በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ! አሜን።
ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው ኃጢያተኛውን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን የኃጢያትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ። የያዕቆብ መ.5፤19-10።
እግዚአብሔር በዘመናት መካከል ለሕዝቡ በባሪያዎቹ እየተናገረ፤ ሕዝቡን ከመከራ እና ከመተላለፋቸው እየመለሰ፤ ወደ ክብሩ መንግስት እያፈለሰ፤ ዓለም ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ አሁን እኛ እስከደረስንበት ጊዜ ድረስ ወንጌል ወደ እኛ ደርሷል። ወደፊትም ዓለምን ከመኖር ወደ አለመኖር እስከሚያመጣት ድረት ይኸ ሁኔታ ይቀጥላል። ስለሆነም ሕዝቡ ባለማወቅ ጨለማ ውስጥ ሲተራመስ ፤ ሕዝቡን በጨለማ ውስጥ የማይተው አምላክ በወደደው ጊዜና ስዓት ነገሮችን ከተሰወሩበት ግርዶሽ ውስጥ ወዶ ይገልጣል። ዛሬም ቃሉንም ሆነ ህጉን ካለማወቃችን የተነሳ እንዳንጠፈ የተሰወረውን ገለጠ። ክብር ለስሙ ይሁን።
ዶግማ ፦ ምንድን ነው?
ቀኖና፦ ምንድን ነው?
ፍትሐ ነገሥት እና ቃለ አዋድስ?
እነዚህን የሐይማኖታችንን መሰረቶች እና በውስጣቸው ያለውን የመተዳደሪያ ስርዓት የያዘ ጥልቅ ሚስጥር ፤ ሕዝቡ በሚገባው እና በሚገባዉ መንገድ እንዲረዳ እና እንዲያውቅ ተደረገ። ተማረ፤ ተረዳ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!
Leave a Reply