‘ባካችሁ ……… ’ባካችሁ……….
እናንት በምድረ–ኢትዮጵያ ያላችሁ፤
“አትሂዱ …..በ‘ግራችሁ…”
ከቻላችሁ ….. “ብረሩ ክንፍአው’ታችሁ።”
ግን……..አደራ……….. ……….
አንዳትረገጡት ……. መሬቱን
እንዳታዩት……… አፈሩን፤
ብታርሱት…… አትዘሩበት
ብዘሩበት …….. አይበቅልበት፤……..
ደምነውና – የትላንና– የዛሬ – የአሁን፣ ትኩስ…. የፈሰሰበት
አጥንት ነውና ያልደረቀ፣ “አጸደ–ህይወት” የወደቀበት
እናንተም ከእንግዲህ፣ ”ዐጽም – ‘ርስቴ” የማትሉት፤………..
ያውም ………………………………..
የባቶቻችሁ፣……..የናቶቻችሁ
ያውም………………………………
የወንድሞቻችሁ፣……..የህቶቻችሁ
ያውም……………………………………
የእቦቀቅላወቹ፣……የታዳጊወቹ፣……..የልጆቻችሁ፤
ዓይናችሁ እያየ፣…….እየሰማጆሮ‘ችሁ
የተመቱ! …የቆሰሉ!….. የተወጉ! …. የተፈነከቱ!…..
የተቀጠቀጡ!…. የተዘለዘሉ!……! ……የተረሸኑ!
…..በገዛ ወገኖቻችሁ………..
ያውም …………”ወገንእኮነን “እያላችሁ።
በደመዋልባችሁ……………………………….
“ኤሉሄ …..ላማሰበቅተኒ!”……. ብላችሁ
ወሰን – ድንበር ለሌለው ሰቆቃችሁ
ብትነግሩትም “ለሰማይአባታችሁ”፤
ግን….. ለምንም– ለማንም አይመችም
ሀዘናችሁ መልክ የለውም……….
ያልተነገረ እንጅ፣ ያልተፈጸመባችሁ ግፍ የለም።
ብትጎጉጡ፣ ደም አልቅሳችሁ፣….. እየየ …ብላችሁ –
ቢያዳርስም ዓለም ….. ሲቃ – ዋይታችሁ …
መቼም– መቼም ቢሆን፣ ምንጩ አይደርቅም የ‘ምባችሁ::…..
እናማ………………………………………..
ሰላም፣ ፍትህ፣ እኩልነት – ሳታሰፍኑ – በመሀከላችሁ
አንድነትንሳታነግሱ – በምድራችሁ
ይቅር ሳትባባሉ፣ ‘ርስ–በርሳችሁ
ሳይመለስ ክብራችሁ፣ ጠፈር – ድንበራችሁ
የድልችቦው – ከፍሳይል፣ ክብር ሰንደቅዓላማችሁ፤……
የወገናችሁን ደምና– አጥንት እንዳትረግጡት
“ይወጋችሁልና እሾኽ ሆኖ፣ የኢትዮጵያ ዐፈር – መሬት!”።
———//———
ፊልጶስ/ ነሀሴ 2008
E-mail: philiposmw@gmail.com
Leave a Reply