
በጁንታው መሪ ደብረጺዮን ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተደረገ ፍተሻ በኮንክሪት የተገነባ ዋሻ ተገኘ።
የጁንታው መሪ ህዝቡን አለንልህ እያሉ ለማምለጫቸው ያዘጋጁት ይህ የኮንክሪት ዋሻ ውስጥ ለውስጥ እስከ 300 መቶ ሜትር እንደሚረዝም ነው የተገለጸው።
በትግራይ ክልል እየተከናወነ ባለው የህግ ማስከበር ዘመቻ በጽ/ቤቱ በተደረገ ፍተሸ ይህ የኮንክሪት ዋሻ ተገኝቷል።
ሻለቃ አምባቻው እንደገለጹት፣ ከመንግስት የህግ ማስከበር ዘመቻ ከተጠናቀቀ በኃላ የሕውሃት ጁንታ መሪ ጽ /ቤትና እኖርበታለሁ ፣ አመልጥበታለሁ ያሉት ዋሻ በቁጥጥር ስር ውሎ የአደባባይ ሚስጥር ሆናል።
ምናልባት ቢሮው ቢመታ ወይም ሊይዙን ቢመጡ በዚህ በኩል ለማማለጥ ያስችለናል ብለው የሰሩት ነው።
የጁንታው መሪ በዋናው በር እንዳይወጡ ሕዝብ ስለሚመለከታቸው፣ በአጃቢ አድርገው በዚህ ዋሻ ተጠቅመው ሳይወጡ አልቀሩም ተብሏል።
ወደ 300 መመቶ ሜትር የሚገመተው ይህ የኮንክሪት ዋሻ በመካከል ማስተንፈሻ አለው፤ መውጫው መንገድም ለዕይታ እንዳይጋለጥ በአፈር የተሸፈ ነው።
የአምገነኖች መጨረሻ ይሄው ነው፣ ቆምኩለት የሚሉትንም ህዝብ ማታለል ባህሪያቸው ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የጁንታው ኃይል መጫረሻ እንደዚህ ነው። ማምለጫቸውን አዘጋጅተው ሄደዋል። (ኢፕድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply