• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሕዝብ ደም የሥልጣን ዕድሜ ማርዘም!

June 21, 2016 12:34 pm by Editor Leave a Comment

በዓለም ላይ ከሚታዩት መንግሥታት ውስጥ ሁለት ዓይነት መንግሥታት ጎልተው የሚታዩ ሲሆን፤ ሁለቱም ወደ ሥልጣን እርካብ የሚወጡበት መንገድ የተለያየ ነው።

አንደኛው በሕዝብ ምርጫና ፍላጎት፣ በዴሞክራሲ መንገድ ሥልጣኑን ለተወሰነ ዓመት የሚረከብ ሲሆን ሌላው ደግሞ በራሱ ፍላጎትና ውሳኔ፣ የሕዝብን ድምፅና ፍላጎት ሳይሰማና ሳይጠይቅ በመሣሪያ ኃይል አስፈራርቶና ደምስሶ የሥልጣኑ ባለቤት የሚሆን ነው።

የመጀመሪያውን የስልጣን ባለቤትነትን የሚከተል የግድ የዲሞክራሲን ሕግና ባህል የተቀበለና በዛም የሚያምን መሆንን፣ ችሎታንና ሕዝባዊነትን፣ አገር ወዳድነትን ይጠይቃል። በሁለተኛው የስልጣን አወጣጥ ግን ሃይልን፣ ማንአለብኝነትን፣ የተከተለ ጭካኔን ብቻ የሚጠይቅ ነው። በመሆኑም አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ ተብለው ይጠራሉ ወይም ይመደባሉ።

አገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ዘመናት በሁለተኛው ዓይነት በስልጣን ላይ በተቀመጡ አምባገነኖች በሚከተሉትና በሚያሰፍኑት ስርዓት ስር ስትማቅቅ የኖረች አሁንም እየማቀቀች የምትገኝ አገር ነች።ሌሎቹም የቅርብና የሩቅ የጎረቤት አገሮች እንደዚሁ በአምባገነን በሆኑ በተመሳሳይ ዓይነት ስርዓቶች ስር የሚማቅቁ ናቸው።

የአምባገነን መንግሥት ወይም ስርዓት የስልጣን ዘይቤ አመጽና ጦርነትን መሰረት ያደረገ ነው። በዚህ አስተሳሰብ የተለከፉት በጦርነትና በሃይል ስልጣን ይይዛሉ፣በጦርነትና በሃይልም የስልጣን ዕድሜያቸውን ያራዝማሉ። ለእነሱ ሰላምና የሕዝብ መረጋጋት አጥፊያቸው ነው። ሰላም የማይኖርበትን መንገድ ይፈጥራሉ፤ ሁልጊዜ ሕዝብ በስጋትና በፍርሃት እያደረ ወደ እነሱ አጥፊ ስርዓት ፊቱን እንዳያዞርና የትግል ስሜቱ እንዲኮላሽ ያደርጋሉ። ከነዚህም ዋናውና አንዱ ስልታቸው በአገር ውስጥና በጎረቤት አገር ሽብርና ጦርነት የሚነሳበትን መንገድ መፍጠርና “አገርህ በውጭ ወራሪ ሃይል ተከበበች ወይም ተወረረች” የሚለው የክተት ጥሪ ማወጅ ይሆናል።በራሳቸው አናት ላይ ያለውን ሸክምና አደጋ በሕዝቡ ትከሻ ላይ ለመወርወርና ትኩረቱን ለመቀየር የማይገለብጡት ድንጋይ የለም።

ይህን የጥፋት መልእክት የሚቃወሙትን በመግደል፣ እምቢ ያሉትን አፍሶ በማስገደድ የጦር ሜዳ ጭዳ ያደርጉታል። ስልጣን ሲይዙ የሕዝቡን ደም በማፍሰስ እንደሆነው ሁሉ በሥልጣንም ላይ ለመቆየት እንዲሁ ሕዝብ ደሙን እንዲያፈስላቸው በማስገደድና በማታለል ሰፊ ዘመቻና ዝግጅት ያደርጋሉ። በጦርነቱም ጊዜ ሆነ ማግስት ለሕዝቡ የሚተርፈው ነገር ቢኖር፣ በጦር ሜዳ መሞት፣ መቁሰል፣ አካለጎደሎ መሆን፣ የንብረት መውደም፣ መፈናቀል፣ በስንቅና ትጥቅ የግልና የአገሪቱን ሃብት ማባከን ነው። ከዚያም በላይ ጦርነቱ ሲያልቅ በሕዝብ መካከል የማይከስም የእርስ በርስ ጥላቻና ቋሚ ጠላትነት መፍጠር ይሆናል።

የሰሞኑም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ተከሰተ የተባለው ግጭት በሥልጣን ላይ የተቀመጡት ሁለት አምባገነኖች የሚጫወቱት የዚሁ የሥልጣን አድን ቲያትር ውጤት ነው።ያለፈውም ሆነ በየጊዜው የሚነሳው ውጥረትና ግጭት የወያኔና የሻእብያ የጥቅም ግጭት እንጂ የሕዝብ ግጭት አይደለም። ሁለቱም አምባገነን ሥርአቶች በሕዝብ የተጠሉ ናቸው። ሁለቱም መንግሥት ነን ባይ ቡድኖች እጃቸው በንጹሃን ደም የጨቀዬ ነው። በሁለቱም ስርዓቶች ስር የሚኖረው ሕዝብ ለነጻነትና ለዴሞክራሲ የሚያደርገው ትግል እያደገ በመሄድ ላይ ነው። ይህንን ሕዝባዊ አመጽና ትግል ለማፈንና ለማቀዝቀዝ ያላቸው አንዱና ቀሪው መሳሪያ “አገርህ ተወረረች” በሚል ጩኸት ማደናገርና በእነሱ ላይ ያነጣጠረውን ፍልሚያ ለጊዜው እንዲረሳና ወደ አላስፈላጊ ጦርነት ገብቶ እርስ በርሱ እንዲተላለቅ ማድረግ ነው። የዚህ አይነቱ ስልት የዛሬ አስራ ስድስት ዓመት የተጠቀሙበት ሲሆን የብዙ መቶ ሽህ ንጹሃን ደምና የአገር ሃብትና ቅርስ ወድሞ እስከ አሁንም በሥልጣን ላይ ለመቆየት እረድቷቸዋል። የሰሞኑም ተንኳሽ ግጭት ከዚያ የተለየ አይደለም። ያለፈው ጦርነት ለሕዝብ አለመተማመንና መራራቅ እንዳገለገለ ሁሉ ያሁኑም በሁለቱም ተንኳሽነት የሚካሄደው ግጭት ወደ ከፍተኛ ጦርነት ቢያመራ ከሚያደርሰው የሕይወትና የሃብት ጥፋት በላይ ከዚያ ለከፋ ለከባቢ ቀውስና ለሕዝብ ቋሚ ጠላትነት የሚዳርግ ይሆናል።

ህወሃት/ኢሕአዴግ ባለፈው ጊዜ ከሻእቢያ ጋር ባደረገው ጦርነት የኢትዮጵያን መብት፣ ክብርና ዳር ድንበር እንዳላስጠበቀና እንደውም ጎጂ በሆነ ውልና መደራደር የአገራችንን ጥቅም አሳልፎ የሰጠ፣ የአገር ክህደት የፈጸመ፣ ለውጭ ሃይሎች ጣልቃ መግባትና በሰላም ፈላጊነት ሽፋን ከመጠቀም ሌላ ያመጣው ጥቅም የለም። አሁንም የዚህ የጦርነት አዝማሚያ ለቀጣይ የሁለት አምባገነኖች እርቅና ድርድር መንደርደሪያ ሊሆን ይችላል። ከድርድር በዃላም የሚገኘው ውጤት የኢትዮጵያን ህልውናና ታሪካዊ መብት የሚያፈርስና አሳልፎ የሚሰጥ እንጂ የሚያረጋግጥና የሚያስከብር አይሆንም።

በኤርትራ የሰፈነው ሥርዓትና መንግስት ለኢትዮጵያ ቅንጣት ያህል አይጨነቅም፤ሙሉ ለሙሉ ተበታትናና ተዳክማ ብትኖር ፍላጎቱ ነው። ጠንካራ ኢትዮጵያ፣ አንድነቷን የጠበቀች ኢትዮጵያ፣ ዴሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያ ለእሱ መኖር አደጋ ነው። ለጊዜው ከህወሃት መራሹ ኢሕአዴግ የተጣላ ቢመስልም፣ እንደ ህወሃት መራሹ ቡድን ሊያገለግለው የሚችል ሌላ ቡድን ካልፈጠረ በስተቀር ኢትዮጵያን በማፈራረሱ ደረጃ ከወያኔ የተሻለ አጋር ሊኖረው እንደማይችል ያውቀዋል። ህወሃት/ኢሕአዴግም እንደዚሁ። የአሁኑም እሰጥ አገባ የሁለት ወዳጆች ጊዜያዊ ጠብ ነው።አህያ ላህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም!!እንዲሉ። ይህን ሁሉ ስናገናዝብ ጦርነቱ የሕዝብን ጥቅም የሚያስከብር ሳይሆን አምባገነኖች ለሥልጣናቸው መራዘም የሚገለገሉበት መሣሪያ ሆኖ እናገኘዋለን።

ሕዝብ በሰላምና በመቀራረብ፣ ሊኖር የሚችለው ጦር ሰባቂ የሆኑ አምባገነን ሃይሎችና መንግሥታት ሲወገዱና በዴሞክራሲ ስርዓት ሲተኩ ብቻ ነው። ለዚያ ደግሞ በአምባገነኖች የሚጎሸመውን የጦርነት ነጋሪትና አዋጅ ሳይቀበሉ ተባብረው የጋራ ጠላታቸው የሆኑትን የአምባገነን ስርዓቶች ለማሶገድ ሲነሱ ነው።የሻእቢያን ስርዓት የሚቃወሙም ሆነ የህወሃት/ኢሕአዴግን የሚቃወሙ ማወቅ የሚገባቸው አንዱን አምባገነን ተጠግቶ ሌላውን አምባገነን ማሶገድ እንደማይቻል ነው። የሚታገሉት ለዴሞክራሲ ስርዓት ከሆነ እነዚህ በስልጣን ላይ ያሉት አምባገነኖች ጠላቶቻቸው ናቸው። የትም ይሁን የትም አምባገነን አምባገነን ነው፡፤ ለዲሞክራሲ የቆመ ሃይል ከሁለት አንዱን አይመርጥም። “ከጅንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጧል” ነው። ጅንጀሮ ጅንጀሮ ነው አምባገነንም አምባገነን!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) አሁን በኤርትራና በቀረው ኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተቀመጡት ሁለት አምባገነን ቡድኖች የቀውስና የጦርነት ተጠያቂዎች እንደሆኑ ያምናል፡፤ሕዝብ እነዚህ ጦረኛ፣ አምባገነንና ዘራፊ ቡድኖች ለዘረጉት የዕድሜ አርዝም የጦርነት ጥሪ ጆሮውን እንዳይሰጥ፣ ደሙን እንዳያፈስ እያሳሰበ ብሎም ሃይሉን አስተባብሮ እነዚህን አምባገነኖች ለማሶገድና በሰላም ለመኖር የሚችልበትን መንገድ እንዲፈጥር ተባብሮ እንዲነሳ ጥሪ ያደርጋል። ሻእቢያና ህወሃት መራሹ ኢሕአዴግ በሥልጣን ላይ እስካሉ ድረስ የኢትዮጵያና የኤርትራ ኑዋሪ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የከባቢው ሕዝብ በሰላም አይኖርም።

በጦርነት ሰበብ አድርጎ ድርድር በመክፈት የአገርን ጥቅምና መሬት አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገውን የብልጦች አስመሳይ እሩጫና ዝግጅት ሁሉም ሊያውቀውና ሊታገለው ይገባል። በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ፣ ለአገራቸው ጥቅም እንቆማለን የሚሉ የገዝው ቡድን ደጋፊወች ጭምር ከሌላው አገር ወዳድ ጋር ተባብረው በስማቸው የሚፈጸመውን ክህደትና አገር ጎጂ ተግባር ሊቃወሙት ይገባል። ያለፈው ይብቃ !ብለው መነሳት ይጠበቅባቸዋል።

በውጭ የሚኖረውም ዜጋ ጦርነቱን እንዲያወግዝና ሁለቱም አምባገነን ስርዓቶች እንዲወገዱ በጋራ እንዲታገል ጥሪያችንን አሁንም እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)
Ethiopian People’s Congress for United Struggle (Shengo)
www.ethioshengo.org
shengo.derbiaber@gmail.com
Tel: 44 7937600756
+1 9168486790
E-mail : shengo.derbiaber@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Uncategorized Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule