• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

June 23, 2013 03:42 pm by Editor Leave a Comment

መልዕክተ ደወል – “ተለዩ”

“ … በኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ በተቃውሞው ጎራ የሚገኙ የተገነዘቡት አንድ ጉዳይ ዝም ብሎ በሆይ ሆይታ ሰላማዊ ትግል ማድረግ ብሎም ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል ነው፡፡ በቆራጥነት፣ በፅናትና አርቆበማየት ነው ለድል መብቃት የሚቻለው፡፡ ሰላማዊ ትግል  ሲባል ሞት፣ እስራትና እንግልት የለም ማለትአይደለም፡፡ ልዩነቱ ሰላማዊ ታጋዩ አይገድልም፡፡ ሠላምን አያደፈርስም፡፡ ነገር ግን በፀናና በተደራጀሁኔታ መብቱን ይጠይቃል፡፡ ሉዓላዊ ስልጣኑን ዕውን ሳያደርግ ወደ ኋላ አይመለስም፡፡ በሠላማዊ ትግልውጤታማ እንዲሆን የሕዝብ አንድነትና የዓላማ አንድነት ወሳኝ ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ትግሉ የራሱስነምግባር አለው፣ መደጋገፍን ይጠይቃል፡፡አንዱ ሲወድቅ እሱን አንስቶ ከፍ ባለ የሞራልና የዓላማልዕልና ትግሉን እየተቀባበሉ ወደፊት መሄድ ይጠይቃል፡፡ አስቀድሞ የነፃነትን ምንነትናየሚከፈለውንዋጋ ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ አሁን የጀመርነው ትግል ግብታዊ ያልሆነ የተጠናና በስሜት የማይነዳ ሰላማዊትግል የአንድ ቅፅበት ግርግር እንዳልሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ ሊረዳ ይገባል። …

“ከእንግዲህ የሚሰማህን ሰቆቃ በቃ ልትል ይገባል፡፡ የአገር ባለቤትነትህንና የዜግነት መብትህን፣ ክብርህን ለማስጠበቅ ከሁሉም ጋር ሆ ብለህ መነሳት አለብህ። ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሕግ የበላይነት ተከብሮ ከጎሣ ይልቅ ሰብዓዊነት የቀደመበት ህዝባዊ መንግሥት የሚቋቋምበትንና አዲሲቷ ኢትዮጵያ የምትመሠረትበት አጋጣሚ አሁን ነው፡፡

“እርስዎ ወደውም ይሁን ተገደው የህወሃት/ኢህአዴግ መሣሪያ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሆይ! የማንነትዎ መገለጫው፣ ክብርና ሞገስን የሚያጎናፅፍዎ ዛሬ እያገለገሉ ያሉትን ህወህት/ኢህአዴግን በመክዳት ለህዝባዊው ትግል አለኝታነትዎን መግለፅ ነው” (ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ ድረገጽ የደወል ጥሪ የተወሰደ)

አንደበት

goshu“… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮት ዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ አገርን መምራትን የሚያክል ታላቅ ሃላፊነት ማሸከም ለኔ ከአእምሮ በላይ ነው …” የዛሬ 22ዓመት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ በአሜሪካ ምክርቤት ከተናገሩት፡፡

መድረክ በአባይ ግድብ ላይ ባይተዋር መደረግ የለብንም አለ

ማብራሪያ እንፈልጋለን፣ የግብጽን ማስፈረራት እንቃወማለን

መድረክ በአባይ ግድብ ላይ ገዢው ፓርቲ የሚያራምደውን ሁሉንም አውቃለሁ የሚል የተመጻደቀ አቋም መቀየር እንዳለበት አስታወቀ። ሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በበኩላቸው በግድቡ ዙሪያ አሁንም ማብራሪያ እንፈልጋለን። የግብጽን የወረራ ማስፈራሪያ አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል።

መድረክ አቋሙን ገልጾ ያሰራጨውን መግለጫ አስመልክቶ ለቪኦኤ ማብራሪያ የሰጡት ዶ/ር በየነ ጼጥሮስ “የአባይ ጉዳይ አገራዊ ነው። ችግር ቢከሰት የኢህአዴግ ብቻ አይደለም። እኛም ያገባናል” ብለዋል። የግብጽ መንግስት አገራዊ በሆነው የአባይ ግድብ ጉዳይ እገሌ ከእገሌ ሳይል ሁሉንም የተቃዋሚ ሃይሎች ያሳተፈ ውይይት ማድረጉን ያመለከቱት ዶ/ር በየነ፣ “ኢህአዴግ ህዝብን መያዝ አለበት። ህዝብ እውነተኛ ወኪሎቹን መርጦ ፓርላማ ባለመላኩ ተቃዋሚዎችን የሚጋብዝ አገራዊ ውይይት ሊደረግ ይገባል” የሚል መልክዕክት አስተላልፈዋል።nile dam

ጉዳዩ ተጀመረ እንጂ እልባት እንዳልተበጀለት በማመላከት የኢህአዴግን “እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ” የሚለውን አቋሙን “መመጻደቅ” በማለት የወረፉት ዶ/ር በየነ፣ ኢህአዴግ ሊየዘጋጅ በሚገባው ውይይት “ጥገኛ” የሚባሉትን የተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ሊያካትት እንደሚገባ አመልክተዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢኒጅነር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው የአባይን መገድብ  ለጥያቄ እንደማያቀርቡት አስታውቀው፣ በርካታ ግልጽ ሊሆኑ የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ ባይ ናቸው። ከቦታው መረጣ ጀምሮ፣ የገንዘቡ ፍሰት፣ የጨረታው አካሄድ፣ የፕሮጀክቱ ጥናትና አገራዊ ደህንነት ላይ ፓርቲያቸው ማብራሪያ እንደሚሻ ተናግረዋል።

የውስጥ ቅሬታዎችን ማስወገድ አግባብ እንደሆነ ያመለከቱት የሰማያዊ ፓርቲ መሪ መንግስት ፕሮጀክቱን ለተራ ፓኦለቲካ ፍጆታ ከመተቀም እንዲቆጠብ ጠይቀዋል። ግብጽ የምታካሂደው ማስፈራራት ክብርና አገራዊ ማንነትን በሚያናንቅ መልኩ መሆኑ እንደሚያሳዝናቸው አመለከቱት ኢንጅነር ይልቃል”ከተፈለገ ታሪካዊ የአባቶቻችንን አሸናፊነት እንደምንደግመው እናሳያለን” ብለዋል። ለሁሉም ግን የውስጥ ችግርን በግልጽነት፣ አገራዊ አጀንዳና ብሄራዊ ምግባባት ሊቀድም እንደሚገባ አመላክተዋል።

ሲፒጄ “ጋዜጠኞች እንዴት የልማት ስጋት ይሆናሉ?” አለ

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጄ እየተጋመሰ ባለው ዓመት ብቻ ከሃያ አንድ አገሮች ሃምሳ አምስት ጋዜጠኞች አገር ጥለው መኮብለላቸውን አስታወቀ። ሲፒጄ የስደተኞች ቀንን አስመልክቶ ባሰራጨው መግለጫ እንዳለው ኢትዮጵያ፣ CPJ-LOGO1ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ሶራያና ኢራንን ጋዜጠኞች የሚሰደዱባቸው ግንባር ቀደም አገራት አድርጎ አስቀምጧቸዋል።

ለቪኦኤ ማብራሪያ የሰጡት የሲፒጄ ሰው “ሩዋንዳ የፕሬስ ነጻነት ቅንጦት ነው” በማለት የኢትዮጵያንና የዩጋንዳን መንገድ መከተሏል አውግዘዋል።

“ጋዜጠኞች እንዴት የልማትና የዴሞክራሲ ስጋት ይሆናሉ” በማለት የሚተይቁት የሲፒጄ ሰው፣ ተጠያቂነት ባልሰፈነበት አገር ልማት ሊታሰብ እንደማይችል አመልክተዋል። በማያያዝም ጋዜጠኞች ልማትንና ዴሞክራሲን ከማሳደግ አኳያ የሚጫወቱት ሚና በሁሉም አቅጣጫ ተቀባይነት ሊኖረው እንደሚገባ አመልክተዋል።

ከህገወጥ የቤት ምዝገባ ጋር በተያያዘ 79 ሰዎች ተከሰሱ

ከ20 /80 እና ከ 10/90 የቤት ፕሮግራም ምዝገባ ጋር በተያያዘ ህገ ወጥ ተግባር ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው 79 ግለሰቦችcondos ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ስራ አስከያጅ አቶ መስፍን መንግስቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፤ ግለሰቦቹ የተከሰሱት ሃሰተኛ መታወቂያ ይዘው በመገኘታቸውና፤ባለትዳር ሆነው ሳለ ባል በመስሪያ ቤቱ ሲመዘገብ ሚስት ደግሞ በወረዳ ምዝገባ ሲያካሂዱ ስለተደረሰባቸው ነው።

ከነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከልም 4ቱ ከ 3 ወር እስከ 1 አመት በሚደርስ እስራት ተቀጥተዋል። የቀሪዎቹ ተጠርጣሪዎች የክስ ሂደት የቀጠለ ሲሆን ዋና ስራ አሲከያጁ የከተማው ነዋሪ የተፈጠረለትን መልካም እድል በእንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባር እንዳይደናቀፍበት ከኤጀንሲው ጎን በመቆም ማጋለጥ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ (አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 16 ፣ 2005፤ ኤፍ ቢ ሲ)

የግብጽ አምባሳደር ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ነን አሉ

የህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በተቀመጠለት አቅጣጫ መሰረት እየተገነባ እንደሆነ በስፍራው ጉብኝት ያደረጉ በኢትዮጵያ የሚገኙ የናይል ተፋሰስ የትብብር ጅማሮ አባል ሀገራት አምባሰደሮች ገለፁ፡፡

አምባሰደሮቹ ስለ ግድቡ ግንባታ በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን የሚነገሩ ጉዳዮችም የተሳሳቱ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡የአባይ ወንዝ ተፈጥሮአዊ የፍሰት አቅጣጫ በጊዝያዊነት በማስቀየር ከዚያም ወደ ተፈጥሮአዊ ፍሰቱ እንዲቀላቀል በማደረግ የቀጠለው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ የዋናው የኮንክሪት ግንባታ ቀጥሏል፡፡

Egyptian Foreign Minister Kamel Amr and his Ethiopian counterpart Adhanom attend a session of the talks over the Nile Dam in Ethiopia's capital Addis Ababaበኢትዮጵያ የሚገኙ የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ጅማሮ አባል ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ግድቡ የደረሰበትን የግንባታ ደረጃ እና ወቅታዊ ሁኔታው በቦታው ተገኝተው ጎብኝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የታንዛንያ አምባሳደር ጆራም ሙካማ ቢስዋሮ እና የኬንያ አምባሳደር ዶክተር ሞኒካ ጁማ የሚከተለውን ብለዋል፡፡”ማየት ማመን ነው አየንና አመንን አንደኛ በእውነትም ፕሮጀክቱ እውን እየሆነ ነው፡፡ በእቅዱ መሰረት እየተሰራ ነው፡፡ ሁለተኛ በአንዳንድ ሚድያዎች የሚሰጠው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየርና የግንባታ ሂደቱ በወንዙ ፍሰት ላይ ምንም ያመጣወ ለውጥ የለም፡፡””ይህ ለአከባብያችን፣ለኢትዮጵያ ብሎም ለመላው አፍሪካ ድል ነው፡፡ በአውነት ይህንን ፕሮጀክት ያሰቡ እና እውን እያደረጉ ያሉት ሰዎችን ማድነቅ እፈልጋለሁ፡፡”

“ይሄ ግድብ የአፍሪካ የህዳሴ መንፈስን የያዘ ፕሮጀክት ነው፡፡ ስራውም በተቀላጠፈ መልኩ እየሄደ ነው፡፡ እናም እንዳየነው ውሃው አሁንም ወደ ታችኞቹ ተፋሰሰ ሀገራት እየፈሰሰ ነው፡፡ ለሜትሮች ብቻ ነው አቅጣጫው የቀየረው ይሄ በምንም መልኩ ሊያሳስብ የሚገባ ነገር አይደለም፡፡”

በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር በበኩላቸው”ሱዳን ለዚህ ፐሮጀክት ሙሉ ድጋፍ አላት፡፡ ምክንያቱም ግድቡ ለአከባብያዊ በተለይ ደግሞ ለግብፅና ሱዳን ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ስለምናምን ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ላይ ከፍተኛ ስራ መሰራቱም ተገነዝቤለሁ”ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደር ሞሃመድ እድሪስ በበኩላቸው”ለኢትዮያውያን እህትና ወንድሞቼ መግለፅ የምፈልገው እኛ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ልማት ጎን መሆናችን ነው ፡፡ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ተመስርቶ የመጣን መንኛውንም ፕሮጀክት እንደግፋለን”ብለዋል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ እያደገ ያለውን የሀይል እጥረት በመፍታት ረገድ የህዳሴወ ግደብ ከፍተኛ አቅም ይሆናል ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ የዩጋንዳ አምባሳደር ሙል ካቴንዴ ፤”በአብዛኛው የአከባብያችን ሀገራት የሃይል ፍላጎት በ3 በመቶ በየወሩ እያደገ ነው፡፡ ለምሳሌ 200 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ ግድብ ብትገነባ በየጊዜወ ግድብ ስትገነባ መኖር ነው፡፡ ይሄ ባለ 6 ሺ ሜጋ ዋት ግድብ ግን ለቀጣናው የሀይል ፍላጎት ትልቅ እፎይታን ነው ይዞ የሚመጣው፡፡” ማለታቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል ፡፡ (አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 16 ፣ 2005፤ ኤፍ ቢ ሲ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule