• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ባንዲራ ጨርቅ አይደለም” የኢህአዴግ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን – ኢብኮ

March 9, 2015 11:05 am by Editor 2 Comments

• የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክት ለአራተኛ ጊዜ በሚዲያ እንዳይተላለፍ ተከለከለ

• ኢብኮ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት “አላስተላልፍም” ብሎ መልሷል

• “ኢብኮ ከገዥው ፓርቲ ጋር ወግኗል” አቶ ዮናታን ተስፋዬ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት “አላስተላልፍም” ብሎ መመለሱን ዛሬ የካቲት 29/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ ገልጾአል፡፡ ኢብኮ በደብዳቤው “የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በምስሉ ግርጌ የተቀመጠው እንዲሁም በቅስቀሳ መልዕክታችሁ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚታየው ሰንደቅ አላማ ምስል የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ የማይወክልና ህገ መንግስቱን…. የሚፃረር ሆኖ አግኝተነዋል” በሚል እንደማያስተላልፍ ገልጾአል፡፡

በሌላ በኩል “ይህ የኢብኮ ተግባር የሰማያዊን ፕሮግራም ላለማስተላለፍ ሆን ተብሎ የተሰጠ ሰበብ ነው” ያለው የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ በህገ መንግስት የተከለከለውን ቅድመ ምርመራ ኢብኮ እየተገበረው ነው ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

“ህግ ተጥሷል ከተባለ እንኳን ፕሮግራሙ ከተላለፈ በኋላ እንከሰስ ነበር እንጅ ባልረባ ምክንያት አላስተላልፍም ብለው መመለስ አልነበረባቸውም” ያለው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ሰንደቅ አላማ የሚውለበለበውን እንጅ ከዛ ውጭ ያለን ማናቸውንም ነገር የሚመለከት አይደለም ሲል ኢብኮ የፓርቲውን መልዕክት ላለማስተላለፍ ያቀረበውን ሰበብ ተችቷል፡፡ አቶ ዮናታን አክሎም “በአዋጅ 654/201 ላይ የሰፈረው ህግ አንድም ቦታ ተሰቅሎ ስለሚውለበለብ፣ ከመኪና ከሚውለበለብ እና በአደባባይ ከሚያዝ ሰንደቅ አላማ ውጭ ስለ ሌላ አንዳችም የሚከለክለው ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ኢቲቪ ለገዥው ፓርቲ በመወገን ፕሮግራማችን እንዳይተላለፍ እያደረገ ነው” ሲል ወቅሷል፡፡

በተያያዘ ዜና ፓርቲው ነገ የካቲት 30 በሬድዮ ፋና ከአንድ ሰዓት ዜና በኋላ ለሚተላለፈው ፕሮግራም ትናንት ስድስት ሰዓት መልዕክቱን ለራዲዮ ጣቢያው ለማስገባት ቢሞክርም “ዘግተው ወጥተዋል፣ ሰኞ ነው የሚገቡት፡፡ ሰኞ አስገቡ” በሚል የሰማያዊ ፓርቲን መልዕክት መልሰዋል፡፡የፓርቲዎች መልዕክት ከሚተላለፍበት 36 ሰዓት ቀድሞ እንዲገባ እንደተባለ የገለጸው አቶ ዮናታን ሰኞ ጠዋት የሚተላለፍን መልዕክት “ሰኞ ጠዋት አምጡ” ብሎ መመለስ ላለማስተላለፍ እንደወሰኑ ያሳያል ብሏል፡፡

ከአሁን ቀደም ኤፍ ኤም 96.3 ሁለት ጊዜ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ አገልግሎት አንድ ጊዜ የሰማያዊ ፓርቲን የቅስቀሳ መልዕክት የመለሰ ሲሆን ይህኛው ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ (ምንጭ: ነገረ ኢትዮጵያ ፌስቡክ)

Filed Under: News Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Solomon says

    March 10, 2015 11:16 am at 11:16 am

    wowowow! This is not Ethiopian Flag.
    Why upside down?

    Reply
  2. zea says

    April 2, 2015 08:13 pm at 8:13 pm

    Yeamara qene mehonuwa new.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule