በእንግሊዝ የተፈበረከው ፈስ የሚያጣራ ውስጥሱሪ በአሜሪካውያን ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊነቱ እየመጣ መምጣቱ ተሰምቷል፡፡ የአምራች ኩባንያ አፈቀላጤ የሆኑት ሲናገሩ “ከአጠቃላይ ሽያጫችን ውስጥ በአሜሪካውያን የሚገዛው እጅግ ከፍተኛውን ቁጥር የያዘ ነው” ብለዋል፡፡
ታዋቂው የውስጥሱሪ አምራች ሽሬዲስ በቅርቡ ፈስ አጣርቶ በማስቀረት እንዳይሸት የሚያደርግ ውስጥሱሪ ለወንዶችና ለሴቶች ለገበያ ማቅረቡ ከተሰማ በኋላ ሽያጩ በ400% አድጓል፡፡
ኩባንያው እንደሚለው በውስጥሱሪው የውስጠኛ ክፍል ከካርቦን የተሰራ ዞርፍሌክስ የሚባል ጨርቅ የተሰፋ ሲሆን ይህም አማካይ የሽታ መጠን ያላቸውን የፈስ ዓይነቶችን 200 ጊዜ ያህል እንዳይሸቱ የማድረግ ችሎታ እንዳለው አፈቀላጤዋ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ሲቀጥሉም “ይህ የውስጥሱሪ ለሁሉም የሚያስፈልግ ነው፤ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ይፈሳል” በማለት የኩባንያቸውን ምርት አስተዋውቀዋል፡፡
በኩባንያው የተሰጠው መረጃ እንደሚያመለክተው የወንዶቹ ውስጥሱሪ ዋጋ ከ39 እስከ 45 ዶላር ሲሆን የሴቶቹ ደግሞ ከ31 እስከ 34 ዶላር መሆኑን ጠቁሟል፡፡
የዋጋው መጠን ከጾታ አንጻር የበርካታውን ተጠቃሚ አመላካች ሆኖ ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡ (ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ)
ezra says
ቂ ቂ ቂ ቂ ቂ ወይ ጐልጉሎች ! ብላችሁ ብላችሁ ደግሞ ፈስ አፈኖ የሚይዝ ዉስት ሱሪ ተገኘ ብላችሁ ጎለጎላችሁ…? I REALLY LIKED The News ቂ ቂ ቂ ቂ …… በእውነቱ ፈረንጆች ፈስ በዝቶባቸዋል ማለት ነው። ቂ ቂ ቂ
በለው! says
***እልል…….በእርግጥ ይህ ወደ አፍሪካ ሀገራት መሸጥ ዕድል ቢገጥመው ወይም ኢንቨስተር ቢሠራበት ያበላዋል! ኢትዮጵያ ውስጥ ያዋጣል።ኢህአዴግ አሁን ባለው ትክክለኛ መረጃ ደጋፊና ተደጋፊዎቹ ቁጥር በሀገር ውሰጥ ብቻ ወደ፬ሚሊየን ሲሆን መሬትና ኮንደምኒይመ የተሰጣቸው አሁንም እንዲሰጣቸው እግራቸውን የሚቀጥኑት ቁጥር ከእነቤተሰበቻቸው ወደ፩ሚሊየን የሚደርስ አባላት እናዳሉት ይደነፋል። ለእነኝህ ሁሉ ለሚነፈት ቱልቱላና ቀደዳ መዝጊያ ውሸት ማጣሪያ ሆኖ ከተሰራ በእውነቱ ከትውልድ ምክነት ፣ከድምፅ ብክለት፣ከንብረት ጥፋት፣ ሁሉ ሀገሪቷንም ይታደጋታል ለኢንቨስተሩም ትቅም ለሀገርም ግንባታ ለራሱ ኢህአዴግም ከግብር(ቫት) ጥቅም ያገኝ ነበር የሚል ምክርና ግንባታ አለኝ ልብ ያለው ልብ ያድርግ!! ውሸት ሰለቸን አሉ…አዎን! ቀወጡት ኩባንያው እንደሚለው ..ዞርፍሌክስ የሚባል ጨርቅ ስለሆነ በአማርኛ እኛ (ዞር በልከዚህ) መሆኑ ነው።ለገበያ ማቅረቡ ከተሰማ በኋላ ሽያጩ በ፬፻% አድጓል፡፡ይህ ከተከታታዩ ፲፩ከመቶ ውሸት ዕድገት አሁን ፰.፭የገባው እራሱ ይህን የውሸት ማጣሪያ ሆኖ አንዳንድ መጠቀም በመጀመራቸው ነው ተብሏል።በእርግጥ ፪.፭ ውሸት ከቀነሰ ተስፋ የሚሰጥ ምርት ነው። ሲቀጥሉም እድሜ፣ ፆታ፣ ዘር፣ ጎሳ፣ የማይለየው ቡድን ውሸት በኢህአዴግ ባህላዊ አሠራር ላይ በራዕይ ለማስፈጸም ከትውልድ ትውልድ እንዲቀጥል ለማድረግ የተነደፈ ቀጣይነት እንጂ ማቆሚያ የለውም ስለዚህ “ይህ ትጥቅ ለሁሉም የሚያስፈልግ ነው፤ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ይዋሻል” በማለት የኩባንያቸውን ምርት አስተዋውቀዋል፡፡ይህንኑ ሥራ ላይ ለማዋል በተያዘው ቀደዳ መሠረት ለኢህአዴግ የምርጫ መቃረቢያው ላይ አጋር ፓርቲዎችም በግድ እንዲጠቀሙበት በነጻ የሚታደል መሆኑን ውስጥ አዋቂና አዳናቂ ዜና ሰባሪዎች ሳይሸረፍና ሳይበረዝ የምርቱ ተጠቀሚ መሆናቸውን አደርባይና ሆድአደሮችም የልባቸውን ጉልጉል አድረገው ተናግረዋል። በለው!