• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከእሁድ እስከ እሁድ

December 31, 2012 07:34 am by Editor Leave a Comment

ጁነዲንና ኢህአዴግ ፊርማቸውን ቀደዱ

ከሚኒስትርነታቸውና ከኦህዴድ ስራ አስፈጻሚነታቸው በግምገማ እንዲነሱ የተደረጉት አቶ ጁነዲን ሳዶ ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ሰንደቅ ጋዜጣ መዘገቡ ይታወሳል። ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብታቸው ለማንሳት ፓርላማው በዝግጅት ላይ መሆኑን ይፋ የምክር ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ አስታውቋል።

ባለፈው ሐሙስ የዓመቱን ዘጠነኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ፕሮግራም ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በአራቱ ላይ ብቻ ተወያይቶ የቀረውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡ ሪፖርተር እንዳለው “የአንድ የምክር ቤት አባልን የሕግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሐሳብን መርምሮ ማፅደቅ” የሚል  ቢሆንም፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ይህንን በቀጣይ ስብሰባ ለመመልከት ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡ ምክር ቤቱ በስምንተኛ መደበኛ ስብሰባው ቃለ ጉባዔ፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅና ሌሎች አዋጆችን ማጽደቁ ታውቋል።

አቶ ጁነዲን ይመልከት አይመልከት ባይታወቅም ከአልጀዚራ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከሽብር ጋር በተያያዘ ባለስልጣንም ሆነ ማንም ከህግ በላይ አይደለም ማለታቸው ይታወሳል። አቶ ጁነዲን ባለቤታቸው ከሽብር ጋር በተያያዘ መታሰራቸው፣ እሳቸውም ባለቤታቸው በእናታቸው ኑዛዜ መሰረት መስጂድ ለማሰራት ከመንቀሳቀሳቸው ውጪ ሰሩት ጥፋት እንደሌለ ጠቅሰው በተለያዩ ጋዜጦች ማተማቸው አይዘነጋም። ሁኔታውን የሚከታተሉ አቶ ጁነዲንና ኢህአዴግ ፊርማቸውን ቀደዱ ብለዋል፡፡

ደህንነትና ጸረሙስና ሊቀናጁ ነው

የፌደራል የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ የሚፈጸሙ ሙስናዎችን ለመመርመር ይችል ዘንድ ከብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት የሚሰራ ግብረ ሃይል ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን ሪፖርተር አስታወቀ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ትኩረት የሚደረግባቸው ዋና ዋና ዘርፎች መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ በሚያንቀሳቅሳቸው የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የስኳር ፕሮጀክቶች፣ የባቡር መስመሮችና የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ላይ ነው።

በከፍተኛ ደረጃ ሙስና ቢስፋፋም ርምጃ ግን አይወስድም በሚል የሚታማው ኢህአዴግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሙስና ላይ ለመዝመት በተደጋጋሚ ዘመቻ እንደሚጀምር ቢያስታውቅም ተግባር ላይ ግን አይታይም። ጸረ ሙስና ኮሚሽን ሲቋቋም በተመሳሳይ ታላቅ ለውጥ ይመጣል ቢባልም ኮሚሽኑ የተጠበቀውን ያህል እንዳልሰራና በህወሃት ውስጥ ያሉትን ዋንኛ ሞሳኝ አሣዎችን ከማጥመድ ይልቅ ጥቃቅኑን ዓሣ በማጥመድ ትልቅ ሥራ እየተሠራ መሆኑን አሳማኝ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረገው አግባብ እንዳልሆነ የሚወቅሱ አሉ።

የዩኒቨርስቲው ዲን ተማሪውን ደፈረ

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተፈጸመ የተባለውን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ደብዛ ለማጥፋት ሲባል በተቀናጀ ሁኔታ የህክምና ማስረጃ እንዲጠፋ መደረጉን ዶቼ ቬሌ በሳምንቱ አጋማሽ ዘግቧል።ጉዳት የደረሰባት ተማሪ በደሏን ለሚመለከታቸው አካላት ብታቀርብም መፍትሄ አለማግኘቷ ታውቋል። አቤቱታዋን ካቀረበችበት ክፍል እስካሁን መፍትሄ አማግኘቷ አነጋጋሪ እንደሆነ ተመልክቷል።

ባለፈዉ ሕዳር መደፈሯ የተገለፀው ይህቺ ተማሪ በደሉ የደረሰባት በዩኒቨርሲቲዉ የተማሪዎች አገልግሎት ዲን በመሆኑ ጉዳዩ እንዲድበሰበስ አድርጎታል። ተፈፀመ የተባለዉን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ጥርጣሬ ደብዛ ለማጥፋት ተጎጂዋ ሃኪም ዘንድ የታከመችበትን ማስረጃ ሙሉ በሙሉ ማግኘት እንዳልቻሉ አንድ ስማቸዉ እንዳይገለጽ የጠየቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ለዶቼ ቬለ መግለጻቸው ታውቋል። እንዲህ ያለ አስነዋሪ ድርጊት ለሚፈጽሙ ወንጀለኞች መረጃ በማሸሽና በመደበቅ በሚተባበሩ የህክምና ባለሙያዎች ላይ ማህበረሰቡ ሊያወግዛቸውና በ“ህግ” ሊጠይቃቸው እንደሚገባ አስተያየት ተሰጥቷል።

ወሮበሎች የደፈሯት ወጣት አረፈች

በህንድ ኒዉዴሊ አስራ ሁለት ወረበሎች የደፈሯት ወጣት አረፈች። ወጣቷ ህይወቷ ያለፈው ለህክምና ሲንጋፖር ከሄደች በኋላ ነው። የሃያ ሶስት ዓመቷ ወጣት ህልፈትን ተከትሎ በህንድ ከፍተኛ ቁጣና ሃዘን ተቀስቅሷል። በአደባባይ ለተቃዉሞ የወጡ ሰልፈኞች ሟች ፍትህ እንድታገኝ እና በአገሪቷ የሚታየዉ ከፍተኛ የወሲብ ጥቃት እንዲቆም ጠይቀዋል።

ወጣቷ  ከሁለት ሳምንት በፊት በኒዉዴሊ አዉቶቡስ ዉስጥ ተሳፍራ ሳለ በስድስት ወንዶች በብረት ዱላ ተደብድባና ተደፍራ ከአዉቶቡሱ መወርወርዋ በተለያዩ መገናኛዎች ነው የተጠቆመው። አሰቃቂ የወሲብ ጥቃት የተፈፀመባት ወጣት በዉስጥ የአካላ ክፍሏ ላይ የደረሰባትን ጉዳት  የህክምና ባለሞያዎች ለማዳን ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ ህይወቷ ሊያልፍ ችሏል። በወጣቷ ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ በርካታ ሴቶች አደባባይ በመውጣት ሴቶች የተሻለ መብት ሊኖራቸው እንደሚገባ  ጠይቀዋል። በዋና ከተማዋ ኒዉዴሊ የተቃዉሞ ሰልፉን ተከትሎ ከፍተኛ የፀጥታ ሃይላት በየመንገዱ የተሰማሩ ሲሆን፤ የከርሰ ምድር የህዝብ ማመላለሻ ባቡሮች መዘጋታቸዉ ታዉቋል። ከአንድ ሳምንት በፊት የወሲብ ጥቃት የተፈጸመባትን ወጣት በማስመልከት በተነሳዉ ከፍተኛ ተቃዉሞ ሰልፍ በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።  አንድ ጸጥታ አስከባሪ ፖሊስ ህይወት አልፏል።

በዩኒቨርስቲ አማርኛ ፊደል ለይተው የማያውቁ አሉ

በኢትዮጵያ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቁልቁል እየተጓዘ የት እስኪደርስ እንደሚጠበቅ ግራ እንደገባቸው በአዲስ አበባ የሳይንስ አካዳሚ ምሁራን አመራሮች ባጠኑት ጥናት አስታወቁ። ጥናቱ በትግራይ፣ በአማራ፣ በደቡብ ክልልና፣ በኦሮሚያ በተመረጡ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የተካሄደ ሲሆን፣ የአሜሪካ ሬዲዮ ዘጋቢ እንዳስታወቀው ችግሩ የነበረ፣ ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው። ከአጥኚዎቹ መካከል ፕ/ር ፉርዳሳ ጀቤሳ “ትምህርቱ እያሽቆለቆለ ሄዷል፤ ወድቋል” ሲሉ፣ ፕ/ር ባዬ ይማም በበኩላቸው “አማርኛን በዋና ትምህርትነት ለማጥናት ከሚመጡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ፊደል ለይተው የማያውቁ አሉ” ብለዋል። “ሳ” እና “ሶ” መለየት አቅቷቸው የሚጠይቁ እንዳጋጠሙዋቸው ተናግረዋል። ችግሩ በኦሮሚኛ ቁቤ ትምህርትና በትግርኛ ላይም እንዳለ አረጋግጠዋል። በጥናቱ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ተወካይ “ችግር ቢኖርም በጥናቱ እንደተቀመጠው አይደለም” ሲሉ ተቃርነዋል።

በጥናቱ እንደተገለጸው ተማሪዎችን በማደራጀት፣ስብሰባ በመጥራት፣ሪፖርት እንዲጽፉ በማድረግ ዋናውን የክህሎትና አመለካከት የማሳደግ ስራ እንዲዘነጋ ተደርጓል።ችግሩም በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ አንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያን 30ሺህ ትኬት ገዙ

ደቡብ አፍሪካ በሚዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለመደገፍ ትኬት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ክፍተኛ መሆኑ ታወቀ። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን/ካፍ/ የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ እንዳስታወቀው በአንደኛ ደረጃ በርካታ ትኬት የገዙት የዛምቢያ ደጋፊዎች ሲሆኑ 50ሺህ ቲኬት ገዝተዋል። ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን 30ሺህ ቲኬት በመግዛት ሁለተኛ ደረጃ ሲይዙ፣ የአልጄሪያ ደጋፊዎች 15 ሺህ ቲኬት በመግዛት የሶስተኛ ደረጃ ይዘዋል።

ከሰላሳ አንድ ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የገባው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባላት ለውድድሩ ብቁ መሆናቸው ከተረጋጋጠ በኋላ የሚቀርብላቸው ውዳሴና ሙገሳ ስለበዛ እንዳያዘናጋቸው ስጋት የገባቸው ወገኖች ሚዲያዎች መረጃና ጠቃሚ ሃሳብ በመስጠት አገራዊ ግዳጃቸውን ያለ ይሉንታ ቢወጡ እንደሚሻል ጠቁመዋል። ለመወዳደሱ ከውድድሩ በኋላ በቂ ጊዜ እንዳለ የሚጠቁሙት ክፍሎች ሁሉም ሚዲያዎች ተመሳሳይ አቋም በመያዝ የድግስና የሽልማት ወሬ ላይ ተጠምደዋል። ቡድኑ ከባድ ሽንፈት ቢገጥመው እነሱም ከመወቀስ አያልፉም ብለዋል። ጋዜጠኛ ከተስካርና ከድግስ ወሬ ይልቅ ቡድኑን ሊጠቅሙ የሚችል መረጃ ወደመስጠት ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule