በጀርመን የኦርየንታል (የመካከለኛው ምስራቅ) ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት አንድ የጋራ ሲኖዶስ ለመመስረት ስለፈለጉ፤ ትላንት የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያውን እርምጃ ወስደዋል። በዚህም መሰረት ጳጳስ አንባ ዳሚያን (የኮፐት ኦርቶዶክስ) እና ሊቀጳጳስ ሙሴ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ) ውል ተፈራርመዋል።
በኮፕት ገዳም የውል ሰነድ ፊርማ፤ ሊቀጳጳስ ሙሴ (2. ከገራ ወደቀኝ) እና ጳጳስ አንባ ዳሚያን (የመካከለኛው ) (ከመሃል) ፊረማቸውን በውሉ ሰነድ ላይ አስቀመጡ። በዚሁ ጊዜ በቦታው የነበሩ፤ አባ ዳዊት ሙሳ ከግብጽ እንዲሁም የገዳሙ ጎብኝ እንግዶች/ካቶሊኮች/ ሞሲኞር ፔተር ፎን ሸታይኒትጽ (ከግራ) እና ዲያቆን ክርስቶፍ ፐሪንስ ቤተልሄም (ከቀኝ) እንዲሁም ሚዛን ገብሩ (ሁዋላ ከግራ) ማግዳሌና ግርማ፤ ሳራ ኪዳኔ እና ሞገስ ተሾመ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Dawit says
ውድ አንባብያን እና በጀርመን የምትገኙ የቤ/ክችን ምዕመናን ከላይ የቀረበው ፅሁፍ የሀሰት ክስ ሲሆን ፣ሀገረ ስብከቱ እንዳይመሰረት የሚፈልጉ ፣የሃይማኖት ዕፀፅ ያለባቸው ፣ጥቅመኛ ግለሰብ የፃፉት መሆናቸው ይታወቃል።
Dawit says
የዚህ ፅሁፍ አስተያት ሰጪ ግለሰብ አስተያየት ከመስጠታቸው በፊት ሀገረ ስብከቱን ወይም የሀገረ ስብከቱን ጳጳስ ስለ ሁኔታው ማጣራት ይችሉ ነበረ ። የዚህ ግለሰብ ክስ በሀገረ ስብከቱ ስብሰባ ላይ አንስተው ውድቅ የሆነባቸው፣ ከሌሎች ሃይማኖት ጋር አንድነን ብለው የፈርሙ፣ የሃይማኖት ዕፀፅ ያለባቸው ፣ ቤ/ክያኒቱን ለ30 ዓመታት የመሩ ነግር ግን ራሳቸውን እንደሃይማኖት መሪ ሳይሆን እንደጦር መሪ የሚያስቡ ፣ተጨባጭ ስራ የሌላቸው እንድ አግልግሎት ዘመናቸው በአሁን ወቅት የሀገረ ስብከቱ መጠናከር ስላልአስደስታቸው የሀገር ስብከቱ እንቅስቃሴ ለማዳከም በሀሰት ስማቸው እየከሰሱ ይግኛሉ።