• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአዲስ አበባ ለተከሰተው የነዳጅ አሻጥር መፍትሔ ሊበጅለት ነው

January 18, 2019 12:39 am by Editor Leave a Comment

በአዲስ አበባ ከተማ የቤንዚን ነዳጅ እጥረት እንዲከሰት እና እንዲባባስ በሚያደርጉ ነዳጅ አቅራቢዎች እና አከፋፋዮች ላይ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በአገር አቀፍ ደረጃ በቂ ነዳጅ እያለ ነገር ግን በአዲስ አበባ ከተማ የቤንዚን እጥረት እንዲከሰት እና እንዲባበስ በመደረጉ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ያካተተ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ስራ መጀመሩ ይታወቃል።

በከተማችን ነዳጅ ለማከፋፈል 120 ገደማ የሚሆኑ የነዳጅ ማደያዎች በሕግ አግባብ ፈቃድ መውሰዳቸው እየታወቀ 106ቱ ብቻ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ጥር 8 ቀን 2011 ዓ/ም በስራ ላይ ከሚገኙ 106 የነዳጅ ማከፋፈያዎች መካከል 100 ማደያዎች ላይ በተደረገው ክትትል 54ቱ በቂ የቤንዚን እና የናፍታ፣ 5ቱ የቤንዚን ብቻ፣ 8ቱ የናፍታ ክምችት ያላቸው ሲሆን 30 ማደያዎች ደግሞ ነዳጅ ማራገፍ ሲገባቸው ያላራገፉ በመሆኑ፣ ቀሪዎቹ ሙሉ ለሙሉ ዝግ ሲሆን አንዳንዶች ለእረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው ጊዚያዊ የቤንዚን እጥረት መከሰቱን ኮሚሽኑ አረጋግጧል።

እጥረቱን ለማባባስ ልዩ ልዩ ምክንያች እንዳሉ በተደረገው ክትትል ማወቅ ሲቻል አንዳንድ የማደያ ሰራተኞች ከህገ-ወጦች ጋር በመተባበር ነዳጅ በተለይ ደግሞ ቤንዚን በበርሜል በመገልበጥ፣ በሞተር ብሰክሌትና በሌሎች ተሽከርካሪዎች ከስፍራ ወደ ስፍራ በማጓጓዝ በጥቁር ገበያ በከፍተኛ ዋጋ ሲሸጡ እንደተደረሰባቸው፣ እንዲሁም ሌሎች ሆን ብለው ነዳጅ በመደበቅ፣ ነዳጅ እያላቸው ለምሳና ለእራት ወጥተናል በሚል ሰበብ በመፍጠር፣ የተወሰኑ ደግሞ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ሲገባቸው ያለበቂ ምክንያት በመዘጋታቸው የማደል ስራው እንዲስተጓጎል እያደረጉ መሆኑን ፖሊስ ገልፆ እጥረቱን ምክንያት በማድረግ በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ህገ-ወጥ የሆነ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ደርሶበታል።

ህጋዊ ፈቃድ ወስደው ያለበቂ ምክንያት አገልግሎት የማይሰጡ ማደያዎች በአስቸኳይ ሥራቸውን እንዲጀምሩ እንዲሁም በጥቁር ገበያ ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ በመሸጥ ላይ ያሉ ከህገ-ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኮሚሽኑ አሳስቦ ነገር ግን ማሳሰቢያውን ተግባራዊ በማያደርጉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ ከላከው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል። በተጨማሪም ነዋሪዎች ሕገወጥ ተግባራትን በነፃ የስልክ መስመር 991 ወይም 01-11-11-01-11 መጠቀም ለፖሊስ ጥቆማ እንዲያደርጉ ኮሚሽን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ባለፉት ቀናት በፀጥታ ችግር ምክንያት በመዲናዋ አዲስ አበባና በክልል ከተሞች የተስተጓጎለው የነዳጅ አቅርቦት በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚፈታ ገልጾዋል።

በአፋር ክልል በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ከእሑድ ጥር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የጂቡቲ መስመር ለሁለት ቀናት ያህል በመዘጋቱ፣ 1,000 የሚሆኑ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ መሀል አገር የሚያደርጉት ጉዞ ተስተጓጉሏል። ከጂቡቲ የሚመጡ ብቻ ሳይሆን ወደ ጂቡቲም የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ለመቆም ተገደው ነበር። በአጠቃላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች የአፋር ክልልን ለማቋረጥ ተቸግረው ቆይተዋል።

በድሬዳዋ በኩል የገቡትም የተወሰኑ ነዳጅ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች ሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. አዋሽ ላይ መንገድ ስተለዘጋባቸው መሻገር አልቻሉም። በዚህ ምክንያት ቤንዚን፣ ናፍጣና የአውሮፕላን ነዳጅ የጫኑ 1,000 ያህል ተሽከርካሪዎች በተለያዩ ቦታዎች ቆመው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በአፋር ክልል የተዘጉት ዋና ዋና መንገዶች ሰኞ ጥር 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በመከፈታቸው የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ጉዟቸውን ቀጥለዋል። “የቆሙት የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ጭምር በመሆናቸው፣ መንገድ ላይ የትራፊክ መጨናነቅ ስለሚኖር አዲስ አበባ ለመድረስ አንድ ሁለት ቀን ይፈጅባቸዋል። ከማክሰኞ ጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ አበባ መግባት ስለሚጀምሩ የተፈጠረው የነዳጅ እጥረት ይቀረፋል። ወደ ክልል ከተሞች እስኪደርሱ ሁለትና ሦስት ቀናት ሊፈጅ ይችላል። በክልል ከተሞች የተፈጠረው የነዳጅ እጥረት በሳምንቱ መጨረሻ ይፈታል። በአዲስ አበባ ግን ከረቡዕ ጥር 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ይረጋጋል፤” ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ነዳጅ የሚያመላልሱ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች መተማ ከተማ ለመቆም መገደዳቸው ይታወሳል። በምዕራብ ጎንደር ዞን በተፈጠረው የፀጥታ ሥጋት 70 ያህል ቤንዚን የጫኑ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች መተማ ከተማ እንደቆሙ ታውቋል። ቤንዚን ለማምጣት ወደ ሱዳን የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በተመሳሳይ ችግር መጓዝ ባለመቻላቸው፣ ከሱዳን የሚገባው የቤንዚን ምርት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ቤንዚን የሚቀዱት ከካርቱም 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ጌሊ የነዳጅ ማጣሪያ ነው። የሱዳን ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ተሽከርካሪዎች እስከ ጥር 6 ቀን 2001 ዓ.ም. ሲጭን የነበረ ቢሆንም፣ ከጥር 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ተሽከርካሪ ማግኘት አልቻለም።

የተዘጋው የመተማ መንገድ ከረቡዕ ጥር 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ የሚከፈት በመሆኑ፣ የተከሰተው የቤንዚን እጥረት በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚፈታ አቶ ታደሰ ተናግረዋል። “ከሱዳን በአሁኑ ወቅት የምናስገባው ቤንዚን የፍጆታችንን 20 በመቶ በመሆኑ ያን ያህል የጎላ ተፅዕኖ አይኖረውም። ዋናው ነገር 80 በመቶ የቤንዚን ፍጆታችን የሚገባው ከጂቡቲ ወደብ በመሆኑ የአፋር ክልል መንገዶች መከፈታቸው ነው፤” ያሉት አቶ ታደሰ፣ የነዳጅ እጥረቱ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሚፈታ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

“ችግሩ ሊከሰት የቻለው በጊዜያዊ የፀጥታ ችግር ነው። የነዳጅ ምርት አቅርቦት ወይም የግዥ ችግር የለም። የተዘጉት መንገዶች በመከፈት ላይ በመሆናቸው የቆሙት ተሽከርካሪዎች እስኪደርሱ ለሁለትና ለሦስት ቀናት ችግር ሊኖር ይችላል። ነገር ግን ኅብረተሰቡ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚፈታ ጊዜያዊ ችግር መሆኑን ተረድቶ መረጋጋት ይኖርበታል። በእርግጠኝነት ችግሩ እስከ ሐሙስና ዓርብ እንደሚፈታ መናገር ይቻላል፤” ብለዋል።

ከሱዳን የሚገባው ቤንዚን በአብዛኛው የሚከፋፈለው በአማራ ክልል ውስጥ በመሆኑ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንደማይኖረው ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል።

አዲስ አበባ ውስጥ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች የአፋር ክልል መንገድ በመከፈቱ፣ ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ይገባሉ ተብለው በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።

(ፎቶ፤ ከኦይል ሊቢያ የነዳጅ ማደያዎች በአንደኛው ቤንዚን እንደሌለ በጽሑፍና በነዳጅ ቀጂ ሠራተኛ ጭምር ሲገለጽ)

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule