በሚመጣው ህዳር ወር ላይ የኢትዮጵያ ልጆች የኦሮሞ ብሄር ለሂቃን ተሰብስበው በከፍተኛ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ሲባል ምክክሩን ወድጄው በስብሰባው ላይ ቢነሳ ጥሩ ነበር ብየ ባሰብኩት ላይ ለመወያየት ነው አነሳሴ። የውይይቱ አሳብ ለሁሉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው በርግጥ። እነዚህ የኦሮሞ ወገኖቼ ከዚህ ስብሰባ በሁዋላ የሚያወጡት የአቋም መግለጫ የኢትዮጵያን ማህበረ ፓለቲካ ለመለወጥ ትልቅ ድርሻ ያለው የትብብር፣ የአንድነት አሳብ እንደሚሆን አምናለሁ።
በአሁኑ ሠዓት ኢትዮጵያችን በከፍተኛ ህዝባዊ ንቅናቄ እየተናጠች ነው። ምን አልባትም ይህ ዓይነቱ ህዝብ መራሽ የሆነ ሰፊ ትግል በታሪካችን አልታየም። የህዝባዊ አመፁ በከፍተኛ ሁኔታ እየገፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት የፓለቲካ ሃይላት ሲቪክ ድርጅቶችና የሃይማኖትና የባህል መሪዎች ሁሉ ሁለት ትላልቅ የምክክር አጀንዳዎች ከፊታቸው ተደቅነዋል። በተናጠልም በጋራም በነዚህ ጉዳዮች ላይ መወያየት አለብን። አንደኛው ወቅታዊ ጉዳይ ይህ የህዝብ ትግል እንዴት ነው የሚቋጨው? እንዴት ነው የሚያልቀው? የሚለው አስቸኳይ ጉዳይ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሽግግሩ ጊዜ ሊሰሩ የሚገባቸው ስራዎች ላይና የሽግግሩ ጊዜ ምን መምሰል እንዳለበት በመምከሩ ላይ ያተኮረ ነው። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Aklilu says
This is exactly what is to be done and main roadmap towards building the future.