የላዚዮ አውራጃ ኦፊሴያላዊ መግለጫ፤ (ቁ. 24/1) ዋና ዋና ነጥቦች
(ዶ/ር ግርማ አበበ በኢጣልያንኛው ሰነድ መሠረት በእንግሊዝኛ ባቀረቡት መሠረት)
ጉዳዩ፤ የአፊሌ ከተማ ማሕበራዊ ምክር ቤት ለማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ አፌሌ ስለ መረቀው ትንሽ የሚሊታሪ ሚዩዚየም፤ እ.አ.አ. ሐምሌ 21 ቀን 2012 ያስተላለፈውን ውሳኔ እንዲሰርዝ የቀረበ ጥሪ፤
በላዚዮ አውራጃ የተወሰደ እርምጃ
እ.አ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2015
እ.አ.አ. ሕዳር 11 ቀን 2004 የወጣውን የላዚዮን አውራጃ ሕግና ሌሎችንም ጉዳዮች በመመልከት፤
በተጨማሪም እ.አ.አ. በየካቲት 18 ቀን 2002 የወጣውን የክልሉን ሕግ በማስታወስ፤
የአፊሌ (ከተማ) ማሕበረሰብ ምክር ቤት እ.አ.አ. በሐምሌ 21 ቀን 2012 አንድ ትንሽ የሚሊታሪ ሚዩዚየም ለማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ እንዲመረቅ የወሰነ መሆኑን በማሰብ፤
ሮዶልፎ ግራዚያኒ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወንጀለኞች ዝርዝር የተመዘገበ፤ በሰዎች ላይ የመርዝ ጋዝ የተጠቀመና በኢትዮጵያ የቀይ መስቀል ሆስፒታል በቦምብ እንዲደበደብ ትእዛዝ ያስተላለፈ በፋሺሽት ኢጣልያ ቁልፍ መሪ የነበረ መሆኑን በማስታወስ፤
የአፊሌ ማሕበረሰብ ምክር ቤት ትንሹን የሚሊታሪ ሚዩዚየም ለማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ በመመረቅ ያስተላለፈውን ውሳኔ እንዲሰርዝ፤ ይህንንም ተግባር፤ የላዚዮ ባለሥልጣን እ.አ.አ. በመጋቢት 13 ቀን 2015 ከወሰነበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀኖች ውስጥ እንዲፈጽም ታዟል።
የማሕበረሰቡ ምክር ቤት ውሳኔውን እንዲሰርዝ የተላለፈለትን ትእዛዝ በተፈቀደለት ጊዜ ውስጥ ካላጠናቀቀ፤ ለትንሹ የሚሊታሪ ሚዩዚየም መሥሪያ በአውራጃው ባለሥልጣን የተሰጠውን ገንዘብ እንዲመልስ ይጠይቃል።
በመጨረሻውም፤ የአፊሌ ማሕበረሰብ ምክር ቤት በአውራጃው ባለሥልጣን የተጠየቀውን ሳይፈጽም ቢቀር፤ ባለሥልጣኑ ጉዳዩን፤ የአፊሌ ከተማ ምክር ቤትን ውሳኔ፤ ወደ ፍርድ ለማቅረብ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል።
(የጣሊያንኛውን መረጃ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
The following is Dr. Girma Abebe’s presentation of the main points contained in the Official Bulletin of Italy’s Lazio Provincial Authority, No. 24 – Supplement 1:
OFFICIAL BULLETIN OF THE LAZIO PROVINCE No. 24 SUPPLEMENT 1
Subject: CALL ON THE COMMUNITY COUNCIL OF AFFILE TO CANCEL ITS DECISION OF 21 JULY 2012 DEDICATING THE SMALL MILITARY MUSEUM IN AFFILE FOR MARSHALL RODOLFO GRAZIANI
ACTION BY THE PROVINCIAL AUTHORITY OF LAZIO
13 MARCH 2015
Recalling, inter-alia, the new statue of the province of Lazio of 11 November 2004,
Further recalling the regional law of 18 Gebruary 2002,
Considering the decision of 21 July 2012 by the Council of the Affile Community whereby it dedicated the small military museum in Affile to Marshall Rodolfo Graziani,
Recalling that Rodolfo Graziani was a key leader of Fascist Ittaly who was listed in the United Nations war criminal list for having used gas against humans and ordered the bombardment of the Red Cross hospital in Ethiopia;
Orders the Affile Community Council to cancel the dedication of the small military museum to Marshall Rodolfo Graziani within 15 days from the date of the decision made by the Lazio Authority on 13 March 2015.
The Provincial authority calls on the Affile Community Council to surrender the funds the Province provided for the construction of the small army museum unless the Community Council carries out its orders on the cancellation within the designated time.
Ultimately, in the absence of action by the Affile Community council to carry out the request of the Provincial Authority, the Authority will take necessary steps to bring the matter to justice about the decision of the members of the Affile town Council regarding the issue at hand.
pheniel says
ስለ ቦኮሀራ በfacebook አድሬሴ massage ቢላክልኝ?