ታዳጊ ወጣት ሐና ላላንጎን ደፍረው ለሕይወቷ ማለፍ ምክንያት ሆነዋል የተባሉ አምስት ተከሣሾች ተፈረደባቸው፡፡
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በተበየነባቸው ወንጀለኞች ላይ ያሣለፈው ከ17 ዓመት እስከ 20 ዓመት የሚደርስ የእሥራት ቅጣት ነው፡፡
በዚህም መሠረት አንደኛና ሁለተኛ ተከሣሽ ሣምሶን ሺበሺና በዛብህ ገብረማርያም በሃያ ዓመት እሥራት፣ ሦስተኛ ተከሣሽ በቃሉ ገብረመድህን በ17 ዓመት እሥራት፣ አራተኛ ተከሣሽ ኤፍሬም አየለ በሃያ ዓመት እሥራት፣ አምስተኛ ተከሣሽ ተመስገን ፀጋዬ በ18 ዓመት እሥራት እንዲቀጡ ችሎቱ ፈርዷል፡፡
አንደኛና ሁለተኛ ተከሣሾች ፍርዱ ከተሰማ በኋላ ችሎቱን ዘልፈዋል፡፡
የሃና ላላንጎ አባትና የቅርብ ዘመዶቿ በቅጣቱ እንዳልረኩ ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን ዘገባ እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡ (መለስካቸው አመሃ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)
Dejene M says
ምንም አላጠፉም ፍርዳቸዉ ስላጠረ ነዉ እንጅ ሞት ብሆን ኖሮ እንደዝህ አይዘልፉም ነበረ ሌላ ፍርድ እድል ካሌ ከፍ ይበል !