የአዜብ አስናቀና የሙሉ ወ/ገብርኤል ክስ ትህነጎችን አበሳጭቷል፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዛሬ ባወጣው መረጃ መሠረት “የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ” ተመስርቶባቸዋል።
በዚህ የክስ መዝገብ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኮሎኔል ሙሉ ወልደ ገብርኤልን ጨምሮ 50 ሰዎች ይገኙበታል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ የሚያርፍበት 123,189 ሄክታር ስፋት የሪዘርቬየር ክሊሪንግና ባዮማስ ዝግጅት ስራ ደኖችን የመመንጠር፣ የማጽዳትና ከአካባቢው (ከግድቡ አርቆ) ወደ ተዘጋጀለት ቦታ የማጓጓዝ ሥራን ለመስራት ከኢፌዴሪ ብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር በብር 5,158,611,599.03 (አምስት ቢሊዮን አንድ መቶ አምሳ ስምንት ሚሊዮን ስድስት መቶ አስራ አንድ ሺ አምስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ከ ዜሮ ሦስት) በተዋዋሉት ውል መሠረት ስራው መጠናቀቅ በሚገባው ጊዜ መጠናቀቁን ባለመቻሉ ከፍተኛ መጠን ያለው የመንግስት ገንዘብ እንዲባክንና ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ በመሆኑ ሁሉም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ተከሳሾች በፈፀሙት በስልጣን አላግባብ መገልገል፣ አንዳንዶቹ የማይገባ ጥቅም ለራሳቸው ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ እና ሃላፊነታቸውን በመጠቀም ከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል።
የወ/ሮ አዜብና የኮ/ሎ ሙሉ መታሰር እንደተሰማ አፍቃሪ ትህነጎችና ዲጂታል ወያኔዎች የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ጀምረዋል። ጉዳዩንም ከህዳሴ ግድብና ከግብጹ ፕሬዚዳንት ጋር በማገናኘት ግለሰቦቹ የታሰሩት በሥልጣን ላይ ያለው የዐቢይ መንግሥት የግብጽን አጀንዳ አስፈጻሚ በመሆኑ ነው ብለዋል። ሆኖም አብረው የተከሰሱ በርካታ ግለሰቦች መኖራቸውና ከዚህ ቀደም የኤልፓ ችግር በዚህ መልኩ ከሜቴክ ጋር ተያይዞ ያልቀረበ በመሆኑ ገና ይፋ የሚሆኑ ብዙ “ጉዶች” ይኖራሉ የሚል ግምት ባብዛኛው ይሰጣል። የትህነጎችና የዲጂታል ወያኔዎች ጫጫታም የሚመጣውን አስቀድሞ ለመከላከል ከመነጨ እንደሆነ ተገምቷል።
ከዚህ በፊት “አይ አዜብ” በሚል ርዕስ የታተመው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply