• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዛሬዎቹ ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› እና ‹‹ሆያሆዬ››

September 11, 2013 05:37 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ በዓሎቻቸውን ስለየበዓላቱ ትርጉም ባላቸው ዝማሬዎችና ጭፈራዎች ያደምቁታል፡፡ ከእነዚህ አንዱ የሆነው የዘመን መለወጫንም ‹‹እንቁጣጣሽ››ን በ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› ያደምቁታል፡፡

እንቁጣጣሽ ሲመጣ ልጃገረዶች ከበሯቸውን ይዘው በየቤቱ እየዞሩ ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› እያሉ ሲጨፍሩ፣ ድምፃዊቷ ዘሪቱ ጌታነህም በየራዲዮ ጣቢያው ‹‹እንቁጣጣሽ እንኳን መጣሽ…›› እያለች በቀጭኑ ድምጿ የምታቀነቅነው ዘፈን ሲሰማ በዓሉን ለመቀበል ያለውን ስሜት ሞቅ ሞቅ ያደርጋል፡፡

ቀደም ሲል ልጃገረዶች ‹‹አበባ አየሽ ሆይን›› ለመጨፈር ተቧድነው እንግጫ ይዘው፣ ከበሯቸውን እየመቱ ከዋዜማ እስከ በዓሉ ዕለት ይጨፍራሉ፡፡ ያኔ የነበረው ጭፈራ የግጥምና የዜማ መፋለስ ችግር አልነበረበትም፡፡ ጨፋሪዎቹም ለዓይን ሞላ ያሉ ነበር፡፡ ጨፍረው ሲያበቁም በዋናነት የሚሸለሙት ቤት ያፈራውን ስለነበር ለሳንቲምና ለብር ብዙም ቦታ አልነበራቸውም፡፡ ልጆቹም ‹‹አበባ አየሽ ሆይ…›› ሲሉ የሚጨፈርላቸው ሰዎችም ትእግስቱ ነበራቸው፣ ለባህሉም ቦታ ይሰጡ ነበር፡፡

ዘንድሮስ? የዘንድሮዎቹ የአዲስ አበባ ጨፋሪዎች ቁጥር ለዓይን የጎደሉ፣ ግጥሙንና ጭፈራውን በተሟላ መልኩ የማይገልጹ እንደሚበዙባቸው ይነገራል፡፡ ልጆቹም እየተዘዋወሩ ሲጨፍሩ የሚጨፈርላቸው ሰዎች ሊለመኑ የተመጣባቸው ስለሚመስላቸው ‹‹አድርሰናል›› ወይም ደግሞ ‹‹አያስፈልግም ሂዱ›› ተብለው ልጆቹ ይመለሳሉ፣ ይባረራሉ፡፡ በምርቃት የሚሸኙ ጨፋሪዎች ካሉ እድለኞች ናቸው፡፡

የዘንድሮዎቹ ልጆች ሙሉውን ጭፈራ እንዲጨፍሩ ዕድሉ ቢሰጣቸውም፣ ሽልማቱ ዳቦ ይሆናል የሚል ግምት አያድርባቸውም፣ ሸላሚዎቹም ‹‹ዳቦ መች ይፈልጉና›› ብለው አቅም የፈቀደውን ሳይሆን ‹‹ይሄ ይበቃቸዋል›› በሚል ስሜት ገንዘብ ይሰጧቸዋል፡፡ ከሦስት ሳምንት በፊት የተከበረው ቡሄም እንደዚያው፡፡ የቡሄንና የእንቁጣጣሽን ጭፈራ በቀደሙት ጊዜያት ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎች አሁን ላይ ያለው ጭፈራ ግጥሙም ዜማውም የተራራቀ እንደሆነ የሚናገሩትም ለዚሁ ነው፡፡

እነዚህ ባህላዊ እሴቶች ዘመን እየተለወጠ ሲሄድና ሥልጣኔ ሲመጣ አብረው የሚቀየሩ፣ የሚጠፉ ወይም የሚረሱ መሆን የለባቸውም፡፡ እነዚህ ጭፈራዎች በዓላቱ ሲመጡ ሁሌም መከናወን የሚገባቸው ኢትዮጵያዊነትን የሚገልፁ ናቸው፡፡

ለዘመናት የቆየን ባህል ስለማስተዋወቅና ለትውልድ ስለማስተላለፍ ሲወሳ የትግራይ፣ የላስታ ላሊበላና የሰቆጣ አሸንዳ (ሻዳይ) እንዲሁም የኦሮሞ ተወላጆች እያሴን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ የትግራይ ልጃገረዶች ወገባቸውን በቄጤማ ሸብ አድርገው ከበሯቸውን እየደለቁ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ የሚጨፍሩት እዚያው ትግራይ ብቻ አይደለም፡፡ አሸንዳ በተከበረበት ያለፈው ሰሞን አንዳንድ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች አሸንዳን የሚጨፍሩ ልጃገረዶችን ሲያስተናግዱ ነበር፡፡ ምሽት ላይም እንደልጅነታቸው ጸጉራቸውን የተላጩ፣ አብዛኛውን ተላጭተው የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ጸጉራቸውን ጉች ጉች ያደረጉ ጎረምሶች በየምሽት ክበቡ እየገቡ በሚያስተጋባ ጭብጨባቸው፣ በኃይለኛ በሚደልቁት ከበሯቸው ድምፅ እንዲሁም ዝላይ እየታጀቡ ሲጨፍሩ ነበር፡፡

መስቀልንም በተመለከተ የኦሮሚያ ተወላጆች የእያሴ ጭፈራን እርጥብ ሣር በመያዝ ዱላቸውን ወደ ሰማይ ቀስረው በእግራቸው መሬቱን እየደበደቡና እየዘለሉ ሁሌ በየዓመቱ ይጨፍራሉ፡፡ ልክ እንደ እያሴና አሸንዳ የአበባ አየሽ ሆይ እና ሆያሆዬ ጭፈራዎች ባህሉንና ታሪኩን በጠበቀ መልኩ ለተተኪው ትውልድ ሲተላለፉ ግን አይታዩም፡፡

ፈረንጆቹ የሃሎዊን በዓልን ሲያከብሩ ልጆቻቸው የተለያዩ አልባሳትን በመልበስ በየቤቱ እያንኳኩ ከረሜላና ሌሎች ጣፋጮችን ሲሰበስቡ ይታያሉ፡፡ ይህ ልማድ በእነርሱ ዘንድ በፊትም ነበር፣ አሁንም አለ፡፡

ብዙዎች እንደሚያምኑት የኢትዮጵያ ብቻ የሆኑት ‹‹አበባ አየሽ ሆይ›› እና ‹‹ሆያ ሆዬ››ም ለትውልድ እየተላለፉ በፊት ወደነበራቸው የግጥምና የዜማ ወግና ባህል መመለስ ሲገባቸው ይህ ሲሆን አይታይም፡፡ በርካታ ዘመናትን ተሻግረው የመጡትን ባህሎች የማሠልጠን ስሜትም ሆነ የጊዜ መለወጥ ተጽዕኖ ሊያደርግባቸው ቢገባም አጨፋፈሩ እየተቃኘ ያለው በሥልጣኔ ሳይሆን ጭራሽ ሊጣጣም በማይችል ግጥምና ዜማ ነው፡፡ ashenda

በኢትዮጵያ በፌዴራል ደረጃ፣ ክልሎችም እንደ ክልል አበባ አየሽ ሆይንም ሆነ ሆያ ሆዬን የቱሪስት መስህብ የማድረግና ባህልና ታሪኩን የማስጠበቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጠፍቶ የነበረውን የአሸንዳ ባህል ለመመለስ በዕድሜ የገፉትን እናቶች አሳትፎ ባህሉ ለዛሬዎቹ ሕፃናትና ታዳጊዎች እንዲመለስ አድርጓል፡፡ የቱሪስት መስህብ ለማድረግም ጠንክሮ እየሠራ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በሚዲያዎችና በተለያዩ አጋጣሚዎች ሆያ ሆዬም ሆነ አበባ አየሽ ሆይ ፈር መልቀቃቸው ሲነገር ዓመታት ቢያልፉም ጆሮ ሲሰጥ አልተስተዋለም፡፡ በመሆኑም የቱሪስት መስህብ ሊሆን የሚገባው ባህል እንደዋዛ እየተሸረሸረ ይዘቱን ለቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የተለያዩ ጥናቶችና መፍትሔዎች ቢቀርቡም ወደ ተግባር ሲለወጡም አይታዩም፡፡ በመሆኑም እንደነበረው ሳይሆን ከዓመት ዓመት ለዛቸውን ሲያጡና ማስተላለፍ የሚገባቸውን መልዕክት ሲሳቱ ይስተዋላሉ፡፡(ምዕራፍ ብርሃኔ)

Filed Under: Social Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule