የጎልጉል ማሳሰቢያ፡ ይህንን ጽሁፍ የላኩልን ሰላማዊት አሰፋ ይባላሉ፡፡ ስለጽሁፉ ይዘት እኛ ከምንናገር ይልቅ አንባቢዎች የራሳቸውን ግንዛቤ እንዲወስዱ ለንባብ አትመነዋል፡፡ ጸሐፊዋን በግል ለማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ በቀጥታ በዚህ አድራሻ ለመጻፍ ይችላሉ (a_selamawit53@yahoo.com) ይህንን ጽሁፍ አስመልክቶ በጨዋነት የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት የሚፈልጉ ሁሉ የሚልኩልንን ጽሁፍ እንደምናትም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ!
ሀገራችን ኢትዮጵያ በጠባብ ዘረኞች መዳፍ ስር ከወደቀች እነሆ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ተቆጠሩ። ህዝባችንም ቢሆን በዋነኛነት በዘር እንዲከፋፈል ተደርጎ እርስ በርሱ እንዳይተማመን ይልቁንም በጠላትነት እንዲተያይ ከመደረጉም ባሻገር በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳይ በገዛ ሀገሩ ባዕድ እንዲሆን ተደርጓል።በኢኮኖሚውም ቢሆን ኑሮው ዕለት፥ዕለት እያሽቆለቆለ በልቶ ማደርን እንደትልቅ ፀጋ ከሚቆጥርበት ዘመነ ፍዳ ላይ ይገኛል።
የፅሑፌ አላማ ሀገራችን ኢትዮጵያ የገባችበትን አዘቅት እና ህዝቦቿ የሚገኙበትን ሰቆቃ ለመዘርዘር ሳይሆን ከዚህ አስከፊ ሁኔታ ሀገራችንና ህዝቦቿ እንዳይወጡ የየበኩላቸውን አስተዋፅኦ ከሚያደርጉ ሰንኮፎች መካከል በአንዱ ዙሪያ ያለኝን አስተያየት ለማካፈል ነው።
የወያኔን ዕድሜ ከሚያራዝሙ በርካታ ምክንያቶች መካከል ጭንጋፍ /ምቱር/ ፖለቲከኞችና ፍሬ አልባ ድርጅቶቻቸው በዋናነት ይጠቀሳሉ።
እነዚህ ጭንጋፍ /ምቱር/ ፖለቲከኞች በሀገር ቤትም ከሀገር ቤት ውጪም በተለይ በአውሮፓና በዩ ኤስ አሜሪካ ይገኛሉ።የሀገር ቤቶቹ በአብዛኛው በምርጫ ሰሞን በወያኔ ተጠፍጥፈው የሚሰሩ አልያም ራሳቸው እንደ አሸን ፈልተው ከምርጫው ጋር አብረው የሚከስሙ ሲሆን ከዛ ውጪ ያሉትም ቢሆን የህዝብ አመኔታ የሌላቸውና መዋያ ባጡ አዛውንቶች የሚዘወሩ ፍሬ አልባ ሆነው እናገኛቸዋለን።ይህ ማለት ግን በሀገር ቤት ከወያኔ ጋር እየተላተመ ብሎም መስዋዕትነት እየከፈለ የሚታገል ድርጅት የለም ማለት አይደለም።
በሌላ በኩል በህዝባችን ቁስል ላይ ጥዝጣዜን እየጨመሩ ከሚገኙት መካከል ውጪ ሀገር የሚኖሩ ነፍስ-አልባ ተንቀሳቃሽ ሬሳዎች ሲሆኑ እኒህ የጨነገፉ ፖለቲከኞች ”ኢትዮጵያን ነፃ እናወጣለን” እያሉ ፍሬ-አልባ ድርጅቶችን በማቋቋም በህዝብ ስም የሚነግዱ፣በነፃነት ስም እየማሉ ነፃ ያልወጡ፣በስደተኛ ወንድሞቻቸው ስቃይ የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ፣የሚሰርቁ፣የሚዋሹ፣ስደተኛ ሴት እህቶቻችንን የሴሰኝነታቸው ማራገፊያ የሚያደርጉ ሲሆን ”ሰው መሳይ በሸንጎ” እንደሚባለው ወድቆ በተነሳው ባንድራችን በየአደባባዩ ሲምሉ፣ስለሀገር አንድነት እና ስለህዝቦቿ ፍትህ ማጣት ሲያወሩ ኤሎሄ ከማለት አልፈን ብዕር እንድናነሳ አስገድዶናል።
ለዛሬ መነሻዬን የአውሮፓ እምብርት ከሆነችው ጀርመን አድርጌአለሁ። (በዚህ አጋጣሚ ውድ አንባብያን ሆይ! በስራ ምክንያት ዩ ኤስ አሜሪካ በየጊዜው የምሄድ በመሆኑ በአሜሪካም ያየሁትንና በቂ ማስረጃ ያገኘሁበትን በቀጣይ እትም አቀርበዋለሁ)። (ሙሉው ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply