
አርብ ዕለት በአቶ ዳውድ ኢብሣ የሚመራ “የአስር ድርጅቶች” ኅብረት ፈጸሙ መባሉ ብዙም ሳይቆይ ስምምነቱን ከፈረሙት መካከል አንዱ ነው የተባለለት የአገው አገር አቀፍ ሸንጎ በስምምነቱ ላይ እንደሌለበት አስታውቋል።
ሸንጎው ባወጣው መረጃ መሠረት ሸንጎው ውኅደት ማድረጉን አስመልክቶ ደጋፊዎቻቸው ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑን በመጥቀስ የሰጠው ምላሽ “በዚህ ዙሪያ ከብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ጀምሮ እስከ ዞንና ወረዳ ውይይት” ያልተደረገበት መሆኑን በመጥቀስ በኅብረት ስምምነቱ ላይሸንጎው እንዳልተገኘ ገልጾዋል።

በተመሳሳይ ዜና ህወሓት “የፌዴራሊስት” ጉባዔ በማለት በመቀሌ ጠርቶት በነበረ ስብሰባ ላይ ከደብረጽዮን በስተቀኝ አንድ ወንበር ቀጥሎ ተቀምጦ የሚታየው በፊት ለፊቱ “የአገው ተወካይ” የሚል ቢሆንም ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት የአገው ማኅበረሰብ ተሰብስቦ ተወካይ እንደማይልክ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
በዚሁ የመቀሌ ስብሰባ ላይ “ኦነግን ወክዬ ነው የመጣሁት” ያለውን ግለሰብ የአውራምባ ታይምስ ባለቤት ዳዊት ከበደ ቃለመጠይቅ ካደረገለት በኋላ በእርግጥ የኦነግ ተወካይ መሆኑን ለማጣራት ወደ ኦነግ ደውሎ ያገኘውን ተስፋ የሚያስቆርጥ ምላሽ በትግሪኛ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዲህ ብሎ ማስፈሩ ዘግበን እንደነበር ይታወሳል፤
የትግሪኛው ትርጉም እንዲህ ይላል፤ “ኦነግን ወክየ ነው የመጣሁት ያለኝ ኣንድ ወጣት ፖለቲከኛን ቃለመጠይቅ ኣድርጌ ነበር፤ ሆኖም ግን ቪድዮውን ከማስተላለፌ በፊት የተላከው ወኪል በትክክል የኦነግ ወኪል መሆኑን ለማረጋገጥ ወደ ኦነግ ጽህፈትቤት ደውዬ ያገኘሁት መልስ በጣም የሚያሳዝን ሆኖ ኣገኘሁት። እንደዚህ የሚባል ስም በአመራር ደረጃም ይሁን በኣባል ደረጃ የለንም፣ በመሠረቱ ወደ መቀለ ስብሰባ አንዲሳተፍ የላክነው ወኪል የለንም ብለው ኣሳፈሩኝ፤ ህውከት፣ ድካም ብቻ ነው ያተረፍኩት። በሉ ኣበሉን ስጡትና ላኩት”።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
በቲፒልፈም ሆነ በኦነግ የተሰባሰበው ስብስብ የሸ ፍጥ የቂም በቀልና ተንኮል አዘል በመሆኑ እንደ ባቢሎን ግንብ በጧቱ መደርመስ መጀመሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ተሰፋ ነው፡፡ በ እውነትና በእወቀት ላይ የተመሰረቱ ፓርቲዎች ሊበረታቱ ሊጎለምሱ ይገባል እንጂ ሽፈጥ አዘል ፓርቲዎች በአይነ ቁራኛ ሊታዩ ይገባል፡፡ ምክንያቱም አለመረጋጋትን የህዝብ መፈናቀልን የ እርስበ እርስ ጦርነትን በመጨረሻም ርሃብን ስደትን ማስከተላቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡