
(ፈቃዱ በቀለ)
በአቶ መለስ ዜናዊ የሚመራው የኢህአዴግ አገዛዝ ስልጣን ከጨበጠ ይኸው 21 ዐመት ሆነው። በዚህ ወደ አንድ ትውልድ የሚጠጋ የአገዛዝ ዘመን በአቶ በረከት ሰምኦን አገላለፅ „ኢህአዴግ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳሳለፈና፣ ኢኮኖሚውም በአስተማማኝ መሰረት“ ላይ እንደቆመ አብስረውልናል። እንደሚሉን ከሆነና መንግስታቸውም ሊያሳምነን እንደሚሞክረው ይህ <በፀና መሰረት ላይ የቆመው ኢኮኖሚ> አገዛዛቸው መንግስት በሚከተለው „ለልማት አትኩሮ በሰጠው የኢኮኖሚ ፖሊሲ“ አማካይነት ነው። በሌላ አነጋገር የሚሉን፣ የኢህአዴግ አገዛዝ 21 ዐመት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲያደርግ የነበረውና ዛሬም የሚያካሄደው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሌላ ሳይሆን ልማታዊ የመንግስት(Developmental State) ፖሊሲን ዋናው መመሪያው በማድረግ ነው። (ሙሉውን አስነብበኝ)
Leave a Reply