የኔነት መለያ ~ የናት ያባቴ አገር ~ የተወለድኩባት፣
ስረ መሰረቴ ~ ቅርንጫፍ ሀረጌ ~ እትብቴ ያለባት፣
ተስፋዬ : ውጥነኔ ~ ህልሜ ሚፈታባት፣
ሀገሬ የኔ ናት~ ፣
ሀገሬ እርስቴ ናት~።
አፈሩን ፈጭቼ ፣
ውሀ ተራጥቼ ፣
ዘልዬ ቦርቄ ~ ያደኩበት መንደር ፣
በሀሳብ በርሬ ~ በምናብ ከንፌ~ የማርፍባት ሰፈር ፣
የማንነቴ ምንጭ ~ መመኪያ አገሬ፣
አድባሬ አውጋሬ ፣
የዘወትር ህልሜ ~ የድካሜ እፎይታ ~ ማረፊያዬ ጎጆዬ፣
የትም የትም ዞሬ ~ ማሳረጊያ ቤቴ ~ አንገት ማስገቢያዬ፣
አገሬ እማማዬ ።
ቀየሩት ይሉኛል ~ አፈረሱት አሉኝ ~ ለወጡት ባዱኛ፣
የኛ ሰፈርማ ፣
ሜዳው ሸንተሩ ~ መቦረቂያ መስኩ ~ አሁን የት አለና፣
ተሸጠ ለሌላ ~
የነሱን ኪስ ሞላ።
ይህው በቀደም ለት ፣
ደውዬ ልጠይቅ ~ የወዳጅ ደህንነት፣
ስልኩ ጠርቶ ጠርቶ ~ “• • • ጥሪ አይቀበልም” ~ የምትል ሴት አለች፣
ያውም ባባቴ ቤት ~ በተወለድኩበት ~ ደሞ ይቺ ማነች?
ብዬ አጠያይቄ ~ ጭራሽ መልስ ባጣ፣
ሳወርድ ሳወጣ፣
ኔት ወርክ ስለሌለ ~ የሚል ምላሽ መጣ።
ኔት ወርክ ስለሌለ?
መብራት ስለሌለ?
ውሀ ስለሌለ?
የት ገባ ተባለ?
የምናየው ልማት፣
በ’ኢቲቪ’ መስኮት?
አረንጓዴ ለብሶ ~ አውድማው አሽቶ፣
እህል ተትረፍርፎ ~ ህዝብ ጠግቦ በልቶ፣
በአየር በምድር ~ መንገድ ተዘርግቶ፣
ከተማው ተውቦ ~ ህንፃው ሰማይ ነክቶ፣
ስልጣኔ ገኖ ~ ቴክኖሎጂው በዝቶ፣
እኔን ግራ ገባኝ • • •?
ማንስ ነው `ሚነግረኝ?
የሚወራው ሌላ የሚታየው ሌላ፣
አረ ለመሆኑ ~ ‘ኢቲቪ’ የሚባለው
የምስኪኗ አገሬ ~ ወይስ የሌላ ነው?
ብሌን ከበደ 20/12/2014
በለው ! says
አይ ሀገሬ ማለት!?
ኢትዮጵያዊ ብለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ
ሉዓላዊነት ተደርምሶ ብሔራዊ አጥፍተው ክልላዊ
እያፈራረሱ-ልማታዊ…አስረው ገለው-ፍትሃዊ
እርስ በእርስ እያባሉ…ነጣጥለው ዲሞክራሲያዊ
ኢንቨስተር ዲያስፐር (ፈላሽ) የሙት ራዕይ አስቀጣይ
ከኅብረ ብሔር…ጎጠኛ ከመሬት ባለቤትነት…በሊዝ ተከራይ
የፈጠርናችሁ ያሉን መጤ ሰፋሪ እንጂ ባለሀገር ነን ወይ?
*********
በኢቲቪ ኢቢ ኤስ መስኮት የሚታየውን ልማትማ
አየን አሉ እንጂ የበላው ጠግቦ መች ተስማማ
ለአረንጓዴማ እንክርዳድም አረንጓዴ ነው
አየን አውድማው ላይ ንፋስ ቅጠሉን ሲንገላታው
መች አሸተ ተወቅቶ ጆንያውን ገበያ አየነው
በስም አይገዛ በዓይን አይሸመት ዝም ነው
እኛማ ፉከራ ወሬውን ጠገብን የበላው ጎረቤት ነው
የእኛ ቀልቀሎ የሞላው ያው ከምፅዋት በመጣ ነው
ምን መንገድ ቢበዛ በአየር አቋራጭ አሳላጭ ፈጣን
የሚሄድ ጫኝ ነው እንጂ የሚመጣ አውራጅ አላየን
በቻይና ሸቀጥ በከተማው ውበት በትላልቅ ፎቆች
አይናማ በበዛበት ግራ ተጋብተው መሪና ተመሪዎች
በጠበበ ምሕዳር ቀኝ የሚያሳይ ጠፋ ሁሉ ግራ አግቢዎች
ቴክኖሎጂ እረቆ ሥልጣኔ በዝቶ ሁሉን ተመፅዋች
እነ ቆርጦ ቀጥል ሜትር ዘርጊ የለ ሁሉ ገመድ ጎታች
እነ አውርቶ-አደር እነ ሆድ-አምላኩ ሁለተኛ ዜጎች
ለምነው ያድራሉ ከታች ወደ ላይ እየተረገጡ ከላይ ወደታች!
ተቀብሎት ሕሊናቸው ኢትዮጵያ የእነሱ እንዳልሆነች
ኢቲቪ ያለ ሰው ብቻውን የኢትዮጵያ አይሆንም
ሰው ያለስብዕናው እግር ያለ ሀገር አይቆምም።
በለው!
Denkew Emagnaw says
የልቤን ኡ ኡ ኡታ