አጼ ምኒልክ በሕይወት ዘመናቸው የሰሯቸውን ድንቅ ተግባራት በደማቅ ብእርና ብራና የተከተቡ ናቸው!
1835 ዓ.ም. ————-ወፍጮ (በ1835ዓም ገደማ የሸዋው ንጉሥ ሣህለሥላሴ ነበሩ በውሃ የሚሥራ ወፍጮ ያስተክሉት ሆኖም በደረሰባቸው ተቃውሞ ሳይሳካላቸው ቀረ:: ተቀውሞውን አሸንፈው ምኒልክ በ1893ዓም አዲስ ወፍጮ አስተከሉ)
1882 ዓ.ም. ————-ስልክ
1886 ዓ.ም. ————ፖስታ
1886 ዓ.ም. ————ባህር ዛፍ
1886 ዓ.ም. ————ገንዘብ
1886 ዓ.ም. ———-የውሃ ቧንቧ
1887 ዓ.ም. ———–ጫማ
1887 ዓ.ም. ————–ድር
1887 ዓ.ም. ————-የሙዚቃ ት/ቤት
1887 ዓ.ም. ———-የፅህፈት መኪና
1889 ዓ.ም. ———-ኤሌክትሪክ
1889 ዓ.ም. —————ዘመናዊ ህክምና
1889 ዓ.ም. ————-ሲኒማ
1889 ዓ.ም. ————–የሙዚቃ ሸክላ
1889 ዓ.ም. ————-ቀይ መስቀል
1890 ዓ.ም. ———–ሆስፒታል
1893 ዓ.ም. ————-ባቡር
1893 ዓ.ም. ————-ብስክሌት
1896 ዓ.ም. ————-መንገድ
1897 ዓ.ም. —————ፍል ውሃ
1898 ዓ.ም. —————ባንክ
1898 ዓ.ም. ————-ሆቴል
1898 ዓ.ም. ————-ማተሚያ
1898 ዓ.ም. ————–ላስቲክ
1899 ዓ.ም. ————አራዊት ጥበቃ
1899 ዓ.ም. ———–የጥይት ፋብሪካ
1900 ዓ.ም. ————-ጋዜጣ
1900 ዓ.ም. ————አውቶሞቢል
1900 ዓ.ም. ———–የሚኒስትሮች ሹመት
1901 ዓ.ም. ———–ፖሊስ ሰራዊት
1904 ዓ.ም. ———የመድሃኒት መሸጫ ሱቅ
አጼ ምኒልክ የኢትዮጵያ መሐንዲስ!
ክብር ለቀደሙት አባቶቻችን!
ፍቅሩ ኪዳኔ
Tadesse says
It is nice,every body/the kings Teodros and Yohannes have done what was possible in their time too,I have never disliked any of our passed kings.
Getachew Selassie says
አጼ፡ምኒልክ፡የተወለዱት፡በፈረንጆቹ፡አቆጣጠር፡ (Aug.17, 1844)
ከሆነ፡የወፍጮው፡ቀን፡ልክ፡አይመጣም።
Editor says
Getachew Selassie
ጉዳዩ እንደዚህ ነው:
የሸዋው ንጉሥ ሣህለሥላሴ ነበሩ በ1835ዓም ገደማ በውሃ የሚሠራ ወፍጮ ያስተከሉት። ሆኖም ድርጊቱ የሠይጣን ሥራ ነው ብለው ቀሳውስት በመቃወማቻቸው እና በዚህ ወፍጮ የተፈጨውን የበላ የሰይጣን አገልጋይ ነው ብለው በመገዘታችው ወፍጮው ፈራርሶ ወደቀ። ቀጥሎም አጼ ቴዎድሮሰ ወፍጮ እንዲያስተክሉ ቢነገራቸውም “የሴቶቻችንን ክንድ ምን ልናደርግበት ነው?” ብለው ከለከሉ። አጼ ዮሐንስ ግን ጉዳዩ ጠቃሚ መሆኑን ተገንዝበው በጉዞ ላይ ፈጪ ሴቶችን ከማጓጓዝ የሚረዳን ነው ብለው ወፍጮ ለማስገባት ቢሞክሩም በሣህለሥላሴ የደረሰው ተቃውሞ በሳቸውም ላይ ደረሰባቸው። ሆኖም ማንኛውንም ተቃውሞና ውግዘት አሸንፈው ወፍጮን ያቋቋሙት ምኒልክ ናቸው።በአድዋ ዘመቻ ጊዜ ጓዙን ያበዛው የፈጪና የወፍጮ ጭነት መሆኑን ያስተዋሉት ምኒልክ በ1893ዓም በስቴቬኒ አማካኝነት ለራሳቸው ወፍጮ አስተከሉ። ወፍጮው የሚፈጨው በሰይጣን ሳይሆን በሰው መሆኑን ለማሳየት ምኒልክ ወፍጮው ቤት እየሄዱ በአስፈጪነት ተግባር ተካፋይ ሆኑ።ንጉሡ ግብር በሚያበሉበት ጊዜም መኳንንቱና ካህናቱ ሰይጣን በፈጨው ዱቄት የተሰራውን እንጀራ አንበላም ሲሉ ምኒልክ ደግሞ በእጅ በተፈጨ ዱቄት የተሰራውን አልበላም አሉ። ምክንያታቸውን ሲያስረዱም “…ፈጫዪቱ በምትፈጭበት ጊዜ ንፈጧ ሲመጣ ተናፍጣ ወዲያው ትፈጫለች ኩሷን ጠርጋ ወዲያው ትፈጫለች። . . . ለዚህ ነው በንፁህ ድንጋይ የተፈጨውን የመኪናን ዱቄት የምንወደው …” ብለው ነበር። ታሪኩ በዚህ አያበቃም በዱቄቱ አሁን “የፈረንጅ ዳቦ” የሚባለው እንዲሠራና እንዲሸጥ ያደረጉት እርሳቸው ናቸው። (ምንጭ: የጳውሎስ ኞኞ “አጤ ምኒልክ” ገጽ. 337-338)
ለሰጡት አስተያየት ከልብ ለማመስገን እንወዳለን – እንደሚገባው አስተካክለናል። እዚህ ላይ ሁሉም አልሰፈረም እንጂ የእምዬ ምኒልክ ሥራ በበርካታ አንደኛዎች የተሞላ በመሆኑ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይመስልም።
የጎልጉል አርታኢ
Getachew Selassie says
ከልብ፡የመነጨውን፡ምስጋናዬን፡አቀርባለሁ።
በጣም፡በጣም፡አድርጎ፡ነው፡የየዋህ፡ሃገሬ፡ሕዝብ፡
ያሳቀኝ።
አስተሳሰብ፡አኔም፡በመጠኑ፡ደርሶብኛል።
ከተግባረዕድ፡ስመደብ፡ነፍሷን፡ይማረው፡ወላጅ፡
እናቴ፡ዘር፡ልታሰድብ፡ነው፡ወይ?ብላ፡ተጨቃጭቀናል።
ለዚህ፡እኮ፡ነው፡አገራችን፡በሳይንስና፡በቴክኖሎጂ፡
ወደ፡ኋላ፡የቀረችው።
ሰለ፡ጣፋጭ፡መልሳችሁ፡
እግዚአብሔር፡ይስጥልኝ።
Mulugeta Andargie says
ለመሆኑ የኔን ኮሜንት የት አደረሳችሁት??? ዴሞክራሲ እንደዚህ ነው???
Editor says
እዚህ ውስጥ ነው ያለው
አርታኢ