ ሲያደርጋት:ቅብጥናዋን ተወት አድርጋ መለሳለስን ትታተከዋለች:: ዝምድና ተፈራ ሆነ!!እንዲህ ነው ትዳር!!ማን ያገኘዋል?? እመት ቀበጢናም ሳታመነታ ያኳሸማትን ጎረምሳ አቀፍ ነዋ!! ዳሩ ለምን ተኳኩላ ወጣች??ፈዘህ የቀረሀው አንተ!! ልታማት ፈለግህ እንዴ??ኧረ ወዳያ እቴ!! ከረፈፍ ሁላ !!ጎልጉሎች!! መርቀናል!!!አጃኢባ ብለን ነበር!! ምንታደርገዋለህ?? ሳይደግስ አይጣላ ሆነና መቼስ ሸርተት እንበል??እንደ ያፍ ወለምታ እንቁጠረው??እንዲያ ይሻላል!! ብሩክ ጉዞ!!
Haccalu: What a literary work. This is not entertainment as other singers do. It is a heavy message to all of us who are concerned for our people and our country that is on a cross road. His message pierce our heart pock our mind to answer the question he left us with. He did not lie. He sees what most of us did not see may be we saw and did not care. As a literary work he put most thing open for us to fill the blank. “እስከዛሬ ታግሰናል…ከእንግዲህ ግን ይበቃናል. This is a reflection of all Ethiopians regardless of nationalities. It is a futile trial to compare Hacchalus song with other as Ato Below put it up as ” …..የለውም አባይ አንቺ ወላዋይ እያለ ያቀነቀነው ማን ነበር?….This was a song of different time to reflect different situation. Haccalu put the peoples grievances in a song. He did not put Oromo grievances or Amhara grievances. He strait forward shows the grievances of all the people. It is a great work as I see it.