• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

December 16, 2012 12:25 pm by Editor Leave a Comment

ገበያ የደራላት ጅቡቲ

ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም ከወደአገርቤት የተዘገበው ዜና መለስን በማስታወሻነት የሚዘክር ሆኗል። ዜናው እንዳለው ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ጅቡቲ ታጁራ ላይ  አዲስ ወደብ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነስርዓት አከናውናለች። የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ  የወደቡ ግንባታ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ የምትፈልገውን የወደብ አገልግሎት በተሟላ ደረጃ እንድታገኝ ያስችላታል ሲሉ የ “ገበያው ደራ” ንግግር አድርገዋል።

በስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ሃይለማርያም ደሳለኝ ፥ አዲሱ የወደብ ግንባታ የኢትዮጵያና የጅቡቲ ህዝብ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑንን ጠቅሰው መናገራቸውን የገለጸው ፋና ብሮድካስቲንግ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት በየብስና በባቡር ትራንስፖርት ፣ በሃይል አቅርቦትና በወደብ አገልግሎት የተቆራኘው የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት በመልካም ደረጃ ላይ ይገኛል” ሲል ለጅቡቲ ገበያ እጅ የሚነሳ ሪፖርት አቅርቧል። ኢትዮጵያ ተከራካሪ መሪ ስለሌላት ህጋዊ ወደቧን አጨብጭባና ደግሳ ካስረከበች በኋላ ተንፈራግጣ የምትሰበስበውን ምንዛሬ ለጅቡቲ እያስረከበችና ለዚሁ የታሪክ ጠባሳ የዳረጓትን አቶ መለስን “ባለራዕይ መሪ፣በብሄራዊ ጥቅም የማይደራደሩ እውነተኛ አባት” እያለች ትኖራለች፡፡

አርቲስት ህይወቴ አበበ አረፈች

ምክንያቱን ሳይገልጽ ኑሮዋን ኡጋንዳ አድርጋ እንደነበር ፋና ሬዲዮ ይፋ ሲያደርግ፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘሎታል። ትውልዷ ሐረር ከተማ ሲሆን ባለትዳርና የአንዲት ልጅ እናት ነበረች። ሃረር አማተር ቲያትር የጀመረችውን ትወና ገፍታበት ለመጀመሪያ ጊዜ “ቀዝቃዛ ረመጥ” የሚለውን ቲያትር በመተወን ብሄራዊ ቲያትር መድረክ ላይ የታየችው በ1992 ነበር ወጣቷ የመድረክ ሰው ህይወቴ አበበ።

አስራ ሶስት ዓመት በቆየችበት የትወና ስራ ባለታክሲ፣ ውበትን ፍለጋ፣ የሰርጉ ዋዜማ፣ የመቃብር ቁልፎች፣ ባለቀለም ህልሞች፣ ሰውየው ወዘተ በተሰኙ ፊልሞችና ቲያትሮች ላይ ተጫውታለች። የ31 ዓመቷ አርቲስት ጳውሎስ ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ ህይወቷ አልፏል። አርቲስቷ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቲያትር ጥበብ የመጀመሪያ ዲግሪ አላት። የዝግጅት ክፍላችን ለቤተሰቦቿና ለአድናቂዎቿ መጽናናትን ይመኛል።

አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ሰብሳቢነት ተነሱ

የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቦርድ ሰብሳቢነት ሹመታቸው መነሳታቸውን ኢሳት አስታወቀ። በቅርቡ በኦህዴድ ተካሂዶ በነበር ግምገማ ተራ አባል ሆነው እንዲቀጥሉ የተወሰነባቸው አቶ ጁነዲንን የተኳቸውና ዩኒቨርስቲውን በቦርድ ሰብሳቢነት የተመደቡት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተክለብርሀን መሆናቸው ታውቃል።

አቶ ጁነዲን ባለቤታቸው በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው መታሰራቸውን በመቃወም አንድ ጽሁፍ በግል ጋዜጣ ላይ ማውጣታቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ጽሁፍ ከስልጣናቸው ለመባረራቸው ምክንያት መሆኑን የመንግስት ቃልአቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል በአንድ ጋዜጣ ላይ ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት፣ ከሳውዲው ቢሊየነር ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን እንዲሁም ከሳውዲ መንግስት ጋር በቅርብ እየሰራ ወ/ሮ ሀቢባ ከሳውዲ ኤምባሲ ገንዘብ በመቀበላቸው እንዴት ሽብርተኛ ሊባሉ ይችላሉ በማለት ጥያቄ ያቀረቡ፣ የአቶ ጁነዲን ደጋፊ የሆኑ የኦህዴድ አባላትም በተመሳሳይ ከሀላፊነታቸው እየተነሱ እንደሆነ ኢሳት ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓ ም ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን የሳውዲ አረብያን መንግስትና የሳውዲ አረብያን ኤምባሲ ሽብረተኝነትን በማስፋፋት ወንጀል ሲከሳቸው አለመሰማቱንም ኢሳት አመልክቷል።

ኤርትራ 18 ለ 6 ትመራለች

ኤርትራና ኢትዮጵያ በ2012 ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ከፍተኛውን ቁጥር እንደያዙ የአሜሪካ ራዲዮ ሲፒጄን ጠቅሶ ዘግቧል። በዓመቱ በአስራ አንድ ወራት 232 ጸሃፊዎች፣ የፎቶ ጋዜጠኞች እና የህትመት አዘጋጆች ታስረዋል። ኢራን፣ ቱርክና ቻይናን በደረጃ ያስቀመጠው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች  በአፍሪካ አርባ አራት ጋዜጠኞች ታሥረዋል ብሏል። ኢትዮጵያ ደግሞ ስድስት ጋዜጠኞችን፡፡ ኤርትራ ሃያ ስምንት ጋዜጠኞችን አስራ ለወራትና ለዓመታት ያስቀመጠችው ያለክስና ያለፍርድ መሆኑን አመልክቷል።

ኤርትራ ያሰረቻቸው ጋዜጠኞች ምሥጢራዊ እሥር ቤቶች ውስጥ በመሆናቸው ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ ያስረዳው ሲፒጄ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥቱ ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችን ለማሠር በሽብር ፈጠራ ላይ የተከፈተውን ጦርነት እንደሽፋን ተጠቅሞበታል ሲል የተለመደና የሚታወቀውን ምክንያት ጠቁማል። የሲፒጄው መሐመድ ኬይታ እንዳሉት “የሽብር ሕግ” የሚለውን የብዥታ አጠራር ጋዜጠኞችንና ተቃዋሚዎችን በደፈናው ለመፈረጅ ጉዳይ ውሏል።

“የሃይለማርያም ካርድ”

የመለስንና የሃይለማርያምን መንገድ በማጣቀስ በፖለቲካ ገጹ ሰፊ ዘገባ ያቀረበው ሪፖርተር ፣ሃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት በይፋ እንዳይሰራጭ የሞገድ አፈና ካደረገበት አልጃዚራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አስመልክቶ “ውህደት” የምትለውን ሃረግ በመጎተት የ“ሃይለማርያም የፖለቲካ ካርድ” ሲል አስተያየት አስፍሯል።

“ለእኛ ዋነኛ ጉዳያችን ድህነትን መዋጋት ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ አካባቢያዊ ውህደት መፍጠር፡፡ ሁለታችን ይህንን ማድረግ ከቻልን ምርታማ እንሆናለን፤” በማለትም አክለው ተናግረዋል፡፡ ድህነትን በተመለከተ በአብዛኛው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አስተያየት አሁንም በመለስ አቋሞች ላይ ያጠነጠነ ቢመስልም፣ “ውህደት መፍጠር ከቻልን” የሚለው ግን አዲስ “መላ” ይመስላል፡፡ “ውህደት መፍጠር” የሚለው ንግግር አቶ መለስ አንስተውት የማያውቁት ርዕሰ ጉዳይ ሲሆን፣ አንድ አዲስ ምዕራፍ አመላካች ሊሆን ይችላል የሚል ትንታኔ እየተሰጠበት ነው እንደሆነ ሪፖርተር ጠቁሟል።

ምናልባትም ሐሳባቸው በፕሬዚዳንት ኢሳያስ ተቀባይነት የሚያገኝ ከሆነ፣ ከአሥር ዓመታት በላይ የዘለቀው የሁለቱም አገሮች “ሰላምና ጦርነት አልባው” ግንኙነት መልኩን በመቀየር አዲስ ታሪክ ያስመዘገባል እየተባለ ነው፡፡ አገራቸው ውስጥ ባለው ሁኔታ ተቀባይነት ያጡትን ፕሬዚዳንት ኢሳያስም ምናልባት ከገቡበት ጥልቅ አዘቅት ውስጥ ሊያወጣቸው ይችላል፡፡ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምም፣ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የበለጠ ተቀባይነት ለማግኘት ሊጠቀሙበት የሚገባ የፖለቲካ ካርድ ሊሆን እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸውን ሪፖርተር ታህሳስ 5 ቀን 2005 አስነብቧል።

ተቋርጦ የነበረው የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክስ እንደገና ተጀመረ
ዋስትና ተፈቅዶለት በ50 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቀ

ሦስት ክሶች ተመሥርተውበትና ዋስትና ተከልክሎ ለአራት ቀናት በማረሚያ ቤት ከቆየ በኋላ፣ ክሱ ተቋርጦ በነፃ የተሰናበተው የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ የተቋረጠው ክስ በድጋሚ ትናንትና ፍርድ ቤት ቀርቦበት በ50 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቀ፡፡ ከነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በፍትሕ ጋዜጣ ላይ በራሱና በጽሑፍ አቅራቢዎች አምስት ጊዜያት ታትመው በወጡ መጣጥፎች ምክንያት ክስ ተመሥርቶበት፣ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ዋስትና በመከልከሉ ማረሚያ ቤት እንዲቆይ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ክስ መሥርቶበት የነበረው የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ፣ ‹‹የማጣራው ምርመራ ስላለኝ እስከዚያው ድረስ ክሴን አቋርጫለሁ፤›› በማለት ነሐሴ 21 ቀን 2004 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ አማካይነት፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ነሐሴ 22 ቀን 2004 ዓ.ም. ከእስር ተፈትቶ ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ ላለፉት ሦስት ወራት አቋርጦት በድጋሚ በተንቀሳቀሰው ክስ ውስጥ ጋዜጠኛ ተመስገን በተለያዩ ጊዜያት ዕትሞች ‹‹ሞት የማይፈሩ ወጣቶች፣ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እስከ መጨፈር፣ የሁለተኛ ዜግነት ሕይወት እስከመቼና ሲኖዶስና መጅሊስ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ›› የሚሉ መጣጥፎች ማወጣቱ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም በወጡት መጣጥፎች ወጣቶችን ለአመፅ አነሳስቷል፣ ቀስቅሷል፣ ስም አጥፍቷል በሚል ነበር የመጀመሪያው ክስ የቀረበው፡፡ አሁንም የቀረበው ክስ ይኼው ነው፡፡

በትናንትናው ዕለት ዓቃቤ ሕግ ለምን ክሱን ማንቀሳቀስ እንደፈለገ እንዲያስረዳ ችሎቱ ጠይቆት፣ ፍትሕ ሚኒስቴር በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ክስን የማቋረጥና የመጀመር ሥልጣን እንዳልው ከመግለጽ ባለፈ በዝርዝር አላስረዳም፡፡ ፍርድ ቤቱ በሁለተኛነት ክስ የተመሠረተበትና የፍትሕ አሳታሚ የሆነው ማስተዋል የሕትመትና የማስታወቂያ ድርጅትም እንዲቀርብ አዞ፣ ክሱ መቀጠል አለመቀጠሉን በሚመለከት ብይን ለመስጠት ለታህሳስ 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ፍትሕ ጋዜጣ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ለሕትመት ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የገባ ቢሆንም፣ ‹‹ፍትሕ ሚኒስቴር እንዳታትም ብሎኛል›› በሚል ምክንያት ማተሚያ ቤቱ አላትምም ማለቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ጋዜጣው በወቅቱ ለምን እንዳልታተመ እስካሁን በግልጽ የተገለጸ ነገር ባይኖርም፣ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት በአቶ መለስ ዜናዊ ሕመምና በአጠቃላይ በወቅቱ ስለነበሩበት ሁኔታዎች የሚያትት መጣጥፍ ይዞ ስለነበር፣ ሕዝብን አላስፈላጊ ውዥንብር ውስጥ ይከታል በሚል ተሰግቶ መሆኑን የሚናገሩ አሉ፡፡ ጋዜጣው ከዚያን ጊዜ አንስቶ ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም፣ ጋዜጠኛ ተመስገን በማኔጂንግ ኤዲተርነት ‹‹አዲስ ታይምስ›› በሚባል መጽሔት ላይ እየሠራ ይገኛል፡፡(በታምሩ ጽጌ – ሪፖርተር)

ሞቃዲሾ የአጥፍቶ ጠፊ ፈንጂ ጥቃት ደረሰባት

ተሽከርካሪ ላይ ፈንጂ ያጠመደ አጥፍቶ ጠፊ ሞቃዲሾ ዉስጥ ራሱንና የሌሎች ሶስት ሰዎችን ህይወት ማጥፋቱን የጀርመን የዜና ወኪል ከስፍራዉ ዘገበ። ሌሎች ስድትስ ሰዎችም በፍንዳታዉ መጎዳታቸዉን ዘገባዉ አመልክቷል።

በአጀብ የሚጓዙ የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ለማጥቃት ያለመዉ አጥፍቶ ጠፊ ኢላማዉን ስቶ መንገድ ዳር የቆሙ ሰዎችን መጉዳቱን ዘገባዉ ጨምሮ ገልጿል። አንድ የሶማሊያ ፖሊስ ባለስልጣን ደግሞ በበኩላቸዉ አጥፍቶ ጠፊዉ ከራሱ በቀር ሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳላደረሰ ነዉ ለአሶሺየትድ ፕረስ የገለፁት። ከሶስተኛ ወገን እስካሁን የተሰማ ማረጋገጫ የለም። ለጥቃቱ አልሸባብ ተጠያቂ መሆኑ ተገልጿል።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule