ታሪክ እንደ ፀሃፊው ነው። ትርክትም ዕውነቱና ውሸቱ እንደ ዶናልድ ትራምፕ አገላለጽ ተለዋጭ ሀቅ (alternate fact) የለውም። ነጭና ጥቁር ነው። አንድም ዕውነት አለያም ውሸት። ተለዋጭ ዕውነት ብሎ ነገር የለም። ታሪክና ትርክት ግን ለዘመናት የውሸትና የዕውነት ገጽታ ተላብሰው ሲጓዙ መኖራቸው አይካድም። ሩቅ ሳንሄድ “የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው” የሚለውን የወያኔን ክህደት ይጠቅሷል። “ኢትዮጵያ ጀግና ኖሯት አያውቅም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ ሆኖም አያውቅ…” የመሳሰሉት የስብሃት ነጋ የተስፋ መቁረጥ ምልክቶችን ልብ ይሏል።
የዛሬው አነሳሴ እንኳ የስብሃት ነጋን ውሸት ለመዘርዘር አልነበረም። የመምህር ገብረኪዳን ደስታን የእንጨት ሽበት አበቃቀል ለመዳሰስ እንጂ። የወያኔ ሽማግሌ የለውም። ከብዙዎቹ ራስ ላይ የምታዩት ነጭ ፀጉር የዕንጨት ሽበት ነው። የአረጋዊነት ምልክት አይደለም። ስለዚህ የወያኔ ሽማግሌ፤ የጦጣ መንኩሴ፣ የጅብ ደፋር ፈልገን እናገኛለን ብላችሁ አትድከሙ። አልፈጠረላቸውም። እንደ ወያኔ ውሸታም፣ እንደ ጦጣ አጭበርባሪ እንደ ጅብ ፈሪ ፈልጋችሁ ካገኛችሁ እኔ ከዐረብ ዳኛ ፊት ቆሜ ቅጣቴን እቀበላለሁ።
በባህላችን እርጅና (ሽምግልና) መቆንጠጫው ዕውነት ነው። ሁለት ፀጉር አብቅየ….. ይላሉ በዕድሜ የገፉ አባቶቻችን። ከዕውነት ውጭ ምንም ቃል የሌላቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሲፈልጉ። የወያኔ መሪዎች ግን ለዚህ ፀጋ አልታደሉም። ውሸታቸው ገደብ፤ ዕድሜአቸው አደብ ገዝቶ አያውቅም። በቅርቡ መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ የተባሉ “የታሪክ ምሁር” ስለ ጎንደርና ስለ ትግራይ የግዛት ክልል ጉዳይ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል። ስለ ወልቃይት።
በዚሁ ነጥብ ዙሪያ ቀደም ሲል ዶ/ር ገላውዲዎስ አራያና ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ቃለ ምልልስ አድርገዋል። የፊተኛው በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የኋለኛው ደግሞ በኢሳት ቴሌቪዥን። የሁለቱ ቃል ግን አንድ አልነበረም። ገላውዲዎስ “ወልቃይት በአጼ ዮሓንስ ዘመን የትግራይ ነበር” ብሎ ሲዋሽ፤ ልዑልነታቸው ግን “በኔም በአባቴም በአያቴም ዘመን ወልቃይት የጎንደር እንጂ የትግራይ ሆኖ አያውቅም” ሲሉ የህሊናቸውን ዕውነት ተናግረዋል። መምህር ገብረኪዳን ደስታ ግን እንደ ዶ/ር ገላውዲዎስ ህሊናቸውን ክደውታል። የሆነው ሁሉ ሆኖ ግን የወልቃይት ጎንደሬነት ወይም ትግሬነት በታሪክ ማስረጃ በፍርድ ቤት እሰጥ አገባ የሚወሰን ክርክር አይደለም። ጥያቄው ከታሪክ ብዥታ ጋር የተያያዘ ጥያቄ አይደለምና። ጥያቄው አሁን እንደ ተወሰነው ወደ ፊትም የሚወሰነው በጉልበት ነው። የጎንደሮችና የትግሬዎች የወደፊት የጅግነነት መክሊት ወልቃይት ስለሚሆን አሁን ታሪክን ዋቤ ጠርቶ መከራከሩ አጉል ግንጭ ማልፋት ይሆናል። ወሳኙ ጠመንጃ ነውና ታሪክ አጣቅሶ መልስ መመለሱ ፋይዳ የለውም።
“የታሪክ ምሁር” የተባሉት መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ቀደም ሲል ቅኔ ማህሌትና ዜማ የተማሩት በጎንደርና በጎንደር አካባቢ በሚገኙ ት/ቤቶች እንደ ነበር ገልጸዋል። ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ዘመናዊ ትምህርታቸውንም የተማሩት በዚያው በጎንደር እንደ ነበር ገልፀዋል። ለጎንደርም ህዝብ ክብርና ፍቅር እንዳላቸው አልሸሸጉም። የትግራይ ህዝብና የጎንደር ህዝብ ከቋንቋ በመለስ ልዩነት የላቸውም ሲሉም የህዝቡን የቆየ ትስስር ገልፀዋል። ዳሩ ይህን ሃቅ በመሰከሩበት አንደበታቸው ግን መልሰው ነጭ ውሸታቸውን ሲነሰንሱበት ተስተውሏል። “የትግራይ ህዝብ ለጎንደር ህዝብ ባለውለታ ነው። አጼ ዮሐንስ መተማ ላይ 100 ሺህ ትግሬ ወታደር ሰውተው ጎንደርን ከድርቡሽ ወረራ ታድገውታል። ወያኔም ጎንደርን ከሻለቃ መላኩ አገዛዝ ነጻ አውጥቶታል” ብለዋል። በዚህም አባባላቸው የትግራይን ህዝብ የጎንደር ባለ ውለታ አስመስለውታል። የትግራይ ወፍ ገልብጣ ነፋች የሚያሰኘውም ይህ የተገላቢጦሽ ውለታ ክፈሉን ባይነታቸው ነው።
ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጥሩው እንዲሉ ሀቁን እናስቀምጥ። አጼ ዮሓንስ ለጎንደር ባለውለታ ሳይሆኑ ደመኛ ናቸው። ምራጭ ካሳ (አጼ ዮሐንስ) ለእንግሊዞች ጌታ አድሮ የናፒየርን ጦር ከምጽዋ እስከ መቅደላ እየመራ ያመጣ በሀገር ክህደት ወንጀል በታሪክ የሚጠየቅ ከሃዲ መስፍን ነበር። ለአጼ ቴዎድሮስ ሞትም ተጠያቂ እርሱ ነው። ምራጭ ካሳ መቅደላ የነበረውን የአገሪቱን ነዋየ ቅድሳትና ቅርሳቅርስ በናፒየር ጦር ያስመዘበረ የእንግሊዞች ቅጠረኛ መስፍን ነበር። በኋላም በንግሥና ዘመኑ የወሎን እስላሞች ወይ ተከስተኑ (ክርስትና ተነሱ) ወይ አገሬን ለቃችሁ ውጡ በማለት እስላሞችን በግድ አከስትኗል። በዚህም ምክኒያት ኃይማኖታቸውን መለወጥ ያልፈለጉ በርካታ የወሎ እስላሞች ወደ ሱዳን ለመሰደድ ተገደዋል። እነዚህም ስደተኛ የወሎ እስላሞች ቤተ መንግሥቱን ደብረ ታቦር አድርጎ የነበረውን አጼ ዮሓንስን ድል ነስተው ወደ አገራቸው ለመመለስ ከድርቡሾች ጋር ተባብረው ወደ ጎንደር ዘምተዋል። ጎንደርም በዘመቻዎቹ ሶስት ጊዜ በሳት ጋይታለች።
እናም ለቃጠሎው ተጠያቂ የሚሆኑት አጼ ዮሐንስ እንጂ ወሎየዎቹ ወይም ድርቡሾቹ አይደሉም። ሊሆኑም አይችሉም። ለወሎ እስላሞች መከፋትና መሰደድ ተጠያቂው ዮሐንስ ነበርና። ዮሐንስም 100ሺህ የትግሬ ጦር ሰውቶ ድርቡሾቹን ድል አደረገ የሚሉን “የታሪክ ምሁር” መምህር ገበረ ኪዳን የሞተው ወታደር ትግሬ ብቻ መሆኑን የታሪክ ማስረጃ አጣቅሰው ግልጽ አላደረጉልንም። የሆነው ሁሉ ሆኖ ግን ንጉሡ ደብረታቦር ከከተሙ በኋላ ወታደራቸው ትግሬ ብቻ አልነበረም። ከተሰዋው ወሎየ፣ ጎንደሬና ጎጃሜ ጋር አብሮ የሞተው ትግሬ ወታደርም የጌታውን ድል ላለማስነጠቅ ህይዎት ገበረ እንጂ ለጎንደር ህዝብ ብሎ አልነበረም። ህይወቱን የገበረውም ጠላት አገርህን ወሯታልና ዝመት ስለተባለ ነበር የዘመተው። ለጎንደር ህዝብ የሚደማ ልብ ኖሮት አይደለም።
ለዚህም ማረጋገጫው የንጉሡ አንገት መቀላትና መሞት እንደ ተሰማ ትግሬው ወደ አገሩ ለመመልስ ጊዜ አልፈጀበትም። ከንጉሡ ሞት በኋላ ቆይቶ የመከላከል ወጊያ ሲያደርግ የቆየው ትግሬ ያልነበረው ወታደር ነበር። ስለዚህ 100 ሺህ ትግሬ መተማ ላይ ለጎንደር ተሰዋ የሚለው የመምህር ገበረ ኪዳን “ታሪክ” ውኃ አይቋጥርም። አድዋ ላይ የተሰዋው ኦረሞ፣ወላይታ፣ጉራጌና አማራ ለትግራይ ህዝብ ብሎ እንዳልተሰዋው መተማ ላይ የወደቀውም ትግሬ ለጎንደር ብሎ አልነበረም። እናም በዚህ እረገድ የትግራይ ህዝብ ለጎንደር ህዝብ ውለታ አልዋለለትም። ንጉሡም እንደ ዛሬዎቹ የልጅ ልጆቻቸው ለጎንደሮች ባለውለታ ሳይሆኑ ደመኛው ናቸው። ካንድም ሁለት ጊዜ በዳይ ናቸው። ስለሆነም ከሃምሌ 5/2008 ጀምሮ ለቀጠለው ግፍና በደል “የጎንደር ህዝብ የትግራይን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለበት” ሲሉ “መምህር” ገበረ ኪዳን የትግራይ ወፍ ገልብጣ እየነፋች መሰለኝ።
“በቅርቡ ጎንደር የተፈፀመው ነገር አሳዝኖኛል” ብለዋል “የታሪክ ተመራማሪው” መምህር። ለዚህም “አስዛኝ” ድርጊት የክልሉ መስተዳደር የትግራይን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት አስምረውበት አልፈዋል። የትግራይ ወፍ ገልብጣ የነፋችውም እዚህ ላይ ነው። “መበደል መበደል ወታደር በድሏል ግን ባላገር ይካስ” እንደ ተባለው ፍርድ መሰለኝ። የወልቃይትን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አፍኖ ወደ ትግራይ ለመውሰድ የአማራውን ክልል መስተዳደር በትምክህት ንቆ ጎንደር ውስጥ የአፈና እርምጃ የወሰደው ትግሬ ነው ወይስ ክብሩ የተደፈረው አማራ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት? ማነው ይቅርታ ጠያቂ ማንስ ነው ይቅርታ ተጠያቂ? የመምህር ገብረ ኪዳን ሽበት የእንጨት ሽበት ሲሆን የሚታየውም እዚህ ላይ ነው።
መምህር ገብረ ኪዳን ደስታ ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ የፈፀመውን በደል ገልብጠው “ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ነው” ሲሉም ድርጊቱን ተመጻድቀውበታል። ማነው ማንን ያጎረሰ? ማነው የማንን እጅ የነከሰ? ማነውስ ለማን ውለታ የዋለ? ጎንደር ነው ለትግራይ ወይስ ትግራይ ነች ለጎንደር ባለውለታ?
ባለፉት በርካታ ዘመናት ራሳቸውም ያልካዱት እርሳቸውንና ወላጆቻቸውን ጨምሮ ወደ ጎንደር እየመጣ ቀን አውጥቶ የሚመለሰው የትግሬ ቁጥር ይኸ ነው አይባልም። ጎንደር ለትግራይ ህዝብ የቀን መውጫ ሆና መኖሯ አይካድም። እኔ እስከ ማውቀው ድረስ የትግራይ ህዝብ በያመቱ ከህዳር እስከ ግንቦት ወር መጀመሪያ ወደ ጎንደር እየተሰደደ በመኸር ወቅት ሴቱ ቀርም ሲለቅም ወይም በችፍርግ የተለቀቀ አውድማ ሲጠርግ፤ ወንዱ ደግሞ አዝመራ አጭዶ እህል ወቅቶ በቀን ሠራተኝነት ሸቅሎ ያጠራቀመውን ወረት ወደ ትግራይ ይዞ ሲመለስ ነው።
ከተማ የገባው ባለ እጅና ነጋዴም ወይ “ልዋጭ ልዋጭ” በማለት አለያም ሰባራ ገንቦ በመለሰን ቀን አውጥቶ ወደ ትግራይ ይመለሳል እንጂ ጎንደሬ ወደ ትግራይ ተሰዶ ቀን ያወጣበት ዘመን ኖሮ አያውቅም። ትግሬ እንጂ ወደ ጎንደርና ጎጃም ሄዶ ተምሮ የሚመለስ አማራ አልነበረም። ስለሆነም አእምሮውን በዕውቀት አጎልምሶ፤ ርሃቡን በዕህል ውኃ አስታግሶ፤ እርቃኑን በልብስ ሸፍኖ የትግራይን ህዝብ ሰው አድርጎ ያኖረው የጎንደር ህዝብ ነበር። በትግሬ እጁ የተነከሰውም የጎንደር ህዝብ ነው። እናም ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ ማለት ያለበት ጎንደሬ እንጂ ትግሬ ሊሆን አይችልም። ለጫንቃው ጨርቅ ለእግሩ መጫሚያ ሳይኖረው ወደ ጎንደር ተሰዶ የጠነጠነ ሃብታም የሆነው ትግሬ ነው የበላበትን ወጭት ሰባሪ የሆነው። ወደ ሁመራና ወልቃይት በቀን ሠራተኛነት የሄደው ትግሬ ለማዳ ሆኖ ቀርቶ ነው ዛሬ አፉን ሞልቶ ወልቃይት የትግሬ ነው የሚለን።
መምህር ገበረ ኪዳን ደስታ ከናዚና ከሞሶሎኒ ጋር አመሳስለው ኢህአፓን “የትግራይ ህዝብ ጠላት” ሲሉ ከሰውታል። ዐይን ራሱን አያይም ሆኖ እንጂ የትግራይ ህዝብ ጠላት ማንም ሳይሆን ትግሬ ነው። ለመምህሩ ግን አይታያቸውም። በጥቅም ታውረዋልና። እርሳቸውን ያሳሰባቸው የትግራይ ህዝብ ችግር አይደለም። የራሳቸውና የቤተሰባቸው ድሎት መደፍረስ ነው። ለዚህም ነው “ነቅናቂ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል” ሲሉ የተደመጡት። ጥሯቸውን ያደፈረሰውም ኢህአፓ እንደ ሆነ አማርረው ተናግረዋል። ግን በትግራይ ህዝብ ማሳበቡ አስገምቷቸዋል። እንዳው ለነገሩ ግን መምህሩ ከደረታቸው ጋር የተጣበቀው ሳንባቸው አቀበት አያስወጣቸው እንደሁ ባላውቅም ወደ አዲ ዩሮፕ ወይም ወደ አጋሜ አውራጃ ወደ አንዱ ወረዳ ጎራ ቢሉ የትግራይ ህዝብ ለኢህአፓ ኢህአፓም ለትግራይ ህዝብ ያለውን ፍቅር በተገነዘቡ ነበር። ስለ ሞሶሎኒና ስለ ናዚ ያላቸው ግንዛቤ ግን “የታሪክ ተመራማሪነታቸውን” እርቃኑን ያቆመው መሰለኝ። ያን አገላለጻቸውን ኢህአፓ ያስተማረው የበለሳ ወይም የጠለምት ገበሬ ቢሰማ “መምህሩ” ሁለተኛ ከሰው ፊት እንኳን የታሪክ ተመራማሪ ነኝ ሊሉ ፊደል የቆጠርኩ ሰው ነኝ ለማለት አይደፍሩም።
መምህር ገበረ ኪዳን ደስታ ወያኔንም እንደ አጼ ዮሐንስ ለጎንደር ህዝብ ባለውለታ ነው ብለውታል። መላኩን የመሰለ ገዳይ ያስወገደለት የወያኔ ሠራዊት ነው ብለዋል። ሀቁ ግን ለጎንደር ህዝብ ወያኔ ሌላው መላኩ ነው። እንዳውም ወያኔ ከመላኩ የከፋ ነው። መላኩ የገደለው ሰውን ነበር። ወያኔ ግን ሰውም አገርም ገዳይ ነው። መላኩ አንድን ዘር ነጥሎ አልገደለም። የገደለው ትግሬውንም አማራውንም ኦረሞውንም ጉራጌውንም … በጅምላ ነበር። ወያኔ ግን አማራ እንጂ ትግሬ አይገድልም። ዛሬ በጎንደር ገዳዩ ትግሬ ነው። ወያኔ ጎንደርን የነገ ብድር ከፋይ አድርጓታል። ያውም ከነ አራጣው።
ጥር 2009
አብርሃም በየነ (abraham3106@comcast.net)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
በለው! says
http://www.ethiopatriots.com/pdf/%E1%89%A0%E1%8D%8B%E1%88%BA%E1%88%B0%E1%89%B5-%E1%88%B5%E1%88%AD%E1%8B%93%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%89%B3%E1%89%A0%E1%8B%AD-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%AD-%E1%8C%88%E1%89%A5%E1%88%A8%E1%8A%AA%E1%8B%B3%E1%8A%95-%E1%8B%B0%E1%88%B5%E1%89%B3-%E1%88%9E%E1%88%8D%E1%89%B6-%E1%8B%A8%E1%8D%88%E1%88%B0%E1%88%B0%E1%8B%8D-%E1%8B%8D%E1%88%B8%E1%89%B5-Getachew-Reda-c.pdf
Tadesse says
He is just worst than memher Gebrekidan,I am so ashamed to say such words on this older man.
tnish atasebum,gazwetegna mallet yehonewn kushasha lsew masnebeb new?And you are calling yourselves a better Ethiopians,esat yeblachehu. derows ke ale amagn men yetebekal? gazetegna le ene wesha new.
Mulugeta Andargie says
Guys!!!History tells us the past and present with facts.