ፊታቸው ላይ የአልበገርም ባይነት ስሜት ጎልቶ ይነበባል፤ እያነከሱም ቢሆን ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ። መገናኛ ራዲዮናቸውን እና የምርኩዝ ከዘራቸውን ይዘው የጁንታው ቡድን አመራር ያለበት ቆላ ተንቤን አቅራቢያ በምትገኝ ሰዋራማ ስፍራ ላይ ጦሩን እየመሩ ይገኛል።
ኮሎኔል ሻምበል በየነ ይባላሉ። በቆሙበት የውጊያ ትዕዛዝ እየሰጡ ኮስታራ ፊታቸውን ወደእኛ ዘወር አደረጉ። ቆስለው አልታከምም በማለት በወኔ እየመሩ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራር መሆናቸውን ሰማንና ታሪካቸውን እንዲያካፍሉን ጠየቅናቸው።
ድንገተኛ ፈገግታ እያሳዩ ቀድሞም የጁንታው አባላት ውጊያ ሰራዊቱ ላይ ሊከፍቱ እንደሆነ ጥርጣሬ ነበረኝ በማለት በተረጋጋ ስሜት ትውስታቸውን ማጋራት ጀመሩ። እኔ የ31ኛ ክፍለጦር ምክትል የኦፕሬሽን አዛዥ ነበርኩ ዋና አዛዡ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቀደም ብሎ የተወሰኑ አባላትን ሽሬ ድረስ ወስዶ ሲሰበስብ የሆነ ነገር ሊፈጥር እንደሚችል አስበው እንደነበር።
ማታውኑ ችግር ሊኖር እንደሚችል በማመን በግሌ ዝግጅት አደረግኩ። ስዘጋጅ በባንክ አካውንቴ የነበረውን ጥቂት ገንዘብ በቤተሰብ አዞርኩ። ከዚያም ጥቃት ለማድረስ ከበባ ሲፈጽሙብኝ ተከብቤያለሁ በሚል ለበላይ አካላት ሪፖርት አደረኩ ።
በመከላከያ ላይ ጥቃት ሲፈጸምም የክፍለጦር አዛዡ ከድቶ የጁንታውን ቡድን ተቀላቀለ። በዚህ ጊዜ የክፍለጦር ኮሚቴ ወይም ከበታች አዛዦች አባላት ጋር በመሆን ግብግብ ፈጸምን። እኔም ከፊቴ ያለውን በጥይት መትቼ ጣልኩ። እኔ ጋር የተጀመረች የመከላከል ተኩስ እስከታችኛው የሻለቃ አመራር ድረስ እየተደማመጠ የመከላከል እርምጃውን ወሰደ።
በኋላም የካምፑን ከበባ አጠናቅቄ ስወጣ ደግሞ የልዩ ኃይል ከውጭ ጠበቀኝ የሚሉት ኮሎኔል፤ እነሱንም ጥሼ በመውጣት ከስምንተኛ ሜካናይዝድ ጦር ጋር ተቀላቀልኩ ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሱታል።
በወቅቱ እግራቸው ላይ በጥይት መመታታቸው እምብዛም ቁብ አልሰጡትም። በዚያ ሁኔታ ላይ እያሉ ወደኤርትራ በማፈግፈግ በዚያ ከሚገኘው እና በጁንታው ታጣቂ ጥቃት ደርሶበት ከሚገኘው ጦራቸው ጋር ተገናኙ። ጦሩን አደራጅተው በመመለስ ሽራሮ ፣ሽሬ፣ አዲ አደራይ፣ አዲነብሪ እና በርካታ ቦታዎች በማስለቀቅ የህግ ማስከበር እርምጃቸውን በብቃት መወጣትም ቻሉ።
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከታፋቸው የሚፈስ ደም እንደ ነበር በቅርበት የሚያውቋቸው ወታደሮች ይናገራሉ። ቁስሉን በየሶስት ቀኑ በጦር ሜዳ አካባቢ እየታከምኩ አንዷ ጥይት ወጣች የሚሉት ኮሎኔል ሻምበል፤ ምርኩዝ ይዘው ግዳጃቸውን መወጣታቸውን ነግረውናል። ዋና አዛዡ ግን የጁንታውን ቡድን በመቀላቀል ለጁንታው አመራር ሽፋን ለመስጠት ጥረት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
አሁን ላይ ቆላ ተንቤን ላይ ወንጀለኛ ለማስመለጥ እና ወንጀለኛ ለመያዝ ዋናው እና ምክትል አዛዡ ፊት ለፊት ተፋጠዋል። ምክትል አዛዥ ዋናውን ከነጀሌዎቹ እያባረረ እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል። ከሚመሩት ጦር ጋር በርካታ ሀገር የከዱ ጄኔራሎችን እያባረሩ ቆላ ተምቤን ላይ ያደረሱት ኮሎኔል ሻምበል፤ እዚህ በመድረሴ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል ሲሉ በኩራት ይናገራሉ።
ቆላ ተምቤን ላይ የመሸገውን የከሃዲው ቡድን አመራር አባላት ለህግ ሲቀርቡ በተሻለ ህክምና በጥይት የተመታውን እግራቸውን ሊታከሙት እንደሚችሉ እንደተወርዋሪ ኮኮብ መሳይ ብልጭታ ባለው ፈገግታቸው ታጅበው በለሆሳስ ነገረውናል። ቦታው ላይ ቆስለውም ቢሆን ጦሩን እየመሩ መገኘታቸው ለሰራዊቱም ብርታት መሆኑን አልሸሸጉንም።
በእጃቸው ከዘራቸውን ጨብጠው የሚንቀሳቀሱት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፤ በጉዳት እያሉም ቢሆን በህግ ማስከበር እርምጃ የጁንታውን አመራሮችን ለመያዝ ፀሐይ ውርጭ ሳይሉ በመታገል ላይ ናቸው። ይህም ኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆችን በየጊዜው አታጣም የሚባለው ብሂል እውነት መሆኑን ያረጋገጠ ነው። (ጌትነት ተስፋማርያም፤ አዲስ ዘመን ህዳር 28/2013 ዓ.ም)
Tesfa says
የዚህን ቁርጠኛ ወታደር ንግግር ደጋግሜ ሰማሁት። ተው ብየው ነበር ይሉናል። ይገርማል እንደሚታረድ በግ ገመዳቸው ሲዘጋጅ እያዪ የኖሩ የሃገሪቱ የቁርጥ ቀን ልጆች። ስንቶች ቆመው ስንቶች በወያኔ ጥይት ወደቁ? ወያኔዎች እብዶች ናቸው። ትላንትም ዛሬም በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ገመና ከማመንጨት የተለዬ በሰላም ሰርተውና ኑረው አያውቁም። ለምን ቢባል በእጃቸው የሰው ደም ስላለ ውስጣቸው ሰላም የለውም።
የ 6 ወር ህጻን ልጅ የማያስበውን ነው ወያኔ አስቦና ተዘጋጅቶ የሰሜኑን ጦር ያጠቃው። ጉራ ጥሩ አይደለም። የሮም አወዳደቅን ያመጣል። ሞሶሎኒን ተዘቅዝቆ እንዲሰቀል ያደረገው ይህ አይነቱ ድንፋታ ነው። ወያኔም አልጠግብ ያለ ሲተፋ ያድራል እንዲሉ ኢትዮጵያዊነትን ክዶ ይህን ሰይጣናዊ ተግባር መፈጸሙ ከበረሃ እስከ ከተማ የነበረውን ባህሪ ገሃድ አውጥቶታል። የትግራይን ህዝብ ሚትህን፤ መሬትክን፤ እህልክን የሚዘርፍና የሚደፍር መጣብህ በማለት ህዝቡ እንዲበረግግ አድርጓል። የሚያሳዝነው የእህል ክምር የሚያቃጥል፤ ጎተራ ያላችሁን እህል የሚቀማ ስለተባሉ ገበሬዎቹ መሬት ቆፍረው እህሉን መቅበራቸውን ይናገራሉ። ግን አሸባሪው ወያኔ በበረሃ ጊዜ የተጠቀመበትን የሻገተ ሃሳብ ዛሬም ሊጠቀም ሲሞክር በቁርጠኛ የሃገሪቱ ልጆች ድባቅ ተመቷል። እኔ ለወያኔ አፍቃሪዎችና ወያኔዎች አዝኜ አላውቅም። ግን አንድ አንድ ጊዜ የምሰማው ነገር ከሰዎች ያበሳጨኛል። ወያኔ ይህን ይሰራል ብየ አላምንም ነበር አለኝ አንድ በነጭ ሃገር የሚኖር ጓደኛዬ። የሰው ጥፍር ሲቀርፍ፤ በቆለጥ ላይ ውሃ ሲያንጠለጥል፤ በሴትና በወንድ ሰውነት ላይ ሲጠዳድባቸው፤ ሰዶማዊ ስራ ሲፈጽሙ፤ በሴቷ ብልት ያልሆነ ነገር ሲከቱ ስትሰማ ምን ብለህ ነበር ያኔ አልኩት። አዘንኩ አለ። ይገርመኛል። የሰው ልጅ ስብ ዕና መለኪያው እኮ ተግባሩ ነው። ወያኔ በሱማሊ ክልል በወገኖቻችን ላይ የፈጸመው በደል እጅግ ከሰው ፍጥረት የወጣ ነው። ግን በእንደመር ሂሳብና በማባበል ፓለቲካ ተሸፋፍኖ በመቅረቱ ዛሬ አብሮ የኖረውን ሰራዊት ከውስጥና ከውጭ በወያኔ የትግራይ ተወላጆች በተኙበት ፈጃቸው። አሁን ነፍሴ አውጪኝ ብሎ የፈረጠጠው ደብረጽዪን በአንድ ወቅት ልጁ ” ለምን ወለድከኝ” ብላ እንደ ጠየከችው ሲናገር መልስ አልነበረኝም። ያው ያልኳት ጊዜዪ ለህዝብ ነው አልኳት ብሏል። ውሸት ነው። መውጫውን ሲያስቆፍር ነው የሚያመሸው የነበር። በህዝብ ስም መነገድ የወያኔ ብቻ ሳይሆን የፓለቲከኞች ሁሉ በሽታ ነው። ወያኔ ግን የተካነበት ሙያው ሰውን እርስ በርስ ማጋደል፤ በዘርና በቋንቋ ሰውን መከፋፈል፤ ብሎም መዝረፍና ሰውን መሰወር፤ መግደል ነው። በማይካድራ የተሰራው በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች በተላላኪዎቻቸው የኦነግ ሸኔ አሽከሮች ያስፈጸሙት ነው። አሁን ለምን ሃጫሉን እንዳስገደሉት፤ ለምን ጃዋር የድረሱልኝ ጥሪ አሰምቶ ሰው እንዳስጨረሰ፤ ለምን በሻሸመኔና በሌሎች የሃገሪቱ ክፍል ሰው እንደ እንስሳ እንደተገደለ ፍንትው ብሎ ይታያል። የዶ/ር አብይ መንግስትን በዚህም በዛም አጣቦ ወያኔ በትግራይ የሰሜን ጦርን ለመምታት ዝግጅቱን ለማጠናቀቅ ረድቶታል። ለዚህም ነው ጦሩ ሳይቀር ወደ ከተማ ሲገባ እየተፈተሸ ይገባ የነበረው። በዘሩ የሰከረው ወያኔ ይኮራበት የነበረውን ጦሩን አስጨርሶ፤ በየስፍራው የተሰገሰጉ ወታደሮችን አስኮብልሎና አታሎ በባዶነት በእርጅና በበረሃና በሰው ሃገር እንዲንከራተቱ አድርጓል። ከእብድ ጋር ያበረ ዋጋው ይህ ነው። የትውልድ ውርደት! ወያኔ ምን ያህል በዘሩ የሰከረ እንደሆነ የሚያሳየው ይህ ሁሉ ሴራ ሲታለም ከመካከላቸው አንድም ሃገሬን እመርጣለሁ፤ የሰሜኑ እዝ የሃገር የወገን ልጅ ነው በማለት ሾልኮ ሹክ ያለ የለም። በታሪካችን እንደ ወያኔ ያለ በራሱ ታሪክ የሰከረ ምንም ሃይል ተፈጥሮ አያውቅም።
አሁን በተራድኦ ስም ወያኔን ለመርዳት የገቡ እንዳሉ ይሰማል። ከዚህ ባሻገር የአውሮፓ ህብረት በራሱ ችግር ተወጥሮ ኢትዮጵያን ሲያስጨንቅ ማንበብ ይገርማል። የት ነበሩ ሰው ጥፍሩ ሲወልቅ፤ ሰው በዘሩ ሲታረድ፤ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው በአልሞ ተኳሽ ሲገደሉ። ነጮች የሚታመኑ አይደሉም። ከዚህ ባሻገር ደግሞ ያለምንም መረጃ ኤርትራ በጦርነቱ ተካፋይ እንደነበረች አሜሪካ ትጠረጥራለች በማለት ዜናው ሲናፈስ አሜሪካ አይለች እንዴ ኢራቅ ውስጥ ሃገር አውዳሚ ነገር አለ መረጃው ይኸው በማለት ሳዳምን በገመድ ሰቅለው ዛሬ ኢራቅ የመከራ ዝናብ የሚዘንብባት? ማን ነው ሊቢያን አፈራርሶ የእብዶች መፈንጫ ሃገር ያደረጋት። በራሱ አስቦ ለራሱ የሚኖርን ህዝብ የነጩ ዓለም ደግፎ አያውቅም። ማን ነው ፓትርስ ሉቡባን፤ ሳሞራ ሚሸልን ሌሎችንም የአፍሪቃ አርቆ አሳቢዎች የገደለውና ያስገደለው? ትራምፕ አይደል እንዴ ለግብጽ ግድቡን እንዲያፈርሱ ምልክት የሰጠው? አምናለሁ ግብጾች በጃንዋሪ 20 አካባቢ ጥቃት እንደሚያደርሱ። ግብጽ ለኢትዮጵያ ተኝተው አያውቁም። ሃገርና ወገንን ለጊዜአዊ ጥቅም የሚሸጡም ጠፍተው ስለማያውቁ ሁሌ እንዳጫረሱን ይኖራሉ። አሁንም ወያኔ ከወደ ካይሮ ተጠራቅሞ ለፈፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፤ አንድ ወያኔ ሲጽፍ (በእንግሊዝኛ) ግብጽ ለምን አሁን ግድቡን ለምን አይመቱም? ማንን ነው የሚጠብቁት። እባካችሁ ምቱት ብሏል። ከሃዲ እንዲህ ነው! እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል። 45 ዓመት ሙሉ ገመናውን ያየው የትግራይ ህዝብ እንኳን ከወያኔ ካድሬ አፈና ወጣ። በመረጠው በፈለገው መንገድ ይኑር። ወያኔ ዳግም ላይመለስ አንቀላፍቷል። አፈርና ድንጋይ አልብሱት። በቃ ተፈጸመ! እኔም በቃኝ!