ሰላሙ የደፈረሰበት ህዝብ የመንፈስ ጤንነት አይሰማውም። ሰላምና ጤና የሚነጣጠሉ አይደሉምና፤ የመንፈስ ጤንነት የደፈረሰበት ህዝብ ጤናማ ነው ማለት አይቻልም። “ሰላም ሳይኖር ሰላም የሚሉ ወዮላቸው!” ከሚለው ከነብያት ቃል ጋራ ተጋጨ። ይህም ብቻ አይደለም። ሰላም የሌለን ቄሶች ሰላም እንደሌለን እያወቅን፤ የተቀጠርንለት እለታዊ ገቢያችን እንዳይቀርብን “ ሰላም ለኩልክሙ” እንላለን። በጥቅሉ ልማድ አድራሾች ሆን። የተዋህዶ እምነት ተከታዮች ነን የምንል ኢትዮጵያውያን ሰላም ምንጭ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሊወሀደን ቀርቶ አልተቀበልነውም። ከዚህ ዓመት የደረስነው አሁን ያለንበት “በደብረ ሰላም ኢይኩን ሀከክ” ማለትም፦ በደብራችን ህውከት ብጥብጥ አይኑር” እያልን ጉሮሯችን እስኪሰነጠቅ የምንጮኸው ላምድ ለማድረስ ብቻ ነው። ስለዚህ “እንኳን አደረሳችሁ” እንጅ “እንኳን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ” ማለት መዋሸት ነው።
አምና መስከረም ፳፻፬ ዓ.ም. (September) 24, 2014 07:07 ደመራ በሚል ርእስ “በሃይማኖታችን፥ በታሪካችንና በባሕላችን አንጻር” አቅርቤው በየድረ ገጾች ተነቧል። የደመራው በዓል የዘመን ርቀት ያማስረሰው በያመቱ የሚታወስ ቢሆንም፤ በእሌኒ ታሪክ ብቻ ተሸፍኖ ሰረዛዊ ታሪክነቱ (ኢትዮጵያዊነቱ) ተሰውሯል። በዚህ ዓመት የገጠመንን እንቃኝበት ዘንድ፤ አምና የተሰወረው ታሪካችን ለማንጸባረቅ “በታሪካችንና በባሕላችን አንጻር” በሚል ርእስ ስለደመራ በዓል አቅርቤ ነበር። ሙሉውን ለማንበበ ከፈለጉ ወደ ከንሳስ መድኃኔ ዓለም ድረ ገጽ በመሻገር ያገኙታል። ዘንድሮ ደግሞ የገጠመንን ለማንጸባረቅ አምና ካቀረብኩት ጨልፌ እንዳቀረብላችሁ ያለንበት ሁኔታ አስገደደኝ ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply