
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የህውሓት ቡድን ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን አውሮፕላን ማረፊያን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።
በርካታ ህወሓት ያደራጃቸው የልዩ ኃይል፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሠራዊት እጃቸውን እየሰጡ መሆናቸውም ታውቋል።
ሠራዊቱ ዘራፊው የህወሓት ቡድን ያደረሰበትን ድንገተኛ ጥቃት በመመከት የመልሶ ማጥቃት ስራ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት እስካሁን ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ መቆጣጠሩ ይታወቃል። (ፋና)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
የአማራን ክልል ኤርፖርት የመክላክያ ሰርዊት የሚቆጣጠርበት ምክንያት አልገባኝም? ወይስ አማራ ክልል ከወያኔ ጋር ተሻርኮ ለወያኔ እኩይ ሥራ መገልገያ ኤርፖርት እንዲኖረው አድርጓል? ማብራሪያ ስጡበት በማርያም!
የመጀመሪያው የዜናው አንቀጽ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። 🙂
አርታኢ
መጠራት ያለበት እንደ ሀገር በመከላከያ ስም መሆን ስላለበት ነው እንጂ ኤርፓርቱን ጨምሮ አጠቃላይ ከተማውን የተቆጣጠረው በርካታ ተዋጊዎችን ያሰለፈው የአማራ ልዪ ሀይል ነው፡፡ ነገር ግን የአማራ ልዪ ሀይል የአየር ላይ ትራንስፓርት ስለማይጠቀም የኤርፖርት ሜዳውን የመከላከያ ሄሊኮፕተሮችን ነው እያስተናገደ ያለው፡፡