መግቢያ
አይ ወያኔ! መጨረሻቸውን በዓይናችን ልናይ ይሆን? አቦ አታስጎምጁኝ! ዓለማቸዉን ሲቀጩ ማቆሚያ ያጠራት ዓለማቸው ጨርሳ ልትቀጭባቸው ነው መሰል! እየዘረፉ እየገፈፉ፣ ሕዝቡን አደኸዩት፣ አስራቡት፣ አሳረዙት። እነሱ ግን ለዕርድ እንደተዘጋጀ ሰንጋ ሲደልቡ፣ ሲሰቡ ሩብ ምዕት ዓመታት አለፉ! አልጠግብ ብለው ግን መትፋት ጀምረዋል! ሕዝባችንን፣ አንገሽግሸውት አንገቱ ድረሰውታል። የከፋው የከረፋው ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ተነቃንቋል! ኦሮሞው ተነስቷል። አማራው ተነስቷል። ኮንሶው ተንስቷል። ኦጋዴን ተነሷል። … እስከወዲያኛው ከፋፍለነዋል ያሉት ኦሮሞ እና አማራ ተስማምቷል! ዕቅዳቸው ከሽፏል።
የወያኔ የግድያ ቡድን አባላት፣ ያልታጠቁ የዜጎቻችንን ደም በጭካኔ አፍስሰው፣ እኵይ ተግባራቸውን ከጀግንነት ቆጥረው ይፎክሩበታል፣ ያቅራሩበታል። አሁን ሴት ገድሎ ምን ያስፎክራል? ሕጻን ገድሎ ምን ያስሸልላል? እኵይ! እኵይ! እኵይ! የእንግሊዝኛው ቋንቋ የበለጠ ይገልጻቸዋል! COWARDS! ያ አልበቃ ብሎአቸው በግፍ ገድለው በነሱው ብሶ ሕዝቡን ሲኮንኑት ማየት አያንገሸግሽም? ንጹህ ዜጎችን እያሰሩ “ሽብርተኞች ናቸው” እያሉ ሲወነጅሉ ማየት አያበሽቅም? የታሠሩትን እያሰቃዩ፣ ያሾፉበታል። አዎን፣ ሰላም ያሸብራቸዋል። አንድነት ያሸብራቸዋል። አገር ወዳድነት ያሸብራቸዋል። አፋቸውን ሞልተው “ልማታችንን ለማደናቀፍ የተነሱ ጸረ-ልማት ኃይሎች በቁጥጥር ሥር አዋልን” እያሉ ይበሻቀጣሉ። ዕውነት ነው፣ እነሱ ከድኃው አፍ እየነጠቁ፣ እየሰቡ፣ እየዳበሩ ለምተዋል። አብዛኛው ከአፉ እየተነጠቀ ያጎርሳቸዋል። እየተራበ፣ እየከሳ እየሰለለ መንምኖ እንሱን ያለማል። ይኸ ሁሉ መብት መጋፋት፣ የዘረፋ ተግባር ዕድሜአቸውን የሚያራዘምላችሁ እየመሰላቸው ጭካኔአቸውን በላይ በላዩ ይጨምራሉ። የወያኔ አጨካከን ከሰው የተፈጠሩ አያስመስላቸውም። የመረረው የመጨረሻውን ዕርምጃ የመውሰዱን ሐቅ፣ ያ በኮለስትሮል የደነደነው አዕምሮቻቸው መረዳት ተስኖታል። ወያኔዎችች የበሉት ያገሳቸዋል! በላይ በላዩ! (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply