• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ከዚህ በኋላ ፍ/ ቤት ላለመቅረብ ወስኛለሁ!…”

December 30, 2019 05:56 am by Editor Leave a Comment

(ኤርሚያስ አመልጋ – ከቂሊንጦ)

ድፍን አንድ አመት!…

በህግ ሊያስጠይቀኝ የሚችል ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት ባልፈጸምኩበት እና ለክስ የሚያበቃ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ለእስር ከተዳረግኩና ፍትህ አገኝ ብዬ ፍርድ ቤት መመላለስ ከጀመርኩ እነሆ ድፍን አንድ አመት ሞላኝ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ እና ፍርድ ቤት በአንድ ሳምባ በሚተነፍሱበት ስርዓት እና አገር ላይ፣ ገለልተኛ ፍርድ እና ሚዛናዊ ፍትህ ማግኘት እንደማይቻል በአንድ አመት የእስር ቤት ቆይታዬ ያረጋገጥኩት ሃቅ ነው!!!

ከዚህ በኋላ ፍትህ አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ራስን ማጃጃል አንደሆነ ተገልጾልኛል፤ አሁን ከስርዓቱ ፍትህ የምጠብቅበት ሳይሆን በእኔ ከደረሰውና ዙሪያዬን ከማየው ተነስቼ የአገራችንን የፍትህ ስርዓት ነውረኛ ባህሪ ለህዝብ የምገልጽበት ወቅት ነው፡፡

“መርምረን እናስራለን እንጂ፣ አስረን አንመረምርም” የተባለለትን የለውጥ ዲስኩርና ፕሮፖጋንዳ ተከትሎ፣ ብዙ ተስፋ የተጣለበት የፍትህ ስርዓት፣ ዛሬም እንደ ትናንቱ ፍጹም የመንግስት ወገንተኝነቱን እና የአምባገነን መንግስት መሣሪያና መጠቀሚያ ሆኖ መቀጠሉን ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለዓለም በድፍረት ማሳወቅ አስፈላጊ መሆኑን ከልብ አምኜበታለሁ፡፡

ከዜጎች ጎን ሆኖ ለእውነት፣ ለፍትህና ለህግ ልዕልና የሚቆም ስርዓት መገንባት ቀጣይ የአገራችን ዜጎች ትልቅ የቤት ስራ መሆኑን በአጽንኦት ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡

ራሳቸውን ከወገንተኝነት ካላጸዱ የፖሊስ፣ የአቃቤ ህግ እና የፍርድ ቤት ተቋማት ጋራ የተጓዝኩበት ረጅም ጎዳና፣ በፍትህ ስርዓቱ ላይ እምነት መጣሌን ትቼ ከመንገዱ ወጣ እንድልና ራሴን በጽሞና እንድጠይቅ አስገድዶኛል፤ አልፎ ተርፎም ከበስተጀርባ በስውር እጆች እየተቀነባበረ የሚሰራብኝ ትልቅ ድራማ እንዳለ ግልጽ አድርጎልኛል፡፡

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት፣ ከኢምፔሪያል ሆቴል ሽያጭ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቃለ-መጠይቅ እፈልግሃለሁ ብሎ ሲጠራኝ፣ ጥሪውን አክብሬ በመሄድ ስለጉዳዩ በቂ ማብራሪያ ሰጥቼ ነበር፡፡ ሊያስጠይቀኝ የሚችልና ለክስ የሚያበቃ ምንም ጉዳይ እንደሌለ በማስረዳት ተግባብተን ነበር የተለያየነው፡፡

ከዚያ ቀጥሎም፣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ምንም አይነት የጥያቄም ሆነ የአቋም ለውጥ ሳያደርግ እንደገና በሌላ ሁለተኛ ዙር በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንድሰጥ ጠየቀኝ፡፡ እኔም በተጠየቅኩት መሰረት በቂ ማብራሪያ በመስጠት፣ ሊያስከስሰኝ የሚችል ምንም ጉዳይ እንደሌለ በአሳማኝ ማስረጃዎችና በምክንያታዊነት አስረዳሁ፡፡

ያቀረብኩት ማብራሪያ አሳማኝ ሆኖ ሳለ ግን፣ የመንግስት ፍላጎት በሚመስል እናባልጠበቅኩት መልኩ ወደ እስር ቤት እንድገባ ተደረግኩ፡፡ በዚህ መልኩ በቂ መረጃና ማስረጃ በሌለበት ወህኒ ከተወረወርኩና እስር ቤት ታጉሬ ፍትህ ፍለጋ ቀናትን፣ ሳምንታትንና ወራትን መቁጠር ከጀመርኩ ይሄው ድፍን አንድ አመት ሞላኝ፡፡

ባለፈው ታህሳስ 17 ቀን 2012 ዓ.ም…

ማልጄ ወደ ልደታ ፍርድ ቤት ስሄድ፣ በእለቱ የሚሰየመው ችሎት የመጨረሻ ብይን እንደሚሰጠኝ በመተማመንና በሙሉ ተስፋ ነበር፡፡ ችሎቱ ሌላ ቀጠሮ ሲሰጥ ግን፣ በውስጤ የተዘራው ተስፋ ድንገት መከነ፡፡ ቀጣይ ያልታወቁ ወራትን በእስር ስማቅቅ እንድገፋ የሚያደርገኝ ቀጠሮ የተሰጠኝ፣ ከፍርድ ቤቶች በስተጀርባ ባሉት ስውር እጆች ግፊት እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ታየኝ፡፡

ይህን እውነታ እየተረዳሁ፣ ፍትህ አገኛለሁ ብዬ መተማመን ከንቱ ጅልነት ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ከዚህ በኋላ የሚሰጠው ፍትህ ቢኖር እንኳን፣ “የዘገየ ፍትህ እንደተነፈገ ይቆጠራል” የሚለው ብሒል እንኳን የሚገልጸው አይመስለኝም፡፡

በአገራችን ነጻና ገለልተኛ ተቋማትን ለመገንባት በተደረገውረጅም ትግል የተከፈለው መስዋዕትነት፣ በጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ በፖሊስና በፍርድ ቤቶች ነውረኛ እና ወጋኝ አካሄድ ከንቱ መቅረቱን ባሰብኩ ጊዜ ጥልቅ ሃዘን ይሰማኛል፡፡

በየዘመናቱ ለመጣው አምባገነን ስርዓት ሁሉ ትልቅ መገልገያ ሆነው የዘለቁት ከላይ የጠቀስኳቸው ተቋማት ነጻና ገለልተኛ መሆን እስካልቻሉ ድረስ፣ የዜጎች መብት ይረጋገጣል ብሎ ማሰብ ፍጹም የማይታሰብ ነው፡፡

የታመመውን የአገራችን ኢኮኖሚ ለማከም እንዲሁም በስርዓቱ ተስፋ ቢስ የሆኑ የአገራችን ወጣቶችን ወደ ዘላቂ መሻሻልና ዕድገት ሊወስዱ የሚያስችሉ ትልልቅ ዕቅዶችን ለመተግበር በተነሳሁበት ወቅት፣ከበስተጀርባ ባሉ ስውር እጆች የሚጎነጎንብኝ ሴራ እና የሚፈጸምብኝ ደባ፣ ፖለቲካዊ ባህሪ እንዳለው ለመገንዘብ ችያለሁ፤ መላው ኢትዮጵያዊም ይህንን እውነታ እንዲረዳልኝ እፈልጋለሁ፡፡

ከአሁን በኋላ ከወገንተኝነት ካልጸዳ ፍርድ ቤት ችሎት መታደም፣ “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” እንደሚሉት ራስን ማታለል ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ ስለሆነም የራሴን አቋም መያዜን እና ከዚህ በኋላ ፍትህ ፍለጋ ወደ ፍርድ ቤት ላለመሄድና ችሎት ፊት ላለመቅረብ ቁርጥ ውሳኔ ላይ መድረሴንለህዝቡ በይፋ ለማሳወቅ እፈልጋለሁ፡፡

በመጨረሻም በኖቤል የሰላም ተሸላሚው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ እንዲሁም በጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በጠቅላይ አቃቤ ህግ እና በሌሎች ተቋማትና ሃላፊዎቻቸው ላይ የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘንና በእነሱ ተስፋ መቁረጤን ሳልናገር ማለፍ አልፈልግም፡፡

ኢትዮጵያውያን ሁሉ ለመሰረታዊና ለሁለንተናዊ ለውጥ ዝግጁ የሚሆኑበት፤ ዘላቂ ትግል በማድረግ ነጻና ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት የሚያስፈልግበት ጊዜው አሁን ነው!!!

(የማይነበብ ፊርማ)

ኤርሚያስ አመልጋ ፣ ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፣ አዲስ አበባ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: ermiyas amelga, Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule