በመሠረቱ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ስለ አብዮቱ “ እኛና አብዮቱ “ የሚል መጸሐፍ ጻፉ የሚል ዜና ስሰማ ፣ መጸሐፋቸው እንደ ሌ/ኮ መንግሥቱ ኃይለማርያም መጸሐፍ በቅጥፈት የተሞላ አይሆንም ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ፡፡ ግን ሳይሆን ቀረ፡፡ በነገራችን ላይ የሻምበሉን መጸሐፍ ገና አላገኘሁትም፣ ነገር ግን አንድ ወዳጄ ከምዕራፍ 13–16 ያሉትን ገጾች ፎቶ ኮፒ አድርጎ ስለሠጠኝ አየተገረምኩኝ አነበብኳቸው፡፡ ሻምበሉን ምን ነካቸው ብዬም እራሴን ጠየኩኝ፡፡ ደራሲው በትምህርታቸው እንዳልገፉ ይገባኛል ፡፡ ሆኖም ግን በትምህርት ያለመግፋት ትንታኔ ላይ ችግር ይፈጥር እንደሆን እንጂ ፤ “ በእጅ የገባን መረጃ ” አሳስቶ ማቅረብ ከምን ሊመነጭ እንደሚችል ፈጽሞ ሊገባኝ አይችልም፡፡ ፍቅረሥላሴ መረጃው በእጃቸው ከሌላቸው አርፈው መቀመጥ አለባቸው እንጂ ባልሆነ ማስረጃ አንባቢን ማሳሳት የለባቸውም፡፡ መረጃው በእርሳቸው በኩል መቅረቡ ደግሞ የበለጠ አደገኛ የሚያደርገው ፣ ግለ-ሰቡ በደርግ ውስጥ በከፍተኛ ሥልጣን ላይ የነበሩ ሰለሆኑ መረጃው አላቸው ተብሎ ስለሚገመት ነው፡፡ ዕውቀት መቸም በሁለት መንግድ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply