• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሰላማዊ ሰልፉን ከበካዮች (Contaminants) እንጠብቀው!

May 31, 2013 10:20 pm by Editor 1 Comment

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ይደረጋል የሚል ዜና ዘሃበሻ ድረ ገጽ ላይ ሐሙስ ምሽት ተመለከትኩት። አንድነት ፓርቲ እና መኢአድም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በአንድነት መቆማቸውን እና መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን መፍቀዱን ጨምሮ ይገልጻል ጽሑፉ። ወዲያውኑ ሰላማዊ ሰልፉ እንከን የለሽ እንዲሆን እጅጉን ተመኘሁኝ። የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ እንደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ተቃውሞ በድስፕሊን የታነጸ እና ክብርን ከመንግስት ሳይቀር የሚጎናጸፍ እንዲሆን እጅጉን ተመኘሁ። የበኩሌንስ ምን አስተዋጽኦ ላድርግ ብዬ ተጨነቅኩ። ይኽን ጽሑፍ በችኮላ እንዳዘጋጅ የገፋፋኝ እሱ ነው።

የሰላም ትግልን ሊበክሉና ለአደጋ ሊያጋልጡት ከሚችሉ ተግባሮች፣ አሰራሮች እና ሁኔታዎች ውስጥ ጥቂቶቹን አንስቼ በአጭር በጭሩ ልበልና ልሰናበት።

(1ኛ) ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ በመንግስት ወይንም በመንግስት ደጋፊዎች አማካኝነት የሚፈጸምበትን የሽብር ጥቃት ለመመከት ሲል የሚፈጽመው ማንኛውም አይነት የኃይል እርምጃ ሰላማዊ ሰልፉን ሊበክል እና ውድቀት ሊያስከትልበት ይችላል። ስለዚህ የዲሞክራሲ አራማጅ የሆነው ወገን ለሽብር መልሱ ሽብር ነው ከሚለው ፍልስፍና መራቅ አለበት። ሰላማዊ ትግል ወደ ኃይል እርምጃዎች ከተንሸራተተ በሰላማዊ መንገድ ለነፃነት መታገል የጀመረው ህዝብ እምነት ሊተን ይችላል። ህዝብ ሁከት አይወድም። ለሽብር መልሱ አለመሸበር መሆን አለበት።

(2ኛ) የሰላም ትግል አመራር የወጣቶች እንዲሁም በእድሜና በተመክሮ የበሰሉ ሰዎች ቅይጥ ቢሆን ለበካዮች ቀዳዳ ላይከፍት ይችላል። በድስፕሊን የታነጸ ግራና ቀኙን የሚያይ እና ሰላማዊ ሰልፈኛው ውስጥ ጸብ ጫሪ ተግባር እንዳይፈጸም የሚጠብቅ በሰላም ትግል መርሆዎች የሰለጠነ ኃይል መሰማራት አለበት።

Party-flyer(3ኛ) በድርጅቶች ህብረት-አመራር ዘንድ የሚታይ ክፍፍል የሰላም ትግልን ይበክላል። ገዢው ቡድን ደጋፊዎቹን በመላክ ወይንም ከሰላም ትግል አመራር ውስጥ ህሊና ደካሞችን በጥቅም በመግዛት ወሬ እንዲያቀብሉት (informants) ሊያደርግ እንደሚችል ቀደም ተብሎ ሊታሰብበት ይገባል። እነዚህ የመንግስት ወሬ አቀባዮች ለውይይት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ ሆን ብለው ስምምነት እንዳይኖር እያደረጉ ዞር ብለው ደግሞ ለሰላማዊ ታጋዩ ህዝቡ ስምምነት ጠፋ ይሉታል። ህዝብ በክፍፍሉ የተነሳ በትግሉ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ። ከፍራቻ መውጣት እና መታገል እንዲሳነው ለማድረግ። ስለዚህ የዲሞክራሲ ኃይሎች ህብረትን ማጠናከር እንዳይሳናቸው እና ጸብ ጫሪ ሰርጎ ገቦች (agent provocateurs) ምኞታቸው እንዳይሳካ መደረግ አለበት።

(4ኛ) የሲቪክ ድርጅቶች አመራሮች በአምባገነኖች ቁጥጥር ስር ከሆኑ የሰላም ትግል በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተበክሏል ማለት ይቻላል። ለምሳሌ የመምህራን፣ የሰራተኛ፣ የወጣቶች ማህበራት አመራሮች በገዢው ቡድን ቁጥጥር ስር ከሆኑ እነዚህ ተቋሞች የመጨቆኛ አጋዥ ምሶሶዎች ሆነዋል ማለት ነው። ነፃ ማውጣት አሊያም ሊላ ትዩዩ (Parallel) ድርጅቶች መመስረት ያስፈልጋል። እነዚህ ተቋሞች የነፃነት ትግልን ኃላፊነት ለእያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመበትንም ይጠቅማሉ። ወጣቱ ብቻ የሁሉም ህብርተሰብ ነፃ አውጪ ሊሆን አይችልም። (5ኛ) በሰላም ትግል ኃይሎች የሚሰጡ መግለጫዎች አግላይነት ከታየባቸው የተገለለው ወገን ወደ ጸበኛነት እንዲሄድ በማድረግ የሰላም ትግል ሊበከል ይችላል። ለምሳሌ የአንድ ተቃዋሚ ድርጅት አባል ሲታሰር የሁሉም ድርጅቶች ጉዳይ ሊሆን ይገባል። መንግስት ሁሉንም በወዳጅ አይን እንደማያያቸው እና ቢቻል ሁሉም ቢጠፉለት እንደሚፈልግ መዘንጋት የለብንም። ጥቃቱ ተራ ጠብቆ የሚመጣ መሆኑ ታውቆ አንዱ ሲጠቃ ሁሉም እንደተጠቃ በመውሰድ በአንድነት መቆም ጠቃሚ ነው።

(6ኛ) የመንግስት ወሬ አቀባዮች (informers) ካሉበት የሰላም ትግል የመንግስት መልክተኛ ቆስቋሾች (agent provocateurs) ሰርገው የገቡበት የሰላም ትግል ይበልጥ ተበክሏል (Contaminated) ሊባል ይችላል። የመንግስት ወሬ አቀባዮች (informers) የሰላም ትግልን አቅምን እና እቅዶችን ለመንግስት ይዘግባሉ። የመንግስት መልክተኛ ቆስቋሾች (agent provocateurs) ግን ሆን ብለው የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋሉ ወይንም እራሳቸው ድንጋይ ይወረውሩ እና ህግ አክባሪው ሰላማዊ ሰልፈኛ እንዲመታ ያደርጋሉ። በሰላም ትግል ኃይል ውስጥ ብጥብጥ ያነሳሳሉ። ለኃይል መልሱ ኃይል ነው የሚል አዝማሚያ በማራመድ የሰላም ትግል መንግስትን በደካማ ጎኖቹ እንዳይገጥመው ያደርጋሉ።

(7ኛ) ፖሊሶች ከከተማው ህዝብ ጋር ተቀላቅለው ስለሚኖሩ ጥሩዎቹን ልናርቃቸው አይገባም። ለምሳሌ ጎረቤቴ የሆነ ፖሊስ እኔ ፍጹም የሰላም ትግል አማኝ መሆኔን እንዲያውቅ አድርጌው ሳለ ድንገት ከፖሊስ ጣቢያ እከሌ ሽብርተኛ ነው እና ይዘህ አምጣ የሚል ትዕዛዝ ቢሰጠው ለአለቃው ሽብርተኛ አለመሆኔን ሊናገር ይችላል።

ለራሳችን ጊዜ ሰጥተን ቁጭ ብለን ብናሰላስል ሌሎች በርካታ ብክለት ሊጋብዙ የሚችሉ ሁኔታዎችን ማግኘት እና እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ማስላት እንችላለን።

ግርማ ሞገስ
ግርማ ሞገስ

ፍጹም ሰላማዊ እና እንከን የለሽ እንዲሆን ምኞቴ ነው!

(girmamoges1@gmail.com)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    June 1, 2013 07:06 am at 7:06 am

    ግርማ ሞገስ ያለው ምክር ነው !
    አይሆንምን ትተህ ይሆናልን ጠርጠር በለው!!
    “ሀገሬ የሕዝቦቿ መሆኗን እንዳውቃት
    ሠላማዊ ሠልፍ ወጥቶ ህዝብ ተናግሮባት”!!
    //////////\\\\\\\\\\\\\\//////////////\\\\\\\\\\/////////
    ፩)መደማመጥ፣ ማለም፣ በሥራ መተርጎም፣ በአንድ አመራር መሄድ፣ ተመሪዎች አብሮአቸው የሚያመራውንና የሚያወራውን ይለያሉ።
    ፪) በትውልድ መካከል የዕውቀትም የሥራም የገጠመኝን ልምድ ያለማንቋሸሽ መቀበል ከራስ ግላዊ ሐሳብ ጋር ማመዛዘን ሎችንም ሀሳብ መጋራትና በተሻለው መቀጠል። አሉባልታ ጥርጣሬ ፍራቻና ጎጠኝነትን ከወያኔ አለመኮረጅ።
    ፫) ከደቦ ድብልቅልቅ፣ የተናጠል የግለሰቦች ጥናት የሐሳብ ልውውጥ ማንነታቸውን ይገልፃል፡ በአብዛኛው ተንኮለኞች ጥሩ ሠዎች ትከሻ ላይ ተንጠላጥለው በሠፊ ትከሳ ተከልለው ያጠፋሉ።ማ፣ ማነው? አመለካከቱ ሥራው ሀገራዊና ወገናዊ ፍልሥፍናው የተቀዳ ነው ወይንስ ረስ ፈለቅ ዕውቀትና ግንዛቤ አለው?አብዛኛው አስመሳዮች የተባለን ሲደግሙ ይያዛሉ። የራሳቸው የሆነ ምንም ዕውቀት የሌላቸው ውይይት ፈሪዎች ግን ጉልበተኞች ተሳዳቢና ቁጡዎች ናቸው።
    ፬)የተማረ ብቻውን ሀገር ነፃ ያወጣል የሚል ድንጋጌም ባይኖር ይራዳል።አንዳንድ ምሁራን አድርባዮች መፅሐፍ አሳትሞ ለመበልፀግ፣ ወይንም ዝናቸውንና ሥራቸውን በቲቪ የሚያሳዩ፣ በሥብሰባ አዳራሽ ቀፈታቸው ላይ ከረባት አጋድመው ተለጥጠው የሚቀመጡ፣ ባለሥልጣን ሲያዩ የሚቁነጠነጡ፣ በድንኳን የፀሐይ መነፅር የሚያደርጉ፣ምግብ ባለበት ባርኔጣና የአንገት ልብስ ደርበው የሚኮፈሱ፣የሀገር ሸክም እንጂ የሠለጠነ ሥርዓት ገንቢና አራማጅና አስተማሪ አይሆኑም።
    ፭) ለመሆኑ ሠላም! እኩልነት! የመሥራትና የመዘወዘወር መብትን የማይፈልግ ተቃዋሚ አለን?። ይህንን እንዳይኖር የፈለገ ደጋፊ ኢህአዴግን ተደግፎ ቆሟል አወዳደቁ አያምርም በፀና ዓላማ ላይ ያልተመሠረቱ የውሸት ፋውንዴሽን ያላቸው ሁሉ ምን በአዋጅ ቢቋቋሙም ብዙ አይቆሙም በለው!!”በአንድ ዓላማ ለመሳተፍ ኅብረት አስፈላጊ ብረት ነው”። ፮)የግለሰቦች ንብረት እንዲያወድም፣ የሀገር ሀብት እንዲያጠፋ፣ተቋማት የሚዘርፍና መሳሪያ ታጥቆ በሰላማዊ የሀገሬውን ሰው ህይወት የሚቀጥፍ ሁሉ ቅጥረኛ.. ወራዳ.. ሌባ.. ባንዳ ነው!!።
    ፯) ማናቸውም የሀገሪቱ ሰላም አስከባሪ አካላት የኢህዴግ ወይንም የሌላ አካል የግል ዘበኞች አደሉም። ሁሉም የሀገሩ ዜጋ ያለ ፆታ፣ ዘር፣ ብሔር፣ቋንቋ፣ክልል፣እምነት ልዩነት ሁሉም የሰው ልጅ ወይንም ዜጋ ሙሉ ጥበቃ ሊደረግለት ህጉም ወታደሩ ወይንም ፖሊሱ የገባው የሥራው ቃል ኪዳን… ወይመ ቃለ-መሓላ ያዘዋል በዚያም ይገዛል። አንዳንድ ከራሳቸው የትምህርት ማነስም ይሁን፣ ከአሰተዳደግ በደል፣ ሀገርንና ሕዝብን፣ ለፓርቲና ለግል ለጥቅም፣ አሳልፈው ይሰጣሉ። በወጣቱም ይሁን በተበዳዩ ህዝብ ጥላቻን ያተርፋሉ መሆን ያለበት በመቀራረብ፣ መተማመን ዓላመን ማስተማር፣በመንግስት ስለተቀጠሩ ሀገር መከላከያን መጥላት በር ከፍቶ ተዘረፍኩ ማለት ሲሆን፣ የህዝብ ድጋፍ የሌለውም ሠራዊት(ወታደር/ፖሊስ) ዛፍ ላይ እንቅልፍ የወሰደው ‘ድብ’ መሆኑ ነው። ለልጆቹ ኩርማን እንጀራ መግዣ የተቀጠረ የድሃ ቤተሰብ ወታደር፣ ህንፃ ከሚያከራየው ‘የነጋዴ ከገበያ አውጭ’ ‘የትግራይ ነፃ አውጭ’ከእነማዕረጉ ‘የፈንጅ ሀገር ዕቃ አምጭ”የመሬት ሻጭ’ ሲሆንም በአርግጥ ወታደሩ አመኔታን አጥቷል። ለወጣቱ የሚመከረው ከተራው ድሃ ፀጥታ አስከባሪ ጋር መስማማት የበለጠ ድል አለው በለው! አዎን፣ ሠላም እንዲሠፍን ስናስብ፣ ሠላም ያለው ነገር እንሥራ! ኢህአዴግ ለፓርቲ አባላትና ሹማምንት የሠጠውን መሬት ለሌላውም ዜጋ መግዛትም መሸጥም መብት ባይኖረውም፣ እንዲሄድበት እንዲናገርበት እንዲሠለፍ፣እንዲቦርቅበት ይፍቀድ!የሠጠውም የመሬት የ፺፱ዓመት የተንቦረቀቀ ኪራይ ከገቢ ውጪው ባይታወቅም፣ ሕዝብ ለመንግስት አለውን ቅሬታ ላማሳወቅ መሰለፍ መበት እንዳለው ማወቅ ግድ ይላል። ማስፈራራት፣ መዋሸት፣መቀፍደድ ይቀም ሠራዊቱም ከሕዝብ ይቁም!አሻጥረኛ! ፀረ-ሕዝብ! ሙሰኛ ኪራይ ሰብሳቢ ይውረድ! ይዋረድ! የተጀመረው የዓባይ ወንዝ ግደብና ያባይ እንባ ሁሉ ይቀጥል!!ሠላም!አሁንም ሠላም! አሁንም እደግመዋለሁ ሠላም በለው! ሠላም። አራት ነጥብ። በቸር ይግጠመን ከሀገረካናዳ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule