
የአማሮ ህዝብ (ኮሬ ጎሳ) እና በጉጂዎች መካከል ከእሁድ (23 ጁላይ) ምሽት ጀምሮ ከባድ በሆነ የድንበር ግጭት መቀስቀሱን ወደ ስፍራው የተጓዙ እማኞች አረጋግጠዋል። ከእሁድ ምሽት ጀምሮ በተነሳው የጎሳዎች ግጭት እስከአሁን ያልበረደ ሲሆን በግጭቱ ሳቢያ በርካታ ቤቶች በመቃጠል ላይ መሆናቸውን ስፍራው ድረስ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ችለናል።
በፎቶው ላይ እንደሚታየው በተነሳው ቃጠሎ አካባቢው በጭስ እየተሸፈነ ይገኛል።
የአማሮ መንገድ በግጭቱ ሳቢያ ስለተዘጋ ወደ ዲላ ከተማ መውጣትም ሆነ ወደ ወረዳዋ መግባት እንዳልተቻለ የአይን ምስክሮቹ ገልጸዋል። የጸቡ መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን በውል ባይታወቅም የሚመመለከተው አካል ጉዳዩን ችላ እንዳለውም ለማወቅ ተችሏል። አንዳንድ ታዛቢዎች ወያኔ አሁን ከገባበት ማጥ ለመውጣት ሲል እንዲህ አይነት ግጭቶችን ሆን ብሎ እንደሚያስነሳ ይናገራሉ። የጎሳ ፖለቲካን በሃገሪቱ ላይ የዘራው የህወሃት ስርዓት በጎሳዎች መካከል በሚደረግ ግጭት ሳቢያ ራሱን በስልጣን ለማቆየት እየተጠቀመ መሆኑ አይዘነጋም።
በአሁን ሰዓት በመላ ሃገሪቱ ኢ-ፍትሃዊ የሆነውን የግብር አዋጅ በመቃውም የተነሳው የስራ ማቆም አድማ እና አመጽ አገዛዙን እየነቀነቀው የሚገኝ ሲሆን እልቂት እያስከተለ ያለው በጉጂ እና በአማሮ የተከሰተው ግጭት አስተዳደራዊ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ አይገመትም።
(ሰበር ዜናውን ከምስል ጋር ያደረሰልን ክንፉ አሰፋ ነው)
Leave a Reply