• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሐጃጆች ሞት

September 25, 2015 12:06 am by Editor Leave a Comment

ለሐጅ ጉብኝት የተጓዙ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ምዕመናን ትናንት ሚና-ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ድንገት በመሞታቸዉ የሐገራት መሪዎችና የድርጅት ተጠሪዎች የሚያስተላልፉት የሐዘን መግለጫ፤ የሐይማኖት መሪዎች ፀሎት ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። በአደጋዉ 717 ሰዎች ሞተዋል፤ ከ800 በላይ ቆስለዋል። የሳዑዲ አረቢያ ገዢዎች የአደጋዉ ትክክለኛ መንሥኤ እንዲጣራ አዘዋል።ኢራን ግን ለአደጋዉ የሪያድ ነገሥታት ሐላፊነቱን እንዲወስዱ አሳስባለች።በሐጂ ጉብኝት ወቅት ተደጋጋሚ አደጋዎች ቢደርሱም በርካታ ሠዉ የሞተበት አደጋ ሲደርስ በሃያ-አምስት ዓመት ዉስጥ የትናንቱ የመጀመሪያዉ ነዉ።

ከመካዉ ዓል-ሐራም እስከ ሞስኮዉ ካቴድራል፤ ከምሥራቅ ለንደኑ እስከ ካይሮዉ አል-አዝሐር፤ ከካምፓላዉ ቃዛፊ፤ እስከ እየሩሳሌሙ ዓል-አቅሳ፤ ከዓለም መሳጂዶች የሚንቆረቆረዉ ዱዓ፤ምልጃ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ከዋይት ሐዉስ እስከ ክሬምሊን ያሉ አብያተ-መንግሥታትም የሐዘን መግለጫዉን እያጎረፉት ነዉ።የሐገራት፤የድርጅቶችና የሐይማኖት መሪዎችም እንዲሁ።

በዱዓ፤ ሐዘን፤ የመፅናናት ምኞቱ መሐል ብቅ፤ ጥልቅ፤ የሚለዉ ጥያቄ ግን እስካሁን ትክክለኛ መልስ አላገኘም። በዚሕ ዘመን፤ ባንዴ፤ ያን ያሕል ሕዝብ እንዴት አለቀ? የአይን ምሥክሩም አልገባቸዉም።

«ምንም ሊገባኝ አይችልም። እንዲሕ አይነት አደጋ የሚደርስበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይገባም። ባካባቢዉ ሰዉ የሚያድሩባቸዉ ድንኳኖች ናቸዉ ያሉት። (ጀመራት) ድልድይንም መጓዝ ያለባቸዉ ባንድ አቅጣጫ ነዉ።ባንድ አቅጣጫ ነዉ የሚዞሩት፤ ወደ ኋላ መመለስ፤ መቆምም አይችሉም።» ሌሎች እንዲሕ ይተርካሉ ድንኳች የተተከሉባቸዉ ጎዳና ቁጥር 204 እና ጎዳና ቁጥር 223-ጀምራት ድልድይ አጠገብ ይገናኛሉ።

እንደ ትናንቱ ባይሆን ኖሮ፤ ምዕመናን ድልድዩ ላይ ሆነዉ ሰይጣንን ለመደብደብ ተምሳሌት ጠጠር ይጥሉበታል። ትናንት ግን ከቁጥር 204 ጎዳና የተነሳዉ የሕዝብ ማዕበል እና ከቁጥር 223 የሚተመዉ ሌላ ማዕበል ሁለቱ ጎዳኖች እሚገጥሙበት ሥፍራ-ሲደርሱ ይላታማሉ።ከዚያ–ትርምስ፤ ግጭት፤ ጩኸት—እና እልቂት።

በሕዝብ መጨናነቅ፤ መገፋፋት፤ መረጋጋጥ፤ በቃጠሎ፤ ሌላ ቀርቶ በግንባታ ክሬን መዉደቅ -በዚያ ቅዱስ ሥፍራ፤ ሰዉ ሲሞት ሲቆስል ያሁኑ በርግጥ የመጀመሪያዉ አይደለም። ሰኔ 1982 በደረሰ አደጋ 1426 ሐጃጆች ካለቁ ወዲሕ በርካታ ሰዉ ሲሞት ግን የትናንቱ የመጀመሪያዉ ነዉ።717 ሰዉ—-ለዚያራ በተከናነባት ጨርቅ እንደ ምሳሌዉ ተከፈነባት። 8 መቶ ቆሠለ።

የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ግድም 364 ሰዉ በተመሳሳይ አደጋ ከሞተ ወዲሕ የሁለቱ ቅዱስ ሥፍራዎች የበላይ ጠባቂ የሚባሉት የሳዑዲ አረቢያ ነገስታት በተለይ መጨናነቁን ለማስተንፈስ፤ ተጨማሪ ድልድዮች፤ መንገዶችና መሿለኪያዎች ማስራታቸዉን፤ የኮሚፒዉተር መቆጣጠሪዎች ማስተከላቸዉን፤ በርካታ የአደጋ ተከላካይ ሠራተኞች ማስማራታቸዉን በየዓመቱ ይናገራሉ። ትናት የሆነዉ-ለምን ሆነ ታዲያ?

ንጉስ ሳልማን ይጣራል ነዉ መልሳቸዉ። «አሳዛኝ አደጋ ነው። የሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩን በተቻለ ፍጥነት አጣርተዉ ውጤቱን እንዲያሳውቁን አዘናል። የምዕመናን ደህነነት ለማስጠበቅ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ።» የንጉሱ የጤና ሚንስትር ግን «የጉዞዉን ደንብና ሥርዓት ያላከበሩ ምዕመናን የፈጠሩት ትርምስ» የሚል መልስ ሰጥተዋል። በየዓመቱ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ የሚያስተናግድ መንግሥት ጥንቃቄ፤ ምክር፤ ዝግጅቱ እልቂት አለማስቀረቱ ብዙዎችን ማሳዘኑ አልበቃ ያለ ይመስል፤ ባለሥልጣናቱ በምዕመኑ ማሳበባቸዉ ማስተዛዘቡ አልቀረም። የኢራን መሪዎች ከመታዘብም አልፈዉ የሪያድ ነገስታት የመካና መዲና «የበላይ ጠባቂ ነን» እንደሚሉት ሁሉ ለአደጋዉም በበላይ ሐላፊነት መጠየቅ አለባቸዉ ባዮች ናቸዉ።

ታዛቢዉ ደግሞ፤ «በቂ ፀጥታ አስከባሪ ወይም ሥርዓት አሲያዥ ቢኖር ኖሮ፤ ሕይወት አድን ሠራተኞች ፈጥነዉ ቢደርሱ፤ ከሁሉም በላይ ተጨማሪ ማስፋፋት ቢደረግ ኖሮ-ያ ሁሉ ሕዝብ ባላለቀ ነበር» ይላሉ።«ሚና ተጨማሪ የማስፋፊያ ግንባታ ያስፈልገዋል። መንገዶቹ መስፋፋት፤ ድንኳኖቹም ተራርቀዉ የሚተከሉበት ሥልት ሊኖር ይገባ ነበር። (ከእንግዲሕም) የሆነ የምሕንድስና ሥራ-መሠራት አለበት።» የሟቾቹ ዜግነትና ብዛት ቀስበቀስ ይፋ እየሆነ ነዉ።

እስካሁን የመጀመሪያዉን ሥፍራ የያዙት ኢራኖች ናቸዉ። 131 ሞሮኮ 87 ሕንድ 14። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እንዳለዉ ኢትዮጵያዉያንም ሞተዋል። ቁጥራቸዉ ግን ገና በይፋ አልተነገረም።

(Deutsche Welle: ነጋሽ መሐመድና አርያም ተክሌ)

Filed Under: News Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule