• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ

February 13, 2020 05:07 pm by Editor Leave a Comment

“በየቦታው የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ዋነኛ ችግር የፖለቲካ አመራሮች እጅ” አለበት

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የተወሰዱ እና ሊወሰዱ ይገባቸዋል ስላላቸው እርምጃዎች የካቲት 5፣ 2012 መግለጫ አውጥቷል። በየቦታው የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ዋነኛ ችግር የፖለቲካ አመራሮች እጅ እንዳለበት የገለጸው መግለጫ ለሀገሪቱ ደህንነትና ለህዝቡ ህልውና ሲባል ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን እንደማይታገስ አቋም መያዙን ይፋ አድርጓል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠ መግለጫ

የሕግ የበላይነትን ማስከበር ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱን የማጠናከርና የህግ የበላይነትን የማክበርና የማስከበር ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወሳል። በተለይም መንግሥት የሕግና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻልና በዘርፉ አሳታፊነትን ለማጎለበት በሰጠው ትኩረት መሠረት ከመንግሥት መዋቅር ውጭ ከፍተኛ ልምድና ብቃት ያላቸውን የሕግ ባለሙያዎች ያካተተ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች አማካሪ ጉባዔ በማቋቋም የሰብዓዊና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ሊያሰፉ የሚችሉ ህጎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

አንዳንዶቹ ከ20 ዓመት በላይ ለማሻሻል ተብሎ ከፍተኛ የሀብት ብክነት ሲፈፀምባቸው የነበረው በአማካሪ ጉባኤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሻሻል የተደረጉት ተጠቃሽ ናቸው።

የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋትና ህዝባችን በፍትሕ ሥርዓቱ ያለውን አመኔታ ለማሻሻል በተወሰደው የማሻሻያ እርምጃ ለህዝባችን ተስፋን ያሰነቁ ተግባራት ተፈፅመዋል።

በሌላ በኩል የህግ ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ ጋር በተያያዘ በከባድ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በጅምላ ጭፍጨፋ እና ከባድ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የዚህ ድርጊት ተሳታፊ የሆኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንዲታይ ተደርጓል።

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተበራከቱ የመጡ የወንጀል ተግባራት በተለይም በብሔር ወይም በክልሎች መካካል በግለሰቦችና ቡድኖች በሚፈጠር ግጭት መነሻነት ወንጀል የተፈጸመባቸው አካባቢዎች ዋና ዋና ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ሥር እንዲውሉ በማድረግ የተደራጀ የምርመራና ክስ የመመሥረት ሂደት ላይ እንገኛለን።

በዚህ መሰረት፣ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ጉጂ ዞን እና በደቡብ ክልል ጌደኦ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች፣ በሶማሌ ብሔራዊ ክልል በጅግጅጋና ሌሎች ዞኖች፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ካማሽ ዞን፣ መተከል ዞን፣ በደቡብ ክልል በሀዋሳ፣ በቴፒና ሸካ ዞን፣ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ ዞን፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ሸዋ እና አዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ በአዊ ብሄረሰብ ዞን በጃዊ ወረዳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባ በሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም በአንዳንድ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተፈጸመውን ወንጀል ድርጊቶችን መነሻ በማድረግ ተጠሪጣሪዎችን ቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራ ተጀምሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም በክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ የፌደራል የፍትህና የጸጥታ መዋቅር አመራሮች እንዲሁም የክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮችና የፍትህና የጸጥታ መዋቅር አመራሮች ባካሄዱት አስቸኳይ ግምገማ ለውጡን ተከትሎ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ማንነትን መሠረት ያደረጉ፣ በሃይማኖት ተቋማት ላይ እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች እንዲሁም በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን ለፍርድ ለማቅረብ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት ህዝቡን ይዞ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

መንግሥት በለውጡ ማግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በህግና ፍትህ ስርዓቱ ላይ እመርታዊ ለዉጥ ለማምጣት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን እንደነበረ እሙን ነው።  የፍርድ ወሳኔ ያገኙና ጉዳያቸው በምርመራ ላይ ያሉ ተጥርጣሪዎችን በምህረት አዋጅ ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል። በርካቶቹ በይቅርታ ከእሥር እንዲፈቱ ተደርገዋል። ይህ የመንግሥት ሆደ ሰፊነትን ያልተረዱ አንዳንድ አካላት ኢ-መደበኛ በሆነ ቡድናዊ አደረጃጀት በርካታ ወንጀሎችን ሲፈጽሙ ተሰተውሏል። በዚህም ክቡር የሰው ልጅ ህይወት ጠፍቷል፣ የሕዝብና የመንግሥት ሀብትና ንብረት ተዘርፏል፣ ወድሟል። ስለሆነም ከእንግዲህ ወዲህ ለሀገራችን ደህንነትና ለህዝባችን ህልውና ሲባል ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን እንደማይታገስ ጽኑ አቋም ተይዟል።

ከፍተኛ አመራሩ ባደረገው ግምገማ በየቦታው የሚፈጠሩ የወንጀል ድርጊቶች ዋነኛ ችግር የፖለቲካ አመራሮች እጅ ያለበት መሆኑን በሚገባ የተረዳ ሲሆን፥ ይህን የማይገባ ተግባር ሲያስፈጽም እና ሲፈፅም በዝምታ ሲያልፍ የነበረው አመራር ከዚህ እንዲታረም በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ ይፈልጋል።

በሀገሪቱ በሚፈለገው መጠን የህግ የበላይነትን በማስከበር ዘንድ የነበረውን ፈተና ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የምንሻገረው እንደሚሆን እሙን ነው። ስለሆነም ይህን ህገ ወጥ ተግባራትን የምንሸከምበት ጫንቃ እና በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ለፍርድ የማናቀርብበት ምንም ምክንያት የማይኖረን መሆኑን እንገልጻለን።

ስለሆነም በዛሬው መድረካችን በተፈጸሙ ወንጀሎች ላይ የተሳተፉ አካላትን በህግ ፊት ለማቅረብ፣ የዜጎች ሰብዓዊ መብት ጥሰት ለመከላከል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲሁም ተጠርጣሪዎች በሕግ ፊት እንዲቀርቡ በሚደረገዉ ጥረት ላይ የሚያደናቅፉ አካላት ላይ ያለምንም ምህረት በማያዳግም ሁኔታ ተጠያቂ የሚያደረግ መሆኑን መግለጽ ይፈልጋል።

በሌላ በኩል ከወንጀል ድርጊቶች ጋር በተያያዘ የተጀመረው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለፍርድ የማቅረብ ሂደቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፤ በዚህም የህግ የበላይነትን የማስከበር እንቅስቃሴ ለድርድር አይቀርብም። ኅብረተሰቡም ጥፋት ፈፃሚዎችን ለህግ ለማቅረብ በሚደረገው ርብርብ እንደ ወትሮው ሁሉ አሁንም የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን።

ኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
የካቲት 5 ቀን 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics Tagged With: AG, Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule